Gebeya

Gebeya

Share

25/06/2020

Gebeya News 📰🗞

በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ የመጀመሪያው የክትባት ሙከራ ተጀመረ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/2012 ዓ.ም (አብመድ) አምስት የአፍሪካ ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ የክትባት ሙከራ አቅም መገንባታቸው ታውቋል፡፡
በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባት በሙከራ ደረጃ ትናንት ሰኔ 17/2012 ዓ.ም እንደተጀመረ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡ በእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በልጽጎ የተሰራው ክትባት በደቡብ አፍሪካ፣ እንግሊዝና ብራዚል መጠነ ሰፊ ሙከራ እየተደረገበት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ከጆሃንስበርግ በክትባት ሙከራው በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፈው ጁኒየር ሙህሎንጎ ''በትንሹ ብፈራም በክትባቱ ምን እንደሚከሰት ለማወቅ እሻለሁ፤ ይህም ለጓደኞቼና ለሌሎች በጥናቱ ምን እንደተካሄደ መናገር ያስችለኛል'' ብሏል።
ካሜሮን፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካና ኬንያ በከፍተኛ ሁኔታ ክሊኒካዊ የክትባት ሙከራ አቅም መገንባታቸውን በደቡብ አፍሪካ የኮሮናቫይረስ የሚኒስትሮች አማካሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሳሊም አብዱል ካሪም ተናግረዋል። ሌሎች ከሰሃራ በታች ያሉ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም ክሊኒካዊ የሙከራ አቅም እንዳላቸው በእንግሊዝ የኅብረተሰብ ጤና ፈጣን ምላሽ ሰጪ የድጋፍ ቡድን ዳይሬክተር ዳንኤል ቦስች አስታውቀዋል፡፡
1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሕዝብ ያላት አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኮሮናቫይረስ ክትባት ጋር በተገናኘ የአቅርቦት መሰናክሎች እንዳይጋረጡባትና እንዳትገፋ የሚሉ ስጋቶች አሉ። የአዓም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ደግሞ ማንኛውም ቀዳሚ የቫይረሱ ክትባት አቅርቦት በእጅጉ በሚያስፈልግበት አካባቢ እንጂ ገንዘብ በመክፈል አቅም መሆን እንደሌለበት እያስታወቁ ነው፡፡
ቻይናም የኮሮናቫይረስ ክትባት ካገኘች የአፍሪካ ሀገራትን ከቀዳሚ ተጠቃሚዎች መካከል እንደምታደርግ ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
በኪሩቤል ተሾመ

Want your business to be the top-listed Clothing Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
00251