Tourism Training Institute

Tourism Training Institute

Share

Photos from Tourism Training Institute's post 20/06/2026

በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የትብብር ስልጠናን ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ::
ቱ.ማ.ኢ
ሰኔ 13/2018 ዓ ም

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና (Cooperative Training) ከሚሰጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅት ለመፍጠር የሚያስችል የምክክር መድረክ አካሄደ።

የፕሮግራሙ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ሲሆኑ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በትብብር ስልጠና ዙሪያ ሰልጣኞች ተሰማርተውባቸው ከነበሩ የሆቴልና የቱሪዝም ተቋማት የነበሩ ሂደቶችን ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎችን ጭምር የሚዳስስ ገለጻ ያቀረቡት የትብብር ስልጠና አስተባባሪና አሰልጣኝ አቶ ሳለአምላክ ፈንታ ናቸው፡፡
እንደ አቶ ሳለ አምላክ ገለጻ ሰልጣኞችን ከመቀበል ጀምሮ በወሰዱት ኮርስ መሠረት በመመደብ እና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ትክክለኛ ውጤት እስከ መሙላት ለተወጡት ኃላፊነት ምስጋናም አቅርበዋል፡፡

ይህ ስልጠና ለሰልጣኞች የተግባር ክህሎትን በተጨባጭ የስራ አካባቢ እንዲቀስሙ፣
ለአሰልጣኝ ተቋማት (ለሆቴሎችና ቱሪዝም ድርጅቶች)፡ የገበያውን ፍላጎት ያማከለ የሰው ኃይል በቅርበት እንዲያገኙ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ለድርጅቶቹም ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት በትብብር ስልጠና የነበረው የዓመቱ እቅድ አፈጻጸም 96 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

በመቀጠልም በቤት አያያዝ እና ላውንደሪ ሰርቪስ ስልጠና የሰልጣኝ መጥፋት እና በሆቴሎችና መስል ድርጅቶች ደግሞ ያለው ፍላጎት መጨመር ምክንያቶቹን እና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እና መወሰድ ያለባቸውን መፍትሔዎች የሚጠቁም ጥናት በአቶ ሰይድ ተስፋዬ ቀርቧል።

ለውይይት በቀረቡ መነሻ የሆኑ ጹሁፎች ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደረጓል።
በማጠቃለያው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በቀጣይ ስልጠናውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ፣ የበቃ የሰው ኃይል ለማፍራት የኢንደስትሪውና የስልጠና ተቋማት ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑ ከቤቱ በተነሱ ሀሳቦች መረዳት ይቻላል ብለዋል።

የስልጠናው አቀራረብ የንድፈሃሳብ 30 ፣ የተግባር 40 በተቋም አጠቃላይ 70 በመቶ ሲሆን ከኢንደስትሪው ደግሞ 30 በመቶ የሚሸፈን ነው፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

Photos from Tourism Training Institute's post 03/06/2026

ቲዎሪን በተግባር፡ የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች በቢሾፍቱ የመስክ ምልከታ አካሄዱ
ቱ.ማ.ኢ
ግንቦት 26/2018 ዓ.ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በክፍል ውስጥ የተማሩትን የንድፈ-ሀሳብ ትምህርት ይበልጥ ለማጠናከር በቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ በሚገኙ ውብ ሀይቆችና የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ የተግባር ልምምድና የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

ሰልጣኞቹ በጉብኝታቸው የቢሾፍቱን ታዋቂ ሀይቆች ስነ-ምህዳር እና የቱሪዝም እምቅ አቅም በተጨባጭ ተመልክተዋል፣ የዋና እና የጀልባ ጉዞ (Boating) ልምምድ አድርገዋል፡፡
የባቦጋያ እና ሆራ አርሰዲ ሀይቆች ታሪካዊ አመጣጥ ለአካባቢው ማህበረሰብ ስላላቸው ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ሰፊ ገለጻ በአስጎቢኚዎች ተደርጎላቸዋል።

በጉብኝታቸው በሆራ ሆራ አርሰዲ እና በቢሾፍቱ ሀይቆች ላይ የሚገኙ የተለያዩ ብርቅዬና ስደተኛ አእዋፋትን የተመለከቱ ሲሆን፣ ስለ አእዋፋቱ ዝርያዎች፣ ባህሪና ስለ ስነ-ምህዳር ጥበቃ ግንዛቤ አግኝተዋል።
በአጠቃላይ ለቱሪዝም ሰልጣኞች በሶስት ክፍል የተዘጋጀው የመስክ ምልከታና የተግባር ስልጠና አስመልክቶ የጉዞው አስተባባሪ እና የቱሪዝም ፋኩልቲ ዲን አቶ ሲሳይ አብርሃም እንደገለጹት ሰልጣኞቹ የወደፊት የቱሪዝም ባለሙያነታቸውንና የአስጎብኚነት ክህሎታቸውን ሊያሳድጉ የሚችሉ ተግባራዊ ልምዶችን የቀሰሙበት ነው ብለዋል፡፡
ይህን መሰል የተግባር ስልጠና የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል እና በኢንዱስትሪው ውስጥ በቀጥታ መሰማራት የሚችሉ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ትልቅ ሚና ይጫወታልም ብለዋል፡፡

ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

Photos from Tourism Training Institute's post 26/05/2026

የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ
ቱ.ማ.ኢ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሰልጣኞች በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል።
በዚህ ጉብኝት የአዲአበባ ዩንቨርሲቲ የእንስሳት ተፈጥሮ ቅርስ ጥበቃ መዘክር፣ የአድዋ ድል መታሰቢያ፣ የጉለሌ እጽዋት እና የእንጦጦ ፓርክ ተጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የቱሪዝም ማኔጀመንት ሦስተኛ ዓመት፣ የቱርጋይድና የቱር ኦፕሬሽን አንደኛ እና ሁለተኛ ዓመት ሰልጣኞች በትምህርታዊ ጉብኝቱ እየተሳተፉ እንደሆኑ የቱሪዝም ፋካሊቲ ዲን አቶ ሲሳይ አብርሃም ተናግረዋል።
በዚህ ትምህርታዊ ጉብኝት የተሳተፉ ሰልጣኞች እንደተናገሩት ጉብኝቱ በንድፈ ያገኘነውን ዕውቀት በተግባር እንድናየው እድል የሰጠነው ብለዋል፡፡ ትምህርታዊ ጉብኝቱ በተለያዩ ቦታዎች የሚቀጥል ይሆናል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

Want your university to be the top-listed University in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Near Guenet Hotel
Addis Ababa
4350