Ethio vine

Ethio vine

Share

28/05/2022

ደጉ ሳምራዊ

✝️"አጠገብህ ያለው ማን እንደሆነ ብታውቅ"

ቅዱስ አባ ቢሾይ የበቁና ክርስቶስ የሚያናግራቸው አባት ነበሩ። ከዕለታት በአንዱ ቀን የገዳሙ መነኮሳት አባ ቢሾይን ክርስቶስ ለኛም ይገለጥልን ዘንድ ንገሩልን ይሏቸዋል። እሳቸውም እሺ ይላሉ። ማታ ሲጸልዩ ክርስቶስ መጣ ከዛ እሷቸው ጌታ ሆይ ለወንድሞቼ መነኮሳት ተገለጥላቸው አሉት። ጌታም ቢሾይ ልጄ ነገ በተራራው ላይ በ6 ሰዓት እንደምገለጥላቸው ንገራቸው አላቸውና ተሰወረ። ቢሾይም ለመነኮሳቱ ነገሯቸው።

ከቀኑ 6 ሰዓት በሆነ ጊዜም መነኮሳቱ ክርስቶስን ለማየት ወደ ተራራ ሲሮጡ አንድ አቅመ ደካማ ሽማግሌ ተራራው ስር ቁጭ ብለው፥ "ልጆቼ እባካቹ ጌታን ላየው እሻለውና እኔንም ውሰዱኝ" እያሉ ለመኗቸው። መነኮሳቱ ግን አንተን ይዘን ታዘገየናለህ ሳናየው ታሳልፈናለህ እኛ ቸኩለናል እያሉ እያለፏቸው ሄዱ። መጨረሻ ላይ አባ ቢሾይ ሲመጡ እነዛ ሽማግሌ አባ ቢሾይን "እባክህ ውሰደኝ" አሏቸው።
አባ ቢሾይም አቅፈዋቸው ጉዞ ጀምሩ ትንሽ ቆይተውም ሽማግሌው ሰውዬ ከበዷቸው ዝቅ ብለው ቢያዩዋቸው ሽማግሌው ወደ ወጣትነት ተቀየሩ እጁና እግሩን ሲያዩት ችንካር አለው። ደነገጡ! ክርስቶስ ነው። ቢሾይ ልጄ እንዳከበርከኝ አከብርሀለው። ለመነኮሳት ወንድሞችህ ተገልጬ እንደነበርና በንቀታቸው ምክንያት እንዳለፍኳቸው ንገራቸው።

አጠገባቹ ያለውን ሳትወዱና ሳታከብሩ እኔን እንወድሃለን እናከብርሀለን ብትሉ ፍቅራቹ ውሸት ነው በላቸው ብሎ ክርስቶሰ ተሰወረ። ሰውን ስናከብር ፈጣሪ ያከብረናል ሰው የፈጣሪ አምሳል ነውና። ፈጣሪን በቀጥታ አናገኘውም በሰው ውስጥ ግን እናገኘዋለንና ሰውን እናክብር። ለዚህ ነው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ ሲመጣ ከነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ያደረጋችሁት ለኔ እንዳደረጋችሁት እቆጥረዋለው ያለን!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00