Selam

Selam

Share

Ethiopia Super Grain Teff in USA 04/12/2022

Ethiopia Super Grain Teff in USA My plate on ethiopian nutrition and diet

በእርግዝና ወቅት ማስወገድ ያለብን የአመጋገብ አይነቶች - Foods and beverages to avoid in pregnancy 21/07/2022

✍ #በእርግዝና # ወቅት #ማስወገድ ያለብን # የአመጋገብ አይነቶች #

📌 በእርግዝና ወቅት ለፅንሱና ለእናትየው ጤንነት አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋነኛው የተስተካከለና ጤናማ የሆነ አመጋገብ መከተል ነዉ። ይህም የሚያስፈልገው ለፅንሱ ጤናማ እድገትና በንጥረ ነገሮች እጥረት ምክንያት በፅንሱ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን ለመከላከል ነው።በፅንሱና በእናትየው ጤንነት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ነገሮች መካከል ንፅህናቸውን ያልጠበቁ ፣ በደንብ ያልበሰሉንና ለጎጂ ኬሚካሎች(ሊድ፣ሜርኩሪ) የተጋለጡ ምግቦችን መመገብ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። በመሆኑም ከሌላው ጊዜ በተለየ በእርግዝና ወራት ላይ ስለምንመገባቸው ምግቦች ጤንነትና ይዘት ማወቅና ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ወራቶች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ ነው።

👉በእርግዝና ወቅት ማስወገድ ያለብን የአመጋገብ አይነቶች

1.ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ የአሳና የበሬ ስጋ፦ በተገቢው መንገድ ያልበሰለ ስጋ በቫይረስ፣ባክቴሪያና ኘሮቶዝዋ አማካኝነት ለሚመጡ የምግብ ላይ ኢንፌክሽኖች የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው።በተለይም በባክቴሪያ ለሚመጡ ኢንፌክሽኖች(Salmonella,Listera and vibro) የመጋለጥ እድሉ ከሌላው የጨመረ ነው።

2.ያልበሰለ ወይም ተሰርቶ የቆየ እንቁላል፦በደንብ ያልበሰለ እንቁላል በባክቴሪያ(samonella) አማካኝነት ለሚመጣው የምግብ ላይ ኢንፌክሽን በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጠ ሲሆን የሚያሳያቸውም ምልክቶች ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣የሆድ ቁርጠትና ተቅማጥ ናቸው።

3.የበሬ ወይም የበግ የውስጥ አካል ስጋ(Organ meat) ፡-የእንስሳት የውስጥ አካል ስጋ በመባል የሚጠቀሱት ልብ፣ኩላሊት፣ጨጓራና አንጨት ሲሆኑ በተፈጥሮ ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑትን የማዕድንና ቫይታሚን ንጥረ ነገሮች አሟልተው የያዙ ናቸው። ነገር ግን በእርግዝና ወቅት እነዚህን የውስጥ አካል ስጋዎችን አብዝቶ መብላት በፅንሱ ጤንነትና ህልውና ላይ አደጋ ሊያደርስ ይችላል።ይህም የሚሆነው የውስጥ አካል ስጋ በዋነኝነት በውስጡ ከሚይዛቸው ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ቫይታሚን ኤ በተለይም የፅንሱ የሰዉነት አካሎች በሚሰሩበት በእርግዝና የመጀመሪያ ወራቶች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ ነው።

📌 የቀረበዉን ጽሑፍ ከወደዱት በቅንነት ሼር ያድርጉ

በእርግዝና ወቅት ማስወገድ ያለብን የአመጋገብ አይነቶች - Foods and beverages to avoid in pregnancy በእርግዝና ወቅት ማስወገድ ያለብን የአመጋገብ አይነቶች - Foods and beverages to avoid in pregnancy

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa