Tricks & Tech Hacks
17/05/2019
የBitCoin Mining ማጭበርበር
ሰላም የፔጃችን ተከታዮች ዛሬ ስለ BitCoin Mining የማጭበርበሪያ ስልቶችና በሃገራችንም እየተፈፀሙ ስለሚገኙ የማታለል ስራዎች እንዲሁም ራሳችንን ከዚህ ተጋላጭነት እንዴት እንደምንጠብቅ እናወራለን፡፡
ወደፊት ዘርዘር ያለ ፅሁፍ በCryptocurrency ዙርያ አቀርባለሁ፡፡
እንደሚታወቀዉ BitCoin Cryptocurrency ዲጅታል የመገበያያ ገንዘብ አንዱ ሲሆን BlockChain በሚባል ቴክኖሎጂ ይተዳደራል፡፡
አሰራሩም ምንም አይነት ባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም ሳያስፈልግ ማንኛዉንም አይነት ግብይትም ሆነ የገንዘብ(Bitcoin) ዝዉዉር መፈፀም ያስችላል፡፡
እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ መጠየቅ ግድ ነዉ፡፡ ምንም አይነት የፋይናንስና ተቋም ወይም ባንክ ከሌለ ማን ይቆጣጠረዋል ግብይቱ መፈፀሙንስ ማን ያረጋግጣል?
ጥሩ ከላይ እንደገለፅኩት Blockchain የተባለዉን ቴክኖሎጂ ይህን ይፈፅማል፡፡
ታድያ በዚህ መሀል ግብይቱ በትክክል መፈፀሙን የሚያረጋግጡ ማይነርስ(Minors) የሚባሉ አካላት አሉ፡፡
ማይኒንግ(Mining) ማለት ዲጅታል ገንዘቡ(BitCoin) መተላለፉን በማረጋገጥ ብቻ ጉርሻ የሚገኝበት ቢዝነስ ነዉ፡፡
ታድያ ለዚህ እጅግ ከፍተኛ የኮምፒውተር ፕሮሰሲንግ አቅምና ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ቢዝነስ ዉስጥ ያሉ እጅግ ትርፋማ የሆኑ ብዙ ኩባንያዎች በቻይና ሃገር ይገኛሉ፡፡ ምክንያቱ ደግም ቻይና የኤሌክትሪክ ዎጋ ርካሽ ስለሆነ ነዉ፡፡
ይህንን ካልን የBitCoin Mining ማጭበርበር ስንል ምን ማለት ማለታችን ነዉ?
ሁለት አይነት ዋናዋና የማጭበርበሪያ ስልቶች አሉ፡
1. Ponzi scheme(ፖንዚ ስኪም)
2. Pyramid scheme(ፒራሚድ ስኪም)
Ponzi scheme(ፖንዚ ስኪም):-
- ይህ የማጭበርበሪያ ስልት በሌሉ የማይኒንግ(Mining) ድርጅቶች ስም፡ እኛ የማይነር ቢዝነስ ሰዎች ነን በሚል ገንዘብ አምጡ ኢንቨስት አድርጉ በማለት ገንዘብ መሰብሰብ የማጭበርበር ስልት ነዉ፡፡
2. Pyramid scheme(ፒራሚድ ስኪም)
- ይህ የማጭበርበሪያ ስልት ነዉ እንግዲህ በሀገራችንና ሌሎችም ሀገሮች እየተስፋፋ የሚገኘዉ፡፡ የዚህ ስልት ዋናዉ መገለጫ ገንዘብ አምጡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ይህን ያህል ፐርሰንት በየጊዜዉ ታተርፋላችሁ፡ ሌላ ሰዉ ባመጣችሁ ቁጥር የትርፍ ፐርሰንታችሁ ይጨምራም በማለት ሰዉን በማነሳሳት የሚደረግ ማጭበርበር ነዉ፡፡
አብዛኛዎቹ በሆቴሎች ስብሰባና ኮንፈረንስ በመጥራት በመስበክ ገንዘባችሁን እንድትሰጡ የማግባባት ስራ ይሰራሉ፡፡ እናንተም ያንን የተጋነነ ትርፍ እዉነት ነዉ ብላችዉ ስትሰጡና ገንዘብ አየሰራችሁ ሲመስላችሁ ነገር ግን እነሱ ጥቂት ተመላሽ እየሰጧችሁ ገንዘባችሁን በሙሉ ለግላቸዉ ያደርጉታል ማለት ነዉ፡፡
ተጠንቀቁ ስለ Cryptocurrency በቂ ዕዉቀት ሳይኖራችሁ ስለ ማይኒንግ አሰራር ሳታዉቁ ገንዘባችሁን እንዳትበሉ !
ከዚህም ሌላ ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ ተጨማሪ መረጃዎችን ማንበብ ትችላላችሁ፡፡
ማንኛዉንም ጥያቄና አስተያየት
ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት ሳተላይት ታመጥቃለች
==============================
ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሚሆነውን
የምድር አሰሳ ተልእኮ ያላትን ሳተላይት በሚቀጥለው መስከረም ታመጥቃለች፡፡
ሳተላይቷም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ካሉ ሳተላይት ካመጠቁ ጥቂት ሃገራት
መካከል አንዷ በመሆን እንደምትካተት ይጠበቃል፡፡
ሳተላይቷ በፈረንጆቹ 2019 መስከረም ወር ላይ በቻይና አማካኝነት ወደ ህዋ
ለማምጠቅ እቅድ ተይዟል፡፡
ሆኖም የቁጥጥር እና ማዘዣ ጣቢያው በኢትዮጵያ እንደሆነ የኢትዮጵያ የህዋ
ሳይንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ መናገራቸውን
ዘኢስትአፍሪካን ኒውስፔፐር ዘግቧል፡፡
በጣም ወሳኝ የሚባሉ የዲዛይን ምእራፎች በኢትዮጵያዊያን መከናወኑን
የገለጹት ዋና ዳሬክተሩ በፕሮጀክቱ 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ የስነ-ፈለክ
ተመራማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ጠቁመዋል፡፡
የቻይና መንግስት ስልጠናዎችንእና ለዲዛይን 6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር
መስጠቱን ዶ/ር ሰለሞን መናገራቸው ተናገረዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ሳተላይት በህዋ ላይ ካላቸው ሌሎቹ 7 የአፍሪካ ሃገራት
ተርታ የሚያስመድባት ሲሆን እስካሁን ደቡብ አፍሪካ፣ግብጽ፣ጋና፣አልጄ
ሪያ፣ሞሮኮእና ጎረቤት ኬኒያ ባለቤት የሆኑ ሃገራት ናቸው፡፡
ምንጭዘኢስትአፍሪካን ኒውስፔፐር
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa