Ethos Entertainment and Events

Ethos Entertainment and Events

Share

05/12/2018

ሳህሌ ደጋጎ
-----
ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ውስጥ “ስቆ መኖር”፣ “እውነት ማሪኝ”፣ የሚሉትን ግጥሞች፣ “ዋይ ዋይ ሲሉ”፣ “ውሸት ለመናገር”፣ “ልብሽን ለአፈርሰው”፣ “ኮቱሜ”፣ የሚሉትን ዘፈኖች ግጥምና ዜማዎች የደረሰው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ነው፡፡
-
ከዚህም ሌላ ለድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ “አይወጣኝም ክፉ ነገር” በሚል የዘፈነችውና በብዙኀን ዘንድ ተወዳጅነት ያለውን (“ወደመጣሁበት ምድር፣ እስክመለስባት በክብር፣ ሰውን ከማስደሰት በቀር፣ አይወጣኝም ክፉ ነገር፣ ሙዚቃውን ያቀናበረው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ነው።
-
ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ “ፍላጎቴ”፣ “ምን ነበር”፣ “ምንድነው ትዝታህ”፣ ... የተሰኙትን የብዙነሽ በቀለን ዘፈኖች ያቀናበረ ሲሆን፣ “ከንቱ ሥጋ” የሚለውንና ሌሎችንም ዘፈኖችዋን ግጥም ደርሶላታል። “አታሳየኝ ጭንቁን”፣ “የፍቅር ወጋገን”፣ “ቃልኪዳን”፣ “በብር አይጋዛም”፣ “ፍቅርህ ቀሰቀሰኝ”፣ የተሰኙትን ዜማና ግጥሞች ያዘጋጀው ሣህሌ ደጋጎ ነው፡፡
-
“ሰው ከተሰማራ” በተሰኘው ዘፈኗ ለምትታወቀው ለድምፃዊት መንበረ በየነ ደግሞ “እንዴት ከረማችሁ” የሚለውን ዘፈን ግጥም የደረሰው ሌ /ኮ /ል ሣህሌ ነበር።
“የቆራጡ መሪ ፍሬው ጎመራ” የተሰኘውንና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ላቀነቀነችው ለድምፃዊት ውብሻው ስለሺ ደግሞ “ይህ ነው ጌትነት”፣ “የምድር ፈተና” የተሰኙትንና በ 1966 ዓ /ም የታተሙትን ዘፈኖችዋን ያቀናበረላት ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ነበር።
-
በዕድሜ ዘመን የኪነ ጥበብ አገልግሎት የክብር ሜዳሊያ እና የ 20 ሺህ ብር ተሸላሚ የሆነው ሣህሌ ደጋጎ፤ የ 30፣ የ 20 እና የ 10 ዓመት የረዥም ዘመን አገልግሎት የወርቅ፣ የብርና የነኀስ እንደዚሁም የተዋጊ ወታደርነት የደረት ዓርማ ኒሻን ተሸለሚም ነበር።

ፀሐፊ ፡ታጁዲን አሊይ

03/12/2018

አሁን ......ለማ ገ/ህይወትን አየሰማሁ ነው።
ስርቅርቁ ዜማቸው ቢቀርባችሁ ግጥማቸውን እንካችሁ!

ኮራ ያለ ዳሌ ሰበር ያለ አንጀት፣
ጠፈፍ ያለ ከንፈር ያልወደቀ ጡት፣
ሰብስቦ ሰጥቷታል ሁሉን ላንድ ሴት፣
እንዴት ያምላክ ፍጡር በእሷ ራብ ልሙት።
***
የገደል ዝንጀሮ ወጣበል ከሳሩ፣
ጠይም የወደደ ገናነው አሳሩ።
***
ፍቅሬ ትዝታዬ በጣሙን ውድ ነሽ፣
ፍቅርሽ ዋጋ አያውቅም ብርቱካን አልማዝ ነሽ።
***
እንደዚህ እንደዚህማ ከሆነ ነገሩ፣
ልብሽና ልቤ ዘብ ይተዳደሩ።
***
እያሉ ጋሽ ለማ ገ/ህይወት በመሰንቆ ታጅበው ይስረቀረቃሉ።
መቼም ዛሬ ላይ በህይወት ቢኖሩ....
".........ባንዘልቅ እንኳን አብረን እንደር" ብሎ የዘፈነውን
ምንኛ ይታዘቡት ነበር??
#ብትችሉ የጋሽ ለማ ገ/ህይወትን ዘፈኖች ፈልጉና ስሙ።

©Abebaw Fiseha

Want your business to be the top-listed Event Planning Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
2906