Eco African
26/05/2026
!
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ
!
The Founding of the Organization of African Unity (OAU)
“በዚህ በዛሬው ቀን በዚህች በዋና ከተማችን በአዲስ አበባ የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ተካፋይ ለመሆን የመጣችሁትን የነፃ አፍሪካ አገር መሪዎች፣ ወንድሞቻችን በራሳችንና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ስንቀበል በጣም ደስ ይለናል።
ይህ ዛሬ እኛ የአፍሪካ ነፃ መንግሥታት መሪዎች የምናደርገው ጉባኤ በዓለም ላይ እስካሁን ድረስ ተወዳዳሪ የለውም። የዚህን ታላቅ ጉባኤ መደረግና የመላው አፍሪካ አገሮች መሪዎች ተካፋይ በመሆን ለዚህች ክፍለ ዓለማችን በውስጧም ለሚገኙት ሕዝቦቻችን ላለን ጥልቅ አሳቢነት ዓይነተኛ ምስክር ነው። ባጭሩ ይህ ቀን ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን በመላ ታሪካዊና ታላቅ ቀን
ነው … ።”
ዕለታዊው የአዲስ ዘመን የወርሀ ግንቦት 15 ቀን 1955 ዓ.ም ዕትሙ በፊት ለፊት ገጽ ላይ፣ ‹‹ሠላሳ የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ጉባኤ በአፍሪካ አዳራሽ ተከፈተ።
ግርማዊ ጃንሆይም የጉባኤው የክብር ሊቀመንበር እንዲሆኑ ተመረጡ።›› በሚል ዐቢይ ርዕስ ስር እንዲህ ይላል፡-
“ቁጥራቸው ከ250 ሚሊየን በላይ በሆኑ አፍሪካውያን እጅግ በጋለ ስሜት ይጠበቅ የነበረውና መላው ዓላም ህዝብ ሁኔታውን በቅርብ ይከታተለው የነበረው የ30ዎቹ የአፍሪካ ነጻ መንግስታት መሪዎች ጉባዔ ግንቦት 14 ቀን ትናንት ከእኩለ ቀን በኋላ በአፍሪካ አዳራሽ ተከፍቷል። … ጉባኤውን የከፈቱት ግርማዊ ንጉሠ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጉባኤው ስራውን ከመጀመሩ በፊት የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እንዲደረግ አሳስበው ጸሎት ተደረገ።
ቀጥሎም የሊቀ መንበር ምርጫ እንዲደረግ አሳስበው የጊኒው ፕሬዚደንት ሴኩቱሬ የመጀመሪያውን ምርጫ እንዲያደርጉ ጠየቁ። ክቡር ፕሬዚደንት ሴኩቱሬ ቀደም ብሎ ተደርጎ የነበረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባዔ ጠቅላላ ውሳኔ ያልሰጠ መሆኑን በመግለጽ ከተናገሩ በኋላ፣ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት የጉባዔው ፕሬዚደንት የላይቤሪያው ፕሬዚደንት ተብማን፤ የተባበረው የአረብ አንድነት ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ናስርና የጋናው ፕሬዚደንት ንኩሩማህ፤ የአይቮሪኮስቱ ፕሬዚደንት ቧኜ፤ የናይጄሪያው ታፌዋ ባሌዋ የሴኔጋሉ ሊዎፖልድ ሴንጎር፤ የኮንጎ ብራዛቪሉ ኦቦ ፋልቤር ዩሉና የታንጋኒካው ጁሊየስ ኔሬሬ የጉባኤው ተከታታይ ፕሬዚደንቶች እንዲሆኑ ሐሳብ አቀረቡ።
ይህ ሐሳብ በጉባኤው አባሎች በሙሉ በመደገፉ በፕሬዚደንት ሴኮቱሬ የቀረበው ምርጫ ጸደቀ። ከዚህ በኋላ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ለዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ሥራ ታላቅ መመሪያ የሚሰጥ ንግግር አደረጉ።”
አፄ ኃይለ ሥላሴ በወቅቱ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግራቸው እንዲህ ብለው ነበር።
“ዛሬ የገጠመን ዕድል በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ መቼም ያልተገኘ ትልቅ ዕድል ነው። በፊታችን የተደቀኑት ችግሮች ያንኑ ያህል ከፍ ያሉና ከባድ ናቸው። ታሪክና ጊዜ የጣሉብን ከፍተኛ ኃላፊነት ሁላችንም ረጋ ብለን እንድናስብና እንድናመዛዝን ያስገድደናል። የተነሳንበትን ከፍተኛ ተግባር በመልካም አከናውነን ብንገኝ ስማችንና ተግባራችን በታሪክ መልካም ስም ይኖረዋል። ተግባራችንን ሳንፈጽም ብንቀር ግን ይታዘንብናል። ስለዚህ እምነታቸውን የጣሉብንን ሕዝቦቻችን በሚመጡት ጊዜያቶች ውስጥ ከእኛ የሚጠብቁትን ሁሉ ለመፈጸም እንዲያበቃን ሁሉን የሚችለውን ፈጣሪያችን ጥበብንና አስተዋይነትን እንዲሰጠን እናምነዋለን፣ እንለምንዋለን።”
ግንቦት 17 ቀን የድርጅቱ ቻርተር ከተፈረመ በኋላ ማታ ላይ ከምሽቱ ሁለት ሰኣት ጀምሮ በታላቁ ቤተመንግስት ስለአፍሪካ መሪዎች እንግድነት ክብር ታላቅ የእራት ግብዣ ተደርጓል::
(ዳንኤል እንግዳ)
63rd Anniversary!
The Founding of the Organization of African Unity (OAU)
“On this very day, in this our capital city of Addis Ababa, we are profoundly delighted to welcome, in our own name and on behalf of the entire Ethiopian people, the leaders of independent African nations, our brothers, who have come to participate in this historic summit.
The summit we, the leaders of independent African states, are holding today is unprecedented in world history. The convening of this grand summit, and the participation of the leaders of all African nations, stands as a distinct testament to the deep care we hold for this continent of ours and for the peoples within it. In short, this day is an entirely historic and momentous day for Africa and Africans…”
The front page of the daily Addis Zemen newspaper, in its May 24, 1963 (Gimbo 15, 1955 E.C.) edition, under the main headline, “Summit Opens at Africa Hall in the Presence of Thirty African Leaders. His Imperial Majesty Elected Honorary Chairman of the Conference,” reported the following:
“The summit of the leaders of 30 independent African nations, which had been anticipated with immense enthusiasm by more than 250 million Africans and closely watched by the entire global community, opened yesterday afternoon, May 23 (Gimbot 14), at Africa Hall. …
His Imperial Majesty Emperor Haile Selassie I, who opened the summit, requested a one-minute moment of silent prayer before the conference commenced its work, which was then observed.
Following this, His Majesty called for the election of a chairman and invited the President of Guinea, Sékou Touré, to make the first nomination. After noting that the preceding conference of Foreign Ministers had not reached a definitive conclusion, Honorable President Sékou Touré proposed that His Imperial Majesty serve as the President of the summit. He further proposed that President Tubman of Liberia, President Nasser of the United Arab Republic, President Nkrumah of Ghana, President Houphouët-Boigny of Ivory Coast, Tafawa Balewa of Nigeria, Léopold Senghor of Senegal, Abbé Fulbert Youlou of Congo-Brazzaville, and Julius Nyerere of Tanganyika serve as vice-presidents of the conference.
This proposal was unanimously supported by all members of the summit, and the nominations presented by President Sékou Touré were approved. Thereafter, His Imperial Majesty delivered a speech that provided grand guidance for the work of this historic summit.”
In his historic speech at the time, Emperor Haile Selassie remarked:
“The opportunity that stands before us today is a monumental one, never before witnessed in African history. The challenges arrayed against us are equally lofty and formidable. The immense responsibility placed upon us by history and time compels us all to reflect calmly and weigh our choices deliberately. If we successfully execute the great task we have undertaken, our names and actions will hold an honorable place in history. However, should we fail to fulfill our duty, history will look upon us with sorrow. Therefore, we trust and pray that our Almighty Creator grants us wisdom and discernment, enabling us to fulfill everything that our peoples, who have placed their faith in us, expect from us in the times ahead.”
Following the signing of the Organization’s Charter on May 25 (Gimbot 17), a grand state dinner was hosted later that evening, beginning at 8:00 PM at the Grand Palace, in honor of the visiting African leaders.
(Daniel Engida)
31/01/2026
https://youtube.com/shorts/TVAld8CFOks?si=DWTzsIcWtt96xqn-
#Ethiopa/Tigray @eco_africa Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
🇰🇪
14/01/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.