Ethio Green Mobility Week

Ethio Green Mobility Week

Share

24/11/2025

2ኛው የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ ሳምንት ከታህሳስ 9 እስከ 12 ይካሄዳል
+++++++++++++++++

| 2ኛው የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ ሳምንት ከታህሳስ 9 እስከ 12 እንደሚካሄድ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ዝግጅቱን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤ ግሪን ሞቢሊቱ ሳምንቱ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ የደረሰችበትን ደረጃ የምታሳይበት ነው።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ትገኛለች፤ በዚህ ሂደት የትራንስፖርት ዘርፉ የራሱን ሚና እንዲወጣ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከትራንስፖርት ዘርፉ የሚወጣውን በካይ ጋዝ ለመቀነስና በኤሌክትሪክ ብቻ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በብዛት ለማስገባት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮ ግሪን ሞቢሊት ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

በኤግዚቢሽኑ የኤሌክትሪክ መኪና አስመጪዎች፣ የኤሌክትሪክ መኪና ተሸከርካሪ መለዋወጫ አቅራቢዎች፣ በጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የሚመረቱና ከውጭ የሚያስገቡ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

በኤግዚቢሽኑ አምራቾች ከፖሊሲ አውጭዎች ጋር ዘርፉን ለማዘመንና ያለውን ማነቆ ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በዝግጅቱ ከ100 በላይ በአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም አቀፍና ሀገር በቀል ተቋማት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

በክብረአብ በላቸው
++++++++++++++++++
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #አርንጓዴትራንስፖርት

Photos from Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia's post 24/11/2025
Want your business to be the top-listed Event/venue in Dubai?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Telephone

Address


Hilton Hotel, # 335,336
Dubai