Tips for Poors
04/02/2026
በዚህ ስዓት በመንፈሳዊ ሕይወትም በብዙ ድካም የምትኖሩ ጌታን ለማስደሰት፣ የቅድሰናን ሕይወት ለመኖር በብዙ ድካም ውስጥ የምትገኙ የተወደዳቹ ወዳጆቼ በብዙ ፈተና በማጣት ሆነ በመውድቅ በመነሳት የምትታገሉ በርቱ ተስፋ አትቁረጡ ተነሱ ሞክሩ በክርስቶስ ባላቹ ፀጋ በርቱ፣ ሞክሩ።
አይዞአችሁ ከመሞከር አንድከም እንበርታ!
ሙከራችን በመልካም እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን።
23/01/2026
አስታወሳችሁት ?
የሆነ ሰሞን በዚህ ዘፈን ቲክቶክ ላይ የሆነ የሩጫ ትሬንድ አስጀምሮ ለጉድ ፈምሶ ፣ መነጋጋሪያ ሆኖ ነበር።
ስሙ መሀመድ አደም ኦጋ ይባላል። ምድር ላይ ያላየው የስቃይ አይነት የለም። በተደጋጋሚ ከሞት አፋፍ ተመልሷል !
ከሊቢያ ወደ ኢውሮፕ ለመግባት ከተሰደዱ 15 ሰዎች ውስጥ ብቸኛ የተረፈው ሰው ነው። በዛ ሰዓት ብዙ መከራዎችን አይቷል። አብረው ከተሰደዱት ውስጥ ግማሾቹ አጠገቡ ሲሞቱ ፣ አንዳንዶችም በተስፋ መቁረጥ ባህር ውስጥ ራሳቸውን ሲጨምሩ ተመልክቷል።
በመጨረሻም በህይወት ከቀሩት ሌሎች 2 ሱማሌዎች ጋር ፣ የራሳቸውን ነብስ ለማቆየት የሞ*ተ ሰው ሬ* #ሳ እስከመመገብ ደርሷል። በዚህም አንዳንዶች ሲወቅሱት ፣ ሌሎችም ሲያደንቁት ቆይቷል።
ሜድትሪያን ባህር ላይ የተሳፈሩበት ታንኳ ሲገኝ ፣ መሀመድ አደም ኦጋ ብቻ እራሱን ስቶ ነበር የተገኘው።
ከዛም በኋላ ለማገገም ብዙ ህክምናዎችን አድርጓል። ሰይፉ ፋንታሁን 'ከነቃህ በኋላ ወደ ጤናህ ለመመለስ ምን ያህል ጊዜ ፈጀብህ ?' ሲለው ፣ መሀመድ አደም ኦጋ 'እስከአሁንም ጤናዬ አልተመለሰም....' ሲል ነበር የመለሰው።
የመሀመድን አደም ኦጋን የህይወት ታሪክ በተመለከተ ዶክመንተሪዎች ተሰርተዋል። መፅሃፍም ተፅፎ ታትሟል።
በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ያለፈው መሀመድ አደም ኦጋ አሁን ላይ አግብቶ ፣ የሴት ልጅ አባት እንደሆነ የሚያሳይ የሚያምር ፎቶ ለቋል።
ከብዙ ሞት ከማምለጥ ፣ ከብዙ ተስፋ ከማድረግ ፣ ከብዙ መታገስ ፣ ከብዙ መከራ በኋላ የሚመጣ አዲስ ህይወት እንዳለ የመሀመድ አደም ኦጋ ህይወት ምስክር ነው !
እንኳን ጌታ ረዳዉ❤🙌
14/05/2024
ለወገን ደራሽ ወገን ብቻ ነው፣
ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው🙏
ጎዳና ላይ ሆኖ ምግብ፣ ልብስ፣ታሞ ህክምና እንዲሁ የተሻለ ስራ የሚሹ በርካታ ናቸው።
ስለዚህ ሁላችንም እነዚህን ወገን ለመርዳት ስትፈልጉ እንዲሁም ከእኛ ጋር አብሮ ለመስራት የምትፈልጉ ወገኖች፦
ለበለጠ መረጃ ፦ WhatsApp +251942203334
በዚህ ደውለው ማግኘት ይችላሉ🙏
የሚረዱ እጆች ሁሌም የተባረኩ ናቸው🙏
Click here to claim your Sponsored Listing.