Ewunet Media

Ewunet Media

Share

30/10/2024

⭕️ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ጥቅምት 20/2017 ዓ፣ም ዕለታዊ ዜናዎች

1፤ የሱማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ዓሊ ሞሐመድ አደን የተባሉ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት በ72 ሰዓታት ከአገሪቱ እንዲወጡ ትናንት አዟል።

ሚንስቴሩ፣ ዲፕሎማቱ ከዲፕሎማሲ ተልዕኳቸው ጋር አብሮ የማይሄድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር በማለት ከሷል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ በዲፕሎማቱ መባረር ዙሪያ ያለው ነገር የለም።

2. የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ "ተቀራርቦ መነጋገርን የመሰለ ነገር የለም" በማለት ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በጋራ ከተነሱት ፎቶ ጋር በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጌታቸው፣ ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም በማለት ኹለቱን የሕወሓት ቡድኖች ለማገናኘት ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ አካላትን አመስግነዋል። ጌታቸው ከደብረጺዮን ጋር በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ፣ መቼና የት እንደተገናኙ ወይም የትኞቹ አካላት እንዳቀራረቧቸው ግን አልገለጡም።

3፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ካለፈው ስምንት አጋማሽ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ግንባሮች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በተካሄዱ ግጭቶች 102 የመንግሥት ወታደሮችንና በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ማርኬያለኹ ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አማጺው ቡድን በመንግሥት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅቻለኹ ያለው፣ ድሬ ኢንጪኒ፣ ደራ፣ ወረ ጃርሶ፣ አመያ፣ ዩብዶ፣ ጉቴ፣ ቦጂ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሳሲጋ፣ አባይ ጮመን፣ ሀርጡማ ፉርሴ፣ ኤልዋዬ፣ ገላና፣ ሱሮ ቡርጉዳ፣ በቾ እና ቦራ በተባሉ የግጭት ግንባሮች ነው። ቡድኑ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች፣ የግንኙነት መስመሮች እንደተቋረጡ መኾኑንም ጠቅሷል። መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ፣ በቡድኑ ላይ መጠነ ሰፊ የኃይል ርምጃ እየወሰደ መኾኑን ገልጧል።

4፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 2 ነጥብ 6 ትሪሊዮን መድረሱን አስታውቋል።

ባንኩ፣ በሩብ ዓመቱ ውስጥ 121 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱንም ገልጧል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ባንኩ 640 ሚሊዮን የገንዘብ ዝውውር በዲጂታል አማራጮች መካሄዱንና ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ46 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አውስቷል። በባንኩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች የ3 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር ግብይት እንደተፈጸመም ተገልጣል። [ዋዜማ]

12/06/2022

ለጥንቃቄ ያህል ነው
ሰሞውኑን የግብፅና የምዕራቡ አለም ጋዜጦች ኢትዮጵያና ግብፅ ሱዳን በኤምሬትስ አደራዳሪነት ወደ ድርድሩ ሊመለሱ ነው እያሉ ዜና እየሰሩ ነው። ይሄንን መረጃ ከነሱ ያነበቡት አንዳንድ ኢትዮጵያዊያንም እንደዚሁ ዘገባ ላይ ሲያውልት ተመልክተናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከመንግሥት ሰዎች ለማጣራት ሞክሬያለሁ። አንደኛ እስከ ሦስተኛ ወገን ድረስ አጣርቸ የሚከተለውን መረጃ አግኝቻለሁ።

ድርድሩ ከአፍሪካ ህብረት ውጭ እንደማይወጣና ኤምሬትስም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንዲጀመር ሦስቱም አገሮች አቋርጠውት ከነበረው ሰላማዊ ድርድር እንዲመለሱ ጥረት እያደረግች እንደሆነና ይሄም ጉዳይ ስኬታማ ትሁን አትሁን የራሷ ፍላጎት ብቻ እንደሆነ የግድቡን ድርደር ከሚመራው ከፍል አረጋግጠውልኛል።

የኤምሬትስ ፍላጎት ሦስቱም አገሮች በአፍሪካ ህብረት ስር የጀመሩትን ድርድር ማስቀጥል ብቻ እንደሆነም ነው ያገኘሁት መረጃ የሚያሳየው። ከዚህ በፊት ሦስቱን አገሮች ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡ አገሮች ነበሩ። ከነዚህ ውስጥ ሳኡዲ አረቢያ አሜሪካ ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ውጭ ሌላ አደራዳሪ እንደማትፈልግ በማሳወቋ ከዚህ ቀደም ከአፍሪካ ህብረት ውጭ የወጣው ድርድር ወደ አፍሪካ ህብረት መመለሱ አይዘነጋም። እናም አገራችን ዳግመኛ ዕንደዚህ አይነት ስህተቶችን እንደማትፈፅም ነው መረጃው የሚጠቁም።

ሱሌማን አብደላ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa
1234