Berhanu.Bro
04/06/2026
#ወንድሜ!
ወልደህ ባታውቅ ነው እንጂ ልጅን ወልዶ ማሳደግ፣ ለቁምነገር ማብቃት እጅግ ከባድ ነዉ። በየእድሜዉ እርከን ብዙ ጭንቀት አለዉ:- ፅንሱ ይፀና ይሆን? በሰላም ይወለድ ይሆን? ጤናማ ሆኖ ይወለድ ይሆን? ጡት ይጠባ ይሆን? በሆነ በሽታ ይቀሰፍ ይሆን? ከእጅ ወድቆ ይቀጭ ይሆን? ሲጫወት አደጋ ይደርስበት ይሆን? በሌላ ሰዉ እጅ ይበደል ይሆን? ለእድገቱ በቂ ነገር ያገኝ ይሆን? ተምሮ ይወጣ ይሆን? በሰላም ወጥቶ ይመለስ ይሆን? ፈጣሪዉን አዉቆ ይፈራ ይሆን? ወዘተ.። አንተም ተወልደህ ያደግከዉ ወላጆችህ በዚህ አይነት ጭንቀት ዉስጥ አልፈዉ ነዉ።
ግን በስተመጨረሻ እነሱ ያላሰቡት አንድ ጭንቀት እዉን ሆነ:- በጭንቅ ወልደዉ በመከራ ያሳደጉት ልጃቸዉ በዋዛ ሌሎች ወላጆች በጭንቅ ወልደዉ በመከራ ያሳደጓቸውን ልጆች ያለምንም ርኅራኄ በጥይት የሚቆላቸዉ ሆኖ አረፈ። ከልጆችም አልፎ ወላጆችንም ጭምር የማይምር ጭራቅ ወጣዉ። ለወላጆችህ በዚህ መልክ ህመም፣ ለወገንህ ቁስል፣ ለሀገርህ ደግሞ ኪሳራ ለመሆን በቃህ። ከፈጠረህ አምላክ ይልቅ የተረገመዉ ዲያብሎስ ከበረ። ይኸዉ ነዉ ያንተ ታሪክ፣ እራስህ ምዕራፉን ካልዘጋህ ቃልህ ሆኖ ለዘለዓለም ይቀመጣል።
ሰላም ይሁን! 🥺🥺
01/06/2026
በፀጋ መቀበሉንስ እኛም እንደርስዎ ነን። በዚህ ረገድ ምንም ልየነት የለም። እንኳንስ የዛሬውን ምርጫ የህይወት እርግጫንም በፀጋ ተቀብለናል። ይመቸን!
እኛ ሰፈር መብራት ጠፍቷል። ቶሎ መልሱ። ካልሆነ ነገ የካርዱ ቀለም ይቀየራል። 🧐
30/05/2026
የጋና ፓርላማ ግብረሰዶማዊነትና ተግባራቱን የሚያስተዋውቅ የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ #ወንጀል የሚያደርግ ሕግ አጸደቀ።
በግብረሰዶማዊነት ተግባራት ውስጥ ተሳትፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በሦስት ዓመት እስራት እንደሚቀጣ ሕጉ ይደነግጋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዚህ የተከለከለ ተግባር ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎችን የሚያውቅ ግለሰብ ለፖሊስ የመጠቆም ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል።
ማንኛውም የግብረሰዶማዊነት እንቅስቃሴ የሚደግፍ ወይም የሚያግዝ አካልም እስር እንደሚጠብቀው ተመላክቷል።
በሕጉ ላይ የግብረሰዶማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ሰዎችን የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የሕግ፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የጤና ባለሙያዎች እንዳይካተቱ ተደርገዋል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ባለፈው ዓመት ወደ ሥልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ የሃይማኖት አባቶች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ ያሉ ሕጎችን እንዲያጠብቁ ጫና ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ሕጉን ያረቀቁት መጋቢ ጆን ንቲም ፎርዦር ፥ " ሕጉ የጋና ቤተሰብ እና ባህላዊ እሴቶች ይጠብቃል። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ለመከላከል የበለጠ ጠንካራ ፣ የበለጠ አካታች፣ የበለጠ ጥብቅ ያደርጋል " ብለዋል።
ጋና እ.አ.አ. በ2024 ተመሳሳይ ህግ ብታወጣም በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት አኩፎ አዶ ሳያጸድቁት በመቅረታቸው ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል።
ፕሬዚዳንት ማሃማ ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ ሕጉ እንዲጸድቅ እንደሚፈልጉ ተናግረው " ሁለት ጾታዎች ወንድ እና ሴት ብቻ በሚለው መርህ እና እሴት አምናለሁ። እና ጋብቻ በወንድ እና በሴት መካከል ብቻ ነው " ብለው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።
ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም
Tikvah-Ethiopia
29/05/2026
#ፍልፍሎች
ቀድሞዉኑ "እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል!" ሲሉ የኖሩ ሀሰተኛ ፓስተሮች የፈለፈሏቸዉ ሀሰተኛ ነቢያትና "እኛ ካልገደልንላችሁ ነፃ አትወጡም!" ሲሉ የኖሩት የፖለቲካ አለሌዎች የፈለፈሏቸዉ ታጋይ ሽፍቶች ዛሬ ላይ እራሳቸዉን የባህሪ አባቶቻቸውን እንኳ የማይሰሙ ሆነዉ ከከተማ እስከ እስከ ገጠር ቁጥቋጦ ስርቻ ድረስ ህዝቡን በመጋጥ ላይ ይገኛሉ። በነዚህ ፍልፍሎች የሚፈለፈሉት ቀጣይ የፍልፍሎች ትዉልድ ደግሞ ምን ያደርጉን ይሆን?
🤔🤔🤔🤨🤨😏😏😏
Life after 50
ለራስ ማስታወሻ
22/05/2026
በአናቱ ምግብ
የምግቡ አይነት:- ማህበራዊ
የምግቡ ዋጋ:- 170 ብር
የምግቡ ይዘት:- መዓት ሩዝ፣ ነፍ ድንች (አልጫና ቀይ)፣ እንጀራው የበዛ የተፈጨ ሥጋ ፍርፍር፣ ከሸኾና እና ከቀንድ አካባቢ የተገኘ የሚመስል ሥጋ ጣል ጣል የተደረገበት ቀይ ቁሌት።
የምግቡ የሙቀት መጠን:- ከዜሮ በታች
የምግቡ ጣዕም:- ሀገር በቀል
ምግቡ የሚሸጥበት ቦታ:- ለደህንነት ሲባል የማይገለጽ፣ የግድ ከሆነ ግን በዉስጥ መስመር
😋
22/05/2026
"ሁላችን ራሳችንን ከሌሎች ይበልጥ መዉደዳችን ለሀሳባቸው ግን ከራሳችን ሀሳብ በላይ ዋጋ መስጠታችን ሁሌም እንደገረመኝ ነዉ" ብሏል ማርከስ ኦሪሊየስ። እናንተስ?
ድሮ "አብዮት ልጆቿን በላች!" ይባል ነበር። አሁን ደግሞ "ብሔርተኝነት እናቷን ባላች!" ያስብላል። የሚገርመው ዋናዎቹ የብሔራቸዉ "ነፃ አዉጪ" ልጆች የሆኑላቸዉ (የሆኑባቸዉ) እናቶች እነዚሁ ሦስቱ ናቸዉ። በዚህ መልኩ ብዙ እናቶች በራሳቸው ልጆች ከመብላቸዉ፣ ከመኖሪያቸዉ፣ ከሠላማቸዉ፣ ከማህበራዊ ድርና ማጋቸዉ፣ ከክብራቸዉ፣ ከእድላቸዉ፣ እና ከተስፋቸዉም ጭምር "ነፃ" ወጥተዋል፣ አልያም በመዉጣት ላይ ናቸዉ። 🥺😥
Click here to claim your Sponsored Listing.