How to Get Knowledge?

How to  Get Knowledge?

Share

10/02/2025
10/02/2025

የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ፡-

ምንም ነገር ብትከስር መጨረሻ ላይ የምትከፍለው በጊዜህ ነው፡፡ የስልጣኔ ሁሉ ስልጣኔ ጊዜን በተገቢው መንገድ የመጠቀም ስልጣኔ ነው፡፡ በሕይወትህ እቅድ የሞላው ኑሮ ለመኖርም ሆነ ማንኛውንም ተግባርህን በወቅቱና በተዋጣለት ሁኔታ ለማከናወን ከፈለክ የጊዜ አጠቃቀምን መሰረታዊ እውነታዎች ከዚህ መጽሐፍ የማግኘት ምርጫ አለህ፡፡

ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . .

የጊዜ ትርጉምና አስፈላጊነት

“ጊዜ ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነው” - William Penn

• የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀው፤

• የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ካለወሩ የተወለደን ሕጻን የወለደችን ሴት ጠይቃት፤

• የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀው፤

• የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ውጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀው፤

• የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸው፤

• የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው፤

• የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰው ጠይቀው፤

• የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው፡፡ - Unknown Source

ሰው ለምንም ነገር የሚከፍለው በገንዘብ ሳይሆን በጊዜ ነው፡፡ ይህ እውነት ቀድሞውኑ ገንዘቡን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣው “ጊዜ” የተባለው ነገር የመሆኑን እውነታ ጠቋሚ ነው፡፡ ጊዜ በአለም ላይ ውድ ከተባሉ ነገሮች ቀደምተኛውን ስፍራ የያዘ ጉዳይ ነው፡፡ ጊዜውን ያባከነ ሰው ሕይወቱን ያባከነ ሰው ነው፡፡

ጊዜን በአግባቡ ባለመጠቀም ምክንያት ሰዎች ገንዘብን ይከስራሉ፣ ወዳጅነትን ያበላሻሉ፣ ከዚያም አልፎ፣ አንዳንድ ጊዜ፣ በሞትና በሕይወት መካከል የሚወስን ገጠመኝ ውስጥ ራሳቸውን ይጨምራሉ፡፡

የጊዜ አጠቃቀማችን ሁኔታ ተጽእኖው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ጊዜ አንድና አንድ በመሆኑ ነው - ጊዜ አንዴ ካለፈ በፍጹም ተመልሶ አይመጣም፡፡ ጊዜ በብዙ እድሎች የተሞላ ሃብት ነው፡፡ ጊዜ እንዲሁ ሲያልፍና ሲባክን ከዚያው ጋር አስገራሚ እድሎችና ሌሎች ውብ ነገሮች አብረው ያልፋሉ፡፡

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Tuesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00