GraceTech
23/03/2026
ቻይና የሰው ልጅን አእምሮ ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ መሣሪያ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቀደች
GraceTech
- ኒውራክል (NMT) የተባለው የቻይና ኩባንያ፣ ሳንቲም የሚያክል አነስተኛ መሣሪያ በአእምሮ ውስጥ በመቅበር የሰውነት ክፍላቸው ለሰለለ ሰዎች እንቅስቃሴን የሚመልስ ቴክኖሎጂ ፈጥሯል። ይህ መሣሪያ በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንግድ እና ለህክምና አገልግሎት እንዲውል በቻይና መንግሥት ፈቃድ አግኝቷል።
- መሣሪያው እንዴት ይሠራል? ይህ መሣሪያ በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩ የነርቭ መልዕክቶችን (Signals) በማንበብ ወደ ዲጂታል መረጃ ይቀይራቸዋል። አንድ ሰው "እጄን ላንቀሳቅስ" ብሎ ሲያስብ፣ መሣሪያው ያንን ሃሳብ ተርጉሞ ሰው ሰራሽ እጅ (Robotic arm) እንዲንቀሳቀስ ያደርጋል።
- በዋነኝነት የአከርካሪ አጥንት ጉዳት ለደረሰባቸው፣ ለፓራላይዝስ (ሽባነት) እና ለተለያዩ የአእምሮ ሕመሞች ተጠቂዎች እንቅስቃሴን ለመመለስና የኑሮ ጥራታቸውን ለማሻሻል ይረዳል።
ከሌሎች የሚለየው በምን ይሆን? እንደ ኤለን ማስኩ ኒውራሊንክ (Neuralink) ሁሉ፣ ይህ መሣሪያ ሽቦ አልባ (Wireless) ነው። ነገር ግን የቻይናው መሣሪያ በአእምሮ ህብረ ህዋሳት ውስጥ ዘልቆ ከመግባት ይልቅ በአእምሮው የላይኛው ክፍል ላይ ስለሚቀመጥ፣ የጉዳት ስጋትን ይቀንሳል ተብሏል።
- እስካሁን ድረስ እንዲህ ያሉ መሣሪያዎች ለምርምር ብቻ እንጂ ለሽያጭ አይቀርቡም ነበር። አሁን ግን ዶክተሮች እንደ ልብ መቆጣጠሪያ (Pacemaker) ሁሉ ይህንንም መሣሪያ ለታካሚዎች ማዘዝ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።
- ወደፊት ይህ ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴን ከመመለስ ባለፈ፣ የማየትና የመስማት ችግርን ለመፍታት፣ እንዲሁም የሰውን ልጅ የማስታወስ ችሎታ ለማሳደግ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ተመራማሪዎች ገልጸዋል።
GraceTech
23/03/2026
በአቅራቢያችን የሚገኘው ጋላክሲ ‘መለወጥ’ በመጀመሩ ስለ ጠፈር ያለንን ግንዛቤ እየቀየረ ነው
GraceTech
ተመራማሪዎች ለምድራችን ቅርብ የሆነው SMC የተባለው ጋላክሲ ከሌላ ትልቅ ጋላክሲ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት ቅርጹና አወቃቀሩ ሙሉ በሙሉ እየተቀየረ መሆኑን ደርሰውበታል።
⭕️ ከጥቂት መቶ ሚሊዮን ዓመታት በፊት በደረሰ ግጭት ምክንያት በጋላክሲው ውስጥ ያሉ ከዋክብትና ጋዞች ተበታትነዋል።
⭕️ ይህ ጋላክሲ እንደ ሌሎች ጋላክሲዎች መደበኛ ስርአት የሌለው መሆኑ ተረጋግጧል።
አዲስ ግንዛቤ፦ ይህ ግኝት ሳይንቲስቶች ስለ ጠፈርና ስለ ጋላክሲዎች እድገት የነበራቸውን የቀድሞ እይታ እንዲቀይሩ ያስገድዳቸዋል።
GraceTech
Click here to claim your Sponsored Listing.