Hussein D. Wotticha

Hussein D. Wotticha

Share

03/11/2023

ይህ እየሆነ ያለው 2ኛ ጥፋት ይሁን? ወላሁ አለም
👇👇👇👇👇👇
"4) ወደ እስራኤልም ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ (እንዲህ በማለት) አወረድን፡፡ በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ፡፡ ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ፡፡

5) ከሁለቱ (ጊዜያቶች) የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለእኛ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን በእናንተ ላይ እንልካለን፡፡ በቤቶችም መካከል ይመላለሳሉ፤ (ይበረብሩታል፡፡) ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር፡፡

6) ከዚያም (በኋላ) ለእናንተ በእነሱ ላይ ድልን መለስንላችሁ፡፡ በገንዘቦችና በወንዶች ልጆችም ጨመርንላችሁ፡፡ በወገንም የበዛችሁ አደረግናችሁ፡፡

7) መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡ መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፤ (አልን)፡፡ የኋለኛይቱም (ጊዜ) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ፣ ያሸነፉትንም ሁሉ (ፈጽመው) ማጥፋትን እንዲያጠፉ (እንልካቸዋልን)፡፡

8 (በመጽሐፉም አልን) «ብትጸጸቱ፡- ጌታችሁ ሊያዝንላችሁ ይከጀላል፡፡ (ወደ ማጥፋት) ብትመለሱም እንመለሳለን፡፡ ገሀነምንም ለከሓዲዎች ማሰሪያ አደርገናል፡፡

9) ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡

10) እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅተንላቸዋል፤"
ቁርአን: የ አል-እስራ ምእራፍ ቁ 4-10

Want your practice to be the top-listed Law Practice in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa