Fira

Fira

Share

Photos from Fira's post 13/04/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የኢፌድሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

አቶ ቴዎድሮስ ወልደሚካኤል የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማዕድ ባጋሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት አስተዳደሩ አቅም ለሌላቸው እና በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን በአልን በአብሮነት እንዲያሳልፉ እንዲሁም አብሮነትን የሚያጠናክሩ የሰው ተኮር ተግባራትን በተለያዩ ወቅቶች ማከናወኑን አንስተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በመልእክታቸው ማዕድ በማጋራት የቆየው ኢትዮጵያዊ ባህል እና እሴቶች በመጠበቅ አብሮነትን እና መደጋገፍን በማጠናከር አረጋዊያንና አቅም የሌላቸው ዜጎች በአሉን በደስታ ለማሳለፍ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ከለዉጡ ወዲህ መንግስት ለሰዉ ተኮር ተግባራት ትኩረት በማድረግ የዜጎችን ህይወት የቀየሩ የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠቅሰዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሚ ሙሄ አሊ በበኩላቸው በበአላት ወቅት የሚካሔዱ ሰዉ ተኮር ስራዎች የአንድነት የመተሳሰብ አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን ከማጠንከር ጎን ለጎን እሴቶቻችንን የበለጠ በማጠናከር ወንድማማችነትንና አብሮነትን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚረዳ ገልፀዋል።

የትንሳኤን በዓል ሲከበር እርስ በርስ በመተሳሰብ በመደጋገፍ በመረዳዳት ሊሆንም ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

በመርሀ-ግብሩ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ፣ የክ/ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ቅ/ጽ/ቤት አቶ ኃላፊ አቶ አሚ ሙሄ አሊ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

13/04/2026

What a message from our pm

TikTok · motivational_zadi2, 1651 likes, 209 comments. “When God start's blessings you.....😊✨❤️ Denzal Washington Best motivational quotes” 12/03/2026

TikTok · motivational_zadi2, 1651 likes, 209 comments. “When God start's blessings you.....😊✨❤️ Denzal Washington Best motivational quotes” 1651 likes, 209 comments. “When God start's blessings you.....😊✨❤️ Denzal Washington Best motivational quotes”

Photos from Fira's post 26/02/2026

በአዲስ አበባ የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ

በአውሮፓውያኑ1962 አንድ ደቡብ አፍሪካዊ ወጣት አዲስ አበባ ኮልፌ በሚገኘው የፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ታየ።

በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የነበረውን ዘረኛና ጨቋኝ የአፓርታይድ ሥርዓት በቃ ለማለት፣ ወታደራዊ ስልጠናና ስልታዊ ዕውቀት ፍለጋ ወደ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያቀናው ወጣት ኔልሰን ማንዴላ ነበር።

በወቅቱ ወጣቱ ኔልሰን ማንዴላ ኢትዮጵያን ፓስፖርት ተዘጋጅቶለት በአዲስ አበባ ኮልፌ የፌደራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ውስጥ ለጥቂት ወራት ቆይቶ ወታደራዊ ስልጠናም ወስዷል።

ዛሬ ያ ታሪካዊ ቦታ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ በዘመናዊ መልክ ታድሶና ተገንብቶ ወደ ዘመናዊ ሙዚየምነት ተቀይሯል።

በኮልፌ የፌደራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ ውስጥ የሚገኘው የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም እና የፖሊስ መኮንኖች ክበብ የዕድሳትና ጥገና ሥራ ተጠናቆ፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በይፋ ተመርቋል።

ሙዚየሙ የነጻነት ታጋዩን የኔልሰን ማንዴላን ገድል ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የነጻነት ትግል ያበረከተችውን የማይተካ ሚና ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ የታሪክ ማህደር ሆኖ ያገለግላል።

በምርቃቱ መርሃ ግብር ላይ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር፣ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Photos from Fira's post 20/02/2026

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

በብልፅግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያዘጋጀውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ የማድረግና የማስተዋወቅ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩም ክቡር አቶ ቴወድሮስ ወ/ሚካኤል ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፣በሀገራችን ለዘመናት የነበሩ መንግስታት የዴሞክራሲ ስብራትን መጠገን ባለመቻላቸው ለዘርፈ-ብዙ ችግሮች ተዳርገን ቆይተናል ብለዋል።

ብልጽግና ባካሄደው ሀገራዊ ሪፎርም የዘመናት ስብራት የነበረው የዴሞክራሲ እጦት ከመጠገኑም በላይ አካታች ዴሞክራሲን መተግበር እንደተቻለ ገልፀዋል።

ብልጽግና በሀገራችን የነበሩ ፅንፍ አመለካከቶችን ወደ መሃል በማምጣት እዉነተኛ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት ማድረጉን አስገንዝበዋል።

የፓርቲው ማኒፌስቶ ዋነኛ ማጠንጠኛ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሆነም አቶ ቴወድሮስ በንግግራቸው አስምረዋል።

አቶ አሚ ሙሄ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር በበኩላቸው፣ ፓርቲያችን ብልፅግና ሀገር በቀል በሆነው የመደመር እሳቤ በመመራት ቃል በተግባር በመግለጥ በርካታ አለም አቀፍ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ በርካታ ድሎች ማስመዝገቡ አስረድተዋል።

አቶ አሚ አክለውም ብልጽግና በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል ማኒፌስቶ ማዘጋጀቱንና የመወዳደሪያ ምልክቱም "የስንዴ ነዶ" መሆኑን ገልፀው ። ማኒፌስቶው ኢትዮጵያን ወደ ተሟላ ብልጽግና በማሸጋገር በአፍሪካና በዓለም ተምሳሌት ሀገር እንድትሆን ፓርቲዉ ያለዉን ቁርጠኝነት ያመላከተ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የፓርቲያችን ብልፅግና የ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የስንዴ ነዶ ምልክት ያደረገበት ምክንያት የመደመር፣ የአንድነት ፣የትብብርና የሉዓላዊነት መገለጫ ማሳያ መሆኑን ያመለክታል ከዚህ በመነሳት የሀገራችን እድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ሉዓላዊነታችንን በማስጠበቅ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር የማሻገር ትልም እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑ አቶ አሚ አስገንዝቧል።

በመድረኩ ላይ የጠንካራ ሀገር በፕሮግራሙ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ ይፋ የተደረገ ሲሆን የመደመር፣ የብልፅግና፣ የልዕልና ትርጉም ያለው የብልፅግና ፓርቲ መለያ ምልክት 'የስንዴ ነዶ' በታላቅ ድምቀት ተዋውቋል።
ተምሳሌታዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ብልፅግናን ይምረጡ !!

20/01/2026
18/01/2026
17/01/2026

St. mary help me and connect with god

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa
Addis Ababa