Mesi Gashawu

Mesi Gashawu

Share

20/05/2025

በውስጥ የተገኘ መረጃ!!!

«የምመራቸውን ወጣቶች ካስጨረስኩ በኃላ ለመንግስት እጄን እሰጣለሁ» አብነው ታደሰ

በአብነው ታደሰ ድብቅ ሴራ በዛሬው ዕለት ብቻ 2 ሻለቃ መሪዎችና 22 ወጣቶች ተገደሉብን። በአባይ ሸለቆ እና በቦረና ወረዳ አካባቢ ከአብነው ታደሰ ጋር የምንቀሳቀስ ወጣቶች መረጃ ለመንግስት እየሰጠ አብነው ታደሰ አስጨረሰን።

በውስጥ መስመር የደረሰኝ መረጃ ነው። እባክህን እያለቅን ነው። ዛሬ አንድ ወንድማችንን አጥተናል። በአባይ ሸለቆና በቦረና አካባቢ በአብነው ታደስ የተባለ ሽማግሌ የምንመራ ወጣቶች ቀን በቀን ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተደዋወለ አስጨረሰን።

አሁን እጄን ለመንግስት ብሰጥ እኔ የምመራቸው ወጣቶች ስለሚያስጨርሱኝ ሁሉንም ቀስ በቀስ ብየ ካስገደልኩ በኃላ እጄን ለመንግስት እሰጣለሁ ብሎ ሲደውል ሰማሁት።

እባክህ ከማለቃችን በፊት ይሄ ሽማግሌ ሰውየ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አድርጉልን።

10/02/2025

የጽንፈኛ ኃይሉ ግፍ በሴት እህቶቻችን ላይ!

ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ኃይሉ ሴት እህቶቻችንን ግፍ በመስራት እንዲህ እያሰቃየ ይገኛል።

በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ አባይ ድልድይ ላይ የሚንቀሳቀሰዉ ፅንፈኛ ቡድን ሴቶችን መረጃ ሰጥታችሗል በማለት የፍጥኝ አስሮ እያሰቃየ ይገኛል።

ሲፈልግ ህዝብ በማገት ገንዘብ ይጠይቃል፣ ሲፈልግ የሀይማኖት አባቶችን በአደባባይ በእንብርክክ በማስሄድ ያዋርዳል አሁን ደግሞ ሴቶችን እንዲህ የኃሊት በማሰር በማሰቃየት ላይ ነው። ይሄ ነው የአማራ ህዝብ ተቆሮቋሪ ነኝ ባይ የሚሰራ ግፍ ነው።

የአማራ ህዝብ በዚህ ዘራፊና ጽንፈኛ ቡድን የደረሰበት ጠበሳ ብዙ ነው።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa