Ethio Tube's
04/04/2025
አዲሱ የትራምፕ ታሪፍ።
አብዛኞቹ ሃገራት ላይ አሜሪካንን ከሚያስከፍሏት ታሪፍ ትራምፕ አሁን የጫኑት ግማሹን ያህል ነው። ለምሳሌ ቻይና 67% ታሪፍ አሜሪካንን የምታስከፍል ሲሆን ትራምፕ በአዲሱ ታሪፍ 34% ያስከፍላሉ። ካምቦዲያ 97% አሜሪካንን ታስከፍላለች፣ አሜሪካ አሁን 49% አድርጋባታለች።
🇪🇹 ኢትዮጵያ፡ 10%
🇨🇳 ቻይና: 34%
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት: 20%
🇻🇳 ቬትናም: 46%
🇹🇼 ታይዋን: 32%
🇯🇵 ጃፓን: 24%
🇮🇳 ሕንድ: 26%
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ: 25%
🇹🇭 ታይላንድ: 36%
🇨🇭 ስዊዘርላንድ: 31%
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ: 32%
🇲🇾 ማሌዥያ: 24%
🇰🇭 ካምቦዲያ: 49%
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም: 10%
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ: 30%
🇧🇷 ብራዚል: 10%
🇧🇩 ባንግላዴሽ: 37%
🇸🇬 ሲንጋፖር: 10%
🇮🇱 እስራኤል: 17%
🇵🇭 ፊሊፒንስ: 17%
🇨🇱 ቺሊ: 10%
🇦🇺 አውስትራሊያ: 10%
🇵🇰 ፓኪስታን: 29%
🇹🇷 ቱርክ: 10%
🇱🇰 ሲሪ ላንካ: 44%
04/04/2025
#
#
•Banner
•Flyer
•Business Card
•Sticker
•T-shirt
•Mugs
All in one
👎👎👎👎 👎👎
📱 0901578081
📱 0904041800
01/04/2025
14/08/2024
ሜሮን ጌትነት እንደገጠመችው
ተቀበል
የህዝብን አደራ በላብና በእንባ በፍቅር አንግቦ፣
አንገትን በነሀስ፣ በወርቅና በብር ሜዳሊያ አስውቦ፣
በዓለም አደባባይ በኩራት መታየት ሠንደቅ አውለብልቦ።
ብቸኛ ሀብታችን ከሃያላን ጋራ ለእኩል የሚያበቃ
ደሃ ስማችንን የሚያሰርዝልን ለጥቂት ደቂቃ።
የጥቂቶች እግር፣ ህልም፣ ድካም፣ ዋጋ፣ የብዙሃን ተስፋ፣
የአመታት ድል፣ ታሪክ በጥቂቶች ጉድለት ብን ብሎ ጠፋ!
ደግ ነው አንዳንዴ…
ሽንፈት ባይዋጥም ያውም ለድል ልምዱ
አልቀበል ያልነው የሀገር አወዳደቅ መታያ መንገዱ
ይሄኛው ነው አንዱ።
ተቀበል!
14/08/2024
“ ዶ/ር አሸብር ህዝብን ካከበሩ ኃላፊነታቸውን ያስረክቡ “ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያን ህዝብ ካከበሩ ሀላፊነታቸውን እንዲያስረክቡ ጠይቋል።
“ በኦሎምፒክ ከአለም አርባ ሰባተኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀን አንገታችንን ቀና ማድረግ አንችልም “ ያለው ኃይሌ “ በኬንያ እና በእኛ መሀል የበርካታ ሀገራት ልዩነት ነው ያለው “ ሲል ገልጿል።
አትሌት ሲሳይ ለማ ታምራት ቶላ እንዲወዳደር በመጠየቁ ትልቅ ክብር እንዳለው የገለፀው ኃይሌ ገ/ስላሴ “ እሱም ወርቅ ነው ያመጣው “ ሲል አክብሮቱን ገልፆለታል።
ሌሎች አትሌቶች እና ሀላፊዎችም ከአትሌት ሲሳይ ለማ መማር እንዳለባቸው እና ሀገርን ማስቀደም እንዳለባቸውም አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር “ እንደሚናገሩት ለኢትዮጰያ ህዝብ ክብር ካላቸው ኃላፊነታቸውን ያስረክቡ “ ሲልም ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ጠይቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.