Seblina Foreign Employment Agent

Seblina Foreign Employment Agent

Share

19/06/2022

It started ...

21/01/2021

ℹ️''የአረብ ሀገር ሴቶች ሰርተው እንጅ
አፋቼውን ከፍተው አይደለም
የሚኖሩት!!

ℹ️ ✅የአረብ ሀገር ሴቶች እንደሻማ
እየቀለጡ ለሌላዉ ሰዉ ብርሀን ይሆናሉ

ℹ️✅የሚያደናቅፈውን እቃ ቀና
የማያደርግ ሁላ እየተነሳ አገርና
ቤተሰቧን ያቆመችውን የአረብ አገር
ሴት መሳደቡ ይገርማል።

✅እናንተ የአረብ ሀገር ልጆች ይልቅም
እናንተ የሀገር ዋልታዎች ናችሁ። ❤
🌹✅የሀገር ባለዉለታወች ናችሁ።
🌹✅የወንድም እህት በለዉለታዎች ናችሁ።
🌹✅የቤተ ዘመድ ዋልታዎች ናችሁ።
🌹✅የአረብ ሀገር ልጆች በቤተሰቦቻቸው ላይ
እና በሀገራቸው ላይ የተንሰራፋውን ድህነት
ያርበደበዱ ጀግኖች ናቸው።

ℹ️ ክብር ይገባቸዋል 👈🙏
ሸርርርርርር

02/10/2020

🧿✅ እያለቀስክ እንደማትመልሰው ከገባህ ስቀህ ሸኘው!

ወዳጄ ስደት በስራ ወጥሮህ /ሽ መኖር ደክሞህ/ሽ ቤተሰብ ናፍቆህ/ሽ ፈገግታ ከፊትህ ጠፍቶ ደስታ እርቆህ ይሆናል፡፡ ወዳጄ ይህንን እውነት እፅፍልሀለው፡፡ የአንድ ዛፍ ታሪክ ልንገርህ! በአንድ ጥቅጠቅ ባለ ጫካ ውስጥ አንድ ቁመናው የማያምር ጠማማ ዛፍ ነበር (ልብ በሉ የማያምር ነው ያልኩት ) ጠማማ ሆኖ በመፈጠሩ ሁሌም አምላኩን ያማርር ነበር....ታዲያ አንድ ቀን አንድ ዛፍ ቆራጭ ብዙ ቁመናቸው ያማሩ ዛፎችን ከቆረጠ በኋላ እዚህ ዛፍ ጋር ሲደርስ ግን ይህንን ዛፍ ብቆርጠው ያን ያህል ገቢ አላገኝበትም ብሎ አስቦ ጥሎት ሄደ ዛፉም" ጌታ ሆይ እንዲህ ጠማማ አድርገህ ስለፈጠርከኝ አመሰግናለሁ" አለ።

አየህ ወዳጄ በርግጥ በባእድ ሀገር መኖር በጣም ይከብዳል ልክ ዛፉ ጠማማ መሆኑ ከብዶት እንደነበረ ማለት ነው :: ስደቱ ነገ አልፎ ዛፉ ጠማማነቱን እንዳመሠገነ አንተም አንቺም የስኬትሽ ጫፍ
ስትደርሺ ታመሠግኛለሽ

ልብ እንበል!!
✅ ጉንደን ካስበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች፤ትነሳለች አንተ ከጉንዳን ትበልጣለህ!!

✅ ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች:: እህቴ ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል.......

✅ አስቢ አንተም አስብ
ያልወረወረ ----- አይመታም
ያላባረረ ------- አይዝም
ያልጠየቀ ------- መልስ አያገኝም
ቀስት ወደፊት ለመወርወር መጀመሪያ ወደ ኀላ መሳብ አለበት አሁን አንቺም አንተም ይህንን መልእክት እያነበብክ ያለኸው እንደቀስቱ በህይወት ጎዳና ወደኀላ አየተሳብሽ ነው ወደፊት ስትወረወሪ ማንም አይችልሽም!!

ኢቺን አባባል አትርሳት (ፋንዲሻ እንዴት አማርሽ ቢሏት እሳቱን ስለቻልኩት) ያለችውን በህይወት መስመር ስኬትን ለማግኘት የግድ መከራውን ማለፍ አለብን!! ደግሞስ ተጨንቀሽ ተበሳጭተህ የምትቀይሪው ነገር አለ?? የለም ! ስለዚህ አንዳንዴ እያለቀስሽ የማትመልሺውን ነገር እየሳቅሽ ማጣትም ብልህነት ነው !!

ሌላውም እንዲማር ሼር ያድርጉ
ምርጥ መጣጥፎች

Want your business to be the top-listed Shop in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
00