Matewos Tema
የሚገርም ገጠመኝ
በዛሬ ውሎ የገጠመኝ ነገር የሚገርም ነበር፣ ከስራ ወዬ ስመለስ ሽሮ ሜዳ አከባቢ አንድ ጉዳይ ስለነበረኝ ሄጄ ነበር ሆኖም አንድ የዘመኑ አዲስ መኪና በሆነ ጊቢ ውስጥ ቆሞ ነበር ነገር ግን ሞተር አልጠፋም ደግሞም የመኪናው መስተዋት ክፍት ጥሎ የሚሄድ የመኪና ባለቤት ገጥሞን የጥበቃ ሰራተኛው ተጨንቆ ስንቆራጠጥ አገኘውና ምነው ብዬ ስጠይቀው አንድ ባለመኪና ሞተሩን አላጠፋም እንደገና መስተዋቱ ክፍት ነው አለኝ፡፡
ሞተሩ ስንተከተክ በጣም ቆይቷል አለኝ፣ ሆኖም የመኪናውን መስታዎት በካርቶን ሸፍኖት ዝናብ እንዳይገባ ስከለክልለት ተገርሜ፣ ለማንኛውም ሞተር እናጥፋለት ብዬው ክፍት በሆነው መስተዋት በኩል በር እንደምንምን ብለን በመክፈት የመኪና ሞተር እንዲጠፋ አድርገን እና መስኮቶቹ እንዲዘጋ በማድረግ የጥበቃውን ልብ አሳረፍንለት፡፡ መኪና እንደልብ በሚሰረቅበት ከተማ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ መግጠሙ ይገርማል፡፡ በእውነት የጥበቃውን ሰራተኛ እግዚአብሔር ይባርከው፡፡
መልካም ምሽት
15/08/2024
በህይወትህ ፈጽሞ መርሳት የሌለባቸው ቁም ነገሮች!!!
1. ሌሎችን ሳትጎዳ ማደግ እንደምትችል ሁሌም አስብ፣
2. ሌሎችን ሳትጫን ህልምህ ሊፈፀም እንደሚችል አስታውስ፣
3. በስልጣን ላይ አንተ ለመቀጠል ማንም ሰው መጎዳት እንደሌለበት ሁልጊዜ አስተውል፣
4. ፈገግታህ እንዲጸና ማንም ሰው ሊያፍር ወይም ሊሸማቀቅ እንደማይገባ ሁሌም አትዘንጋ፣
5. ሌሎች እንደተነሱ አንተም መነሳት እንደምትችል ሁሌም አትርሳ፣
6. በሌሎች ስቃይ እርካታ ማግኘት በፍጹም እውነተኛ ደስታ እንደማያመጣ እወቅ፣
7. የሌሎችን ደስታ፣ በጎ ፈቃድና ተስፋ የምታበላሽ ሳትሆን የሌሎችን ልብ የሚያበራ ጥሩ ሻማ ሁን
8. በሌላው ሰው እንባ ፈጽሞ አትደሰት፣ ሥልጣንህን ሌሎችን ለመቅጣት ፈጽሞ አትጠቀምበት ሕይወት አስተማማኝ አይደለም ነገን ፈጽሞ አታውቅምና፣ የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ እንደሚመጣ ፈጽሞ ማወቅ ስለማትችል በዛሬው ቀን ያለህን ቦታ ሌሎችን ለማበሳጨት እና ለመጉዳት አትጠቀምበት።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
Addis Ababa
24254