Eyob zerihun

Eyob zerihun

Share

Photos from Eyob zerihun's post 16/01/2025

❤️ እናትዋ ጎንደር
📸Fanos Pictures

Photos from Eyob zerihun's post 16/01/2025

ስቻለው ፈጠነ - ታሪክን ያዜመና ያቀነቀነ ባለሙያ!
Hoheteberhan Getu እንደፃፈው እስከመጨረሻው አንብቡት ታተርፋላችሁ እና👇👇👇
| ዘፈኑ ሲሰማ ስለ ጎንደር የዘፈነ ይመስላል።በእርግጥም ስለ ጎንደር ዘፍኗል። አሌ አይባልም።አንድ ጊዜም ብቻ ሳይሆን ደጋግሞ አቀንቅኗል። እንዲያውም በአደባባይ ትንሽ እንቦጭቀውና የእትብት መካነ-ልደቱን ቻግኒን በጎንደር ፍቅር ሳይቀይራት ይቀራል? ፍቅር እውር ነው ተብሎ ዬለ? የአስቻለውን የጎንደር ገጠመኝ ከራሱ በቀርስ ማን ያውቃል? ግን እኮ ለሀሜት ፈጥሮን እንጅ አስቻለው ባለፈው ባወጣው ባለ-አስራ ሶስት ትራክ አልበሙ ያላቀነቀለት ዬት አለ? ከእናትዋ ጎንደር እስከ እመት ሸዋ፣ እንገር ወሎ፣ ካሲናው ጎጃም... ኧረ ስንቱ!
"አሞራው -ካሞራ" የሚለው ነጠላ ዜማው ሲደመጥ ግን ታሪክ ነው ያዜመውና ያቀነቀነው። የዘፈኑ ማጠንጠኛና ባለቤቱ ደግሞ ራስ አሞራው ውብነህ ተሰማ የስሜኑ አርበኛ ናቸው። ባለቤታቸው ዘነበች መሸሻንም፣
እናትዋ ብልሽ-እህትዋ ብልሽ፣
መች ደረስኩልሽ፣
እናትዋ ጎንደር እጅ የዘረጋሽው፣
ዘነበች መሸሻን ወልዳ የሳመችው። እያለ አውስቷቸዋል።
ይህ የጥበብ ውጤት በሰርቃራቃ ድምፅ እየተንቆረቆረ ወደ አድማጭ ጆሮ ሲደርስ አድማጭ ደግሞ የግድ ራስ አሞራው ውብነህ ማናቸው? ትውልዳቸውስ ወዴት ነው ሲባል ከያኒው ወገራን፣ አርማጭሆን፣ ጎንደርን ማሰስ ግድ ሆነበት። እናም ጎንደርን እንደ ተለመደው ተቀኘባት። በራስ አሞራው ውብነህ ተሰማ አሳቦ በጎንደር ፍቅር የተነደፈው አስቻለው ጎንደርን ዙሪያ ገባዋን ዳሷታል። ራስ አሞራው ፋሽሽት ኢጣልያን ያርበደበዱባቸውን ጋራ-ሸንተረሮች፣ የዓውደ ውጊያ ሥፍራዎች በጥበቡ ጎብኝቶ አድማጭንም አስጎብኝቷል።
አስቻለው ታሪክን በጥበብ በሚገባ ገልጾታል። የተቋጠሩት ስንኞች ለቤት መሙያ የተደረደሩ አይደሉም። ለፈረንካ መልቀሚያ ሲባል የይድረስ-የይድረስ ሥራ አለመሆናቸውን ስንኞቹ ራሳቸው አፍ አውጥተው በራሴያቸው ቅላፄ እያዋዙ ይናገራሉ። በታሪክ የታጨቁ ናቸው። የታሪክ መፃሕፍትን ያስነብባሉ። ዜና መዋዕልን ይናገራሉ። ገድላተ ጀግኖቻችንን ያወሳሉ። ትናንትን አልረሱም። አገርኛ የቋንቋ አገላለጽ ዘይቤያቸው በክራሩ ሲያንቆረቁራቸው የደም ሥር ሁሉ ያቆማሉ። በደስታ ሲቃ ያስፈነድቃሉ። ሲያስፈልጋቸው ያስተክዛሉ። ሆዴ-ቡቡ የሆነውንም ያስለቅሳሉ። ታሪክን፣ ቋንቋን፣ እሴትን፣ ባሕልን፣ ልማዳዊ ወግን አጣምረው በጥበብ ተከሽነው ቀርበዋል። አስቻለው ለየት ያለ አቀራረብ ይዞ መጥቷል። ሁሉም ሲሰሙት አይጠገብም። በቃ ሙዚቃን ሕይወት ዘርቶበታል። በሀገር-በቀል ዜማና ድርሰት አስውቦታል።
"አሞራው ካሞራው" በሚለው በሰሞነኛው ነጠላ ዜማው ደግሞ ፋሽሽት ኢጣልያን በማርበድበድ በጀግንነት የታወቁትን የነፃነት አርበኛ ራስ አሞራው ውብነህን ገልጿቸዋል ሳይሆን ብቻ ተቀኝቶላቸዋል። በጀግንነት ሕያው ታሪካቸው "ራስ" የሚል ከፍተኛ መንግሥታዊ የሹመት ማዕረግ ሕዝብ ደግሞ "አሞራው" ብሎ ሰይሟቸዋል። በሕዝብ ልብ ውስጥ ገብቶ የሕዝብ የሹመት ማዕረግ ማግኘትና መመረጥ ጊዜ የማይሽረው ማዕረግ ነው።
ፋሽሽት ኢጣልያን ባርበደበዱበት ወቅት ሕዝብ ጀግንነታቸውን ተመልክቶ፣
የሰማውን እንጃ ሮም ገሰገሰ፣
የጦሩ መድኃኒት አሞራው ደረሰ።
ያየህም ተናገር-የሰማህም አውራ፣
ተገናኝቶ ዋለ አሞራው ካሞራ።
ጎንደር ከግንቡ ላይ ያለው ነጭ አምበጣ፣
ከምን ሊገባ ነው አሞራው ሲመጣ።
እያለ ገድለ ጀግንነታቸውን ገልጾላቸዋል። አስቻለውም ከዚህ ታሪክ ተነስቶ ሰሞነኛውን ነጠላ ዜማውን "አሞራው-ካሞራ" ሲል ሰይሞታል። እንደ አሞራ በአየር መብረር የሚቀራቸው፤ በእግረኛ ተዋጊነታቸውም ለምድር ያስቸገሩ፣ ጠላትን ያርበደበዱ ተወርዋሪ ተዋጊ አርበኛ ስለነበሩ፣ አሞራው ካሞራ ብለው ከንስር አሞራ ጋር መድበዋቸዋል። እንደ ታሪክ ጸሐፊ አስቻለው ታሪካችንን እያቀነቀነ በአጥንታችንና በሥጋ እንዲዋኃድ አድርጓልና ምስጋናችን ይድረሰው።
ግን አንድ ጥያቄን ያጭራል። በታሪክ ተለብደው፣ በሰምና ወርቅ ቅኔ ቅኝት ተሞልተው፣ በውስጠ-ወይራና በሰም-ለበስ አገላለጽ ተቋጥረው የቀረቡ ስንኞችን ስንቶቻችን እንረዳቸዋለን? ብቻ አስቻለው በጥበብ ኢትዮጵያን ገልጿታል። በክራሩ አዚሞላታል። የክራር ቅኝት ቃኞቹ እጆችህ ይባረኩ። ድምፅሕም እንደተስረቀረቀ በማስደመም ይቀጥል።
አስቻለው ክራሩን ይዞ ቀድሞውኑ የመነነው፤
ለካስ ይህን ሁሉ እምቅ ታሪክ በክራሩ ሊያስቃኘን ነው።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa