EthioObserver
07/12/2025
07/12/2025
ምንያህል ተሾመ ፣ አድስ ህንፃ ፣ አስራት መገርሳ ፣ አበባው ቡጣቆ we will never forget this legends
''ሰርጌ ላይ የተጨፈረው በቴዲ አፍሮ ዋልያ በሚለው ዘፈን ነበር''
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሌጀንድ ምንያህል ተሾመ ስለ ሰርጉ ገጠመኝ የተናገረው
"ሰርጌ ብሄራዊ ቡድኑ ጳጉሜ ላይ አልፎ መስከረም ላይ ነበር ፓርኪንግ ሁላ አልነበረም ሰርጉ ላይ የተጨፈረው በቴዲ አፍሮ ዋልያ በሚለው ዘፈን ነበር ስቴዲየም ያለሁ ነበር የመሰለኝ ባለቤቴ ከኋላ ሆና እኔን ተሸክመው በዋልያ ዘፈን ሲጨፍሩ ነበር::"
29/11/2025
𝐕𝐎𝐓𝐄: Is Bukayo Saka world class? 🤔
06/11/2025
Addis Ababa today
06/11/2025
የምናይበትን ነገር እናፅዳ!
| አንድ ሰውዬ በኬኒያ ሀገር ለመታከም ወደ መንግስት ሆስፒታል አቅንቶ 'X-ray' ከተነሳ በኋላ ፣ በጥሩ ጤንነት ላይ ያለች በረሮ ልቡ ውስጥ እንዳለች ይነገረዋል።
ወደ ሲንጋፖር ሄዶም መታከም እንዳለበት ይነግሩታል። ታማሚውም ወደ ሲንጋፖር ሄዶ ሲታይ ፣ የታየው በረሮ ልቡ ውስጥ ሳይሆን 'X-ray' ከሚያነሳው ማሽን ውስጥ የተገኘ መሆኑን ያስረዱታል።
ብዙ ግዜ የምናይበትን ነገር ሳናፀዳ አሊያም የምንመለከትበት መስታወት ሳነነፃ የሌላውን እድፍ ለመናገር እንሮጣለን ፣ እድፉ እኛ ምንለው ነገር ሳይሆን አስተሳሰባችን ወይም የምናይበት መነፅር ነው!
06/11/2025
የባህር በር፤ የሀገር ክብር
ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል ያልተሰበረ የሉዓላዊነት ታሪክ ያላት ሀገር ነች። ለዘመናት አባቶቻችን የዚህችን ታላቅ ምድር ክብር እና ጥቅም በመስዋዕትነት ሲጠብቁ ኖረዋል። በታሪካችን ጉልህ ስፍራ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ያላት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መብት ነው። ቀይ ባህር የውሃ አካል ብቻ አይደለም። ቀይ ባህር ኢትዮጵያን ከአለም አቀፍ ንግድ፣ ባህል እና ስልጣኔ ጋር ያስተሳሰረ መግቢያ በር ነበር።
በአክሱም ዘመነ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ በነበረው መገናኛ መስመር በዓለም እንቅስቃሴ ውስጥ ዋና ሚና ትጫወት ነበር። ይህ መዳረሻ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ውጭ ካለው አለም ጋር ያገናኝ የነበረ በመሆኑ የሀገራችንን ክብር የሚያሳይ ነበር።
ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቷ ተገልላ ከአለም እንድትርቅ ተደርጋለች።
መንግሥት ይህንን ታሪካዊ ስህተት ለማረም፣ የሰላም አማራጭ መንገድን በማስቀደም በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።
ከታሪክ አኳያ፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ መገኘቷ በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዱ የመሆን ሚናችን ማዕከላዊ ነበር። የአክሱም መንግሥት ስመ ገናና የሆነው፣ ከጥንት የአለም ስልጣኔ አውራ ከሆኑ የአለም ሀገራት ጋር ግንኙነት የገነባነው እና የአፍሪካ የሥልጣኔ ብርሃን ሆነን ያገለገልነው በዚህ መዳረሻ ነው።
ዛሬ፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ የወደብ መዳረሻ ከታሪካዊ መብት በላይ ሲሆን ኢኮኖሚያዊ አስፈላጊነቱም የላቀ ነው። በፈጣን ለውጥ ውስጥ በሚገኝ ዓለም፣ ወደ ባህር መድረስ አንድ አገር ምን ያህል ተወዳዳሪ ሊሆን እንደሚችል ይገልፃል።
በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን ፍትሃዊና ሰላማዊ መንገድ ማረጋገጥ ለሀገር ልማት፣ ለኢኮኖሚያዊ ደህንነት እና ለመጭው ትውልድ ደህንነት ቁልፍ ነው። የብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ብልፅግና ሁሉን አቀፍ፣ ሉዓላዊ እና ወደፊት የሚመለከት መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል። የረዥም ጊዜ ልማትን ማስመዝገብ ቀጠናዊ ትብብርን ማጠናከር እና የኢትዮጵያን ህጋዊ ጥቅሞች መጠበቁን ማረጋገጥ እንደሚጠይቅ ይገነዘባል። ስለዚህ የባህር በር ተጠቃሚ የሚያደርግ ጥያቄ ማንሳት አብሮ መኖር፣ መነጋገር እና ከጎረቤቶቻችን ጋር የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።
ለወጣቱ ትውልድ የወደብ ተደራሽነት ጥያቄ ከወደፊታቸው ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። የሸቀጦች ዋጋ፣ የኢንዱስትሪዎች ጥንካሬ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። በራሷ የምትተማመን፣ የበለጸገች እና ተደማጭነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ህዝባችን ከሌላው አለም ጋር ለመገናኘት የሚያስፈልጉትን የሎጂስቲክስና የኢኮኖሚ መግቢያ መንገዶችን ማረጋገጥ አለብን።
ብሔራዊ ኩራት የሚረጋገጠው በባለፉት ድሎች ብቻ ሳይሆን በመጪው የጋራ ራዕያችን ነው። ሰላማዊና ስልታዊ በሆነ መንገድ የባህር በር ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የዚያ ራዕይ አካል ነው።
06/11/2025
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቅርቡ የሚያስመርቀውን የልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ኃይል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያሠማራ አስታወቀ!
ኮማንዶው የትኛውንም ዓይነት ግዳጅ መፈፀም የሚችልና ለበርካታ ወራት ልዩ ሥልጠና እንደወሰደ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል አስታውቀዋል፡፡
“የፖሊስን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግና ተልዕኮውን የሚያሳልጥ ዘመናዊ የትጥቅ አቅም በልዩ ሁኔታ ተሟልቷል፤ ይህንን መጠቀም የሚችል የልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ኃይል አሠልጥነን ለማስመረቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ርቀት የራዲዮ ግንኙነት ሥርዓት በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚያስገባም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
02/11/2025
የታሪክ መዳረሻችን እና የሕልውና መሠረታችን ቀይ ባሕር እና ዓባይ ነው።
ባሕር ዳር: ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻ እንደኾኑ የሚነገርላቸው የዳማት እና የአክሱም ስራወ መንግሥታት ሥልጣኔያቸው የቀይ ባሕር በርን ተከትሎ የተመሠረቱ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።
የአክሱም ዘመነ መንግሥት በመሀል ሀገር በተነሳው የውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ መውደቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት እንዳይኖራት አድርጓል።
የኢትዮጵያ የኃያልነት ዘመን የነበረው የአክሱም ሥራወ መንግሥት ማክተማሚያ እና የዛጉዬ ሥራወ መንግሥት መባቻም ኤርትራ የምትባል ሀገር ፈጽሞ አልነበረችም። ኤርትራ እንደ ሀገር በጣሊያን ቅኝ ግዛት ዘመን የተከሰተች ሀገር መኾኗን የታሪክ መዛግብት አስረግጠው ይመሰክራሉ።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር ያላነስ የባሕር ክልል ነበራት። ኢትዮጵያ ከአሰብ እስከ ምጽዋ፣ ከዘይላ እሰከ ታጁራ፣ ከአዶሊስ እሰከ በርበራ ድረስ ያሉ ጥንታዊ ወደቦችን በባለቤትነት እና በበላይነት ለዘመናት ስታሥተዳድራቸው እና ስትገለገልባቸው እንደነበር ታሪክ የሚዘክረው ትውልድ የማይረሰው ሀቅ ነው።
በእርግጥም ቀይ ባሕር በኢትዮጵያ የታሪክ ገጽ ባለብዙ መልክ ነው ለማለት ያስደፍራል።
ሌፍተናንት ኮማንደር መረባ አቶምሳ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት ምሁር እና የቀድሞው የባሕር ኃይል ባልደረባ ናቸው። ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻ እና መዳረሻ እንደኾነ ተናግረዋል።
ቀይ ባሕር የሀገሪቱ ወሰን በመኾኑ ያለፉት ዘመናት ነገሥታቶችም ያሥተዳድሩት እና ይገለገሉበት እንደነበር ገልጸዋል። አጼ ካሌብ በቀይ ባሕር እጅግ የዳበር የባሕር ኃይል እንደነበራቸው ነው ያጣቀሱት።
ቀይ ባሕርን ተሻግረው የመንን እና ደቡብ አረቢያን ተቆጣጥረው ሲያሥተዳድሩት እንደነበር ነው የጠቆሙት። አጼ ዘርያዕቆብም ቢኾን ከ1434 እሰከ 1468 ዓ.ም በነበረው የንግሥ እና ዘመናቸው ቀይ ባሕርን በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው ሲያሥተዳድሩት እንደነበር ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ባላት ጥንታዊ የወደብ ታሪክ እስከ የመን፣ ፑትላንድ ሶማሌ፣ አረብ ምድር እና የኩሽ ምድር ጠረፍ ድረስ የንግድ ልውውጥ ስታደርግ የነበረው የቀይ ባሕር ዳርቻ ባለቤት ሥለነበረች ነው ብለዋል።
የቀይ ባሕር ቀጠና ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ የገባቸው እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ጣሊያን አፍሪካን ለመቀራመት በመጡ ጊዜ ግብጽ ከካይሮ እስከ ሱዳን፣ ከሶማሌ እስከ ኢትዮጵያ ሞምባሳ ድረስ ያለውን ክልል ለመቆጣጠር አቅዳ መዝመቷንም አንስተዋል።
ይህ ሁሉ ሲኾን ግን ግብጽ በራሷ አቅም ብቻ አልነበረም ለመውረር የተነሳችው። ከአውሮፖ የቀጠረቻቸውን ወታደራዊ ኃይሎችን በማዝመት ነው ብለዋል።
ጅኦፖለቲካ ማለት የአንድ አካባቢ የጅኦግራፊ፣ የስራቴጅ፣ የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚ ሁኔታዎች መስተጋብር መገለጫ እንደኾነ የገለጹት ሌፍተናንት ኮማንደር በርባ አቶሚሳ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ብሔራዊ ህልውና ከቀይ ባሕር እና ከዓባይ ሸለቆ ጅኦፖለቲካ ጋር በጥብቅ እና በጥልቅ የተቆራኘ ነው ብለዋል።
ቀይ ባሕር እና የዓባይ ሸለቆ ጠረፎች እና ወሰኖች ኢትዮጵያን ከሁሉም አህጉራት ጋር የሚያገናኙ በሮች እና ድልድዮች መኾናቸውን ነው በአጽንኦት የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ቀይ ባሕር እና ዓባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ፣ ለሀገሪቱ ዕድገት እና ጥፋትም መሠረት ናቸው ማለታቸው ይታወሳል።
ቀይ ባሕር በሲውዝ ቦይ አማካኝነት ከሜድንትራንያን ባሕር ጋር የተገናኘ እንደመኾኑ መጠን የዓለም የገቢ እና የወጪ ንግዶች እስከ ሩቅ ምሥራቅ
02/11/2025
“ አርሰናል ሊቆም የማይችል ቡድን መስሏል “ ጋርዲዮላ
| የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሊጉ መሪ አርሰናል የሚጫወትበትን መንገድ “ እጅግ አስደናቂ “ ሲሉ ገልጸዋል።
“ አርሰናል አሁን ሊቆም የማይችል ቡድን ይመስላል “ ያሉት ጋርዲዮላ “ የሚጫወቱበት መንገድ አስደናቂ ነው ምንም ግብም አይቆጠርባቸውም “ ብለዋል።
“ በመከላከል ረገድ በጣም ጠንካራ ናቸው፤ ግቦችን በተለያዩ መንገዶች እና በተለያዩ ተጨዋቾች እያስቆጠሩ ነው። “ ጋርዲዮላ
Click here to claim your Sponsored Listing.