Kaleab Teshome

Kaleab Teshome

Share

Photos from Kaleab Teshome's post 23/01/2024

ገነነ ሲያነብም ሆነ ሲመራመር አይደክመውም-ቢደክመው እንኳን ድካሙን ይረሳል፡፡ ገነነ ታሪክን ሲያቀርብ ማጣፈጡን ያውቅበታል፡፡ ለ45 ደቂቃ በዩኒቨርሲቲ የታሪክ ክፍለ ጊዜ ላይ ከመታደም የ12 ደቂቃዋ የገነነ ምጥን የታሪክ ጨዋታ ወደ አእምሮ ኩልል ብላ ትገባለች፡፡ ይህንን ለማድረግ ትልቅ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ማንበብን ይጠይቃል፡፡ ጥልቅ ምርምር ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ነገሮችን ወይም ያለፉ ታሪኮችን በሚገባ አዋዝቶ ማቅረብን ይጠይቃል፡፡ ማዋዛት የገነነ ልዩ ክህሎት በአድማጭ ፤ አንባቢ በተመልካች የተመሰከረለት ነው፡፡ገነነ ይጽፋል ያነባል የእግር ኳስ ቴክኒክን ያስተዋውቃል፡፡ ገነነ መጽሀፎቹን ሲጽፍ ከበቂ ጥናት ጋር ነው፡፡ ደግሞም መጽሀፎች ጥሩ የሽያጭ ሰንጠረዥ ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ ገነነ መኩሪያ በ 1970ዎቹ መጨረሻና በ 1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሀገራችን ብቅ ካሉ በሳል የሚድያ ሰዎች አንዱ ነው፡፡

©️ ተወዳጅ ሚዲያ (በእዝራ እጅጉ)

ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሀፍት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በሞት መለየት አስደንጋጭ መረጃ ነው። ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለው!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa
1000