Ethio Times
26/11/2024
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፅንፈኛው ቡድን እጅ እየሠጠ ነው።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አምባ ጊዮርጊስ፣ ገደብየና ወርቀ ደሙ አካባቢዎች ለዓመታት የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውኩና ሲዘርፉ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን አባላት ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለ ጦር እጅ ሰጥተዋል።
በቀጠናው የሚገኘው ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ተክሌ አጋ በቀጠናው በተደጋጋሚ ሰላማዊ ውይይት በማድረግ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን አማራጭ አድርገውና በፍቃደኝነት ሃያ አምስት ታጣቂዎች ከ16 ክላሽ፣ 01 አርባ ጎራሽ እና ሌላም በመያዝ እጃቸውን መስጠታቸውን ገልፀዋል።
የአካባቢው ህብረተሰብ መከላከያ ሠራዊቱ በሚያደርጋቸው ስምሪቶችና በሚወጣቸው ግዳጆች እያሳየ ያለው ድጋፍና እገዛ የሚደነቅ በመሆኑ ለቀጣይም አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ሲሉ የክፍለ ጦር አዛዥ ተናግረዋል።
https://t.me/GanderTimes
16/08/2024
በ2023 የሩሲያ እና ኢራን የንግድ ግንኙነት 5 ቢሊየን ዶላር ደርሷል
በኢራን እና ሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ እንደሚገኝ አሜሪካ ገለጸች።
የዩክሬኑ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሀገራቱ ግንኙነት መጨመሩ ተሰምቷል
በሩሲያ እና ኢራን መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደሚገኝ አሜሪካ አስታወቀች፡፡
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር መስርያ ቤት ፔንታጎን ምክትል ቃል አቀባይ ሰብሪና ሲንግ በሳምንታዊ መግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት የሀገራቱን ግንኙነት አሜሪካ በቅርበት እየተከታተለች ትገኛለች፡፡
ከዋሽንግተን በተጻራሪ የቆሙት ሞስኮ እና ቴሄራን ከሶቭየት ህብረት መፍረስ ጀምሮ እያሳደጉት የሚገኝው ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተጠናክሮ ይገኛል፡፡
ሞስኮ እና ቴሄራን በመካከለኛው ምስራቅ በኢራቅ፣ ሶርያ ፣ አፍጋኒስታን የሚያንጸባርቁት ሀሳብ ተመሳሳይ ከመሆኑ ባለፈ በአንዳንድ ሀገራት ላይ ለተመሳሳይ ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወቃል፡፡
ሀገራቱ በጋዛው ጦርነት ለሀማስ እንደሚወግኑም የፔንታጎን ምክትል ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያ በዩክሬን ላይ በምታደርገው ውግያ የኢራን ከፍተኛ የጦር መሳርያዎች እና ድሮኖች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ነው ያነሱት፡፡
ባሳለፍነው መጋቢት ሮይተርስ ባወጣው መረጃ ኢራን ለሩሲያ 400 ባላስቲክ ሚሳኤሎችን መላኳን ከውስጥ ምንጮቼ አገኝሁት ባለው መረጃ መዘገቡ ይታሰዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ሞስኮ እና ቴሄራን ጉዳዩን ቢያስተባብሉም መሰል የጦር መሳርያ ድጋፎ እና ልውውጦች በሀገራቱ መካከል እንደሚደረግ ተደጋጋሚ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
ሶስተኛ አመቱን ባስቆጠው የዩክሬን ጦርነት ሩሲያ የመድፍ ተተኳሶችን ፣ ድሮኖችን እና የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤሎችን ከኢራን እንደምታስገባ ሲገለጽ በተመሳሳይ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን ለኢራን በመሸጥ ላይ እንደምትገኝ ተነግሯል፡፡
ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ ኢራን ከሩሲያ ጋር ከቀረጥ ነጻ የንግድ ስምምነት ላይ ደርሳለች፤ ከዚህ በተጨማሪም በ2010 ሀገራቱ የተፈራረሙትን የሁለትዮሽ የትብብር ስምነት በአዲስ ስምምነት ተክተዋል፡፡
በ2023 የታደሰው ስምምነት ኢኮኖሚ ፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትብብርን የሚያካትት ሲሆን ለ20 አመታት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ አመት በሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 5 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ነበር፡፡
በአለም አቀፍ መድረክ የሀገራቱን ወዳጅነት እና ትብብር በስጋትነት የምታየው አሜሪካ በቅርብ አመታት እያደገ የመጣውን ግንኙነታቸውን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብላለች፡፡
ለተለያዩ አዳዲስ መረጃዎች ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ☞ https://t.me/GonderTimes
13/08/2024
ኢራን በሞስኮ ለእይታ ያቀረበችው ድሮን - “ሞሃጀር-10”
ኢራን በሞስኮ የባለስቲክ ሚሳኤሎች እና ድሮኖችን ጨምሮ አዳዲስና ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎቿን ለእይታ አቅርባለች
ኢራን በእስራኤል ላይ እፈጽመዋለው ያለችው የበቀል እርምጃ በሚጠበቅበት ወቅት በሞስኮ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎቿን ለእይታ አቅርባለች።
ለእይታ ከበቁት ውስጥ በራሷ አቅም የተገነባው “ሞሃጀር - 10” የተሰኘ ድሮን ይገኝበታል።
“ሞሀጀር -10” የአሜሪካ ባለስልጣናት ኢራን ለሩሲያ ልካዋለች የሚሉት “ሞሃጀር- 6” ተከታይ ነው።
ግዙፉ ድሮን በሚጓዘው ርቀትም ሆነ በሚሸከመው ተተኳሽ ከዚህ ቀደም ቴህራን ከሰራቻቸው ድሮኖች የተሻለ መሆኑን መኸር የተሰኘው የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ለሩሲያ መላኳ ተገለጸ
“ሞሀጀር -10” 2 ሺህ ኮሎሜትሮችን መጓዝ ይችላል፤ አርፎ ሃይል መሙላት ሳይጠበቅበት 24 ስአት ሙሉ ይጓዛል የተባለለት ድሮኑ 300 ኪሎግራም የሚመዝን ተተኳሽ መሸከም እንደሚችልም ተጠቅሷል።
ቴህራን “ሞሀጀር - 6” ከተባለው ድሮን አንጻር የመጫን እና የመጓዝ አቅሙ በእጥፍ የጨመረውን “ሞሀጀር -10” በሞስኮ ለእይታ ያቀረበችው የመካከለኛው ውጥረት በተባባሰበት ወቅት ነው።
እስራኤል በግዛቴ ውስጥ የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ሃላፊ ኢስማኤል ሃኒየህን መግደሏ ሉአላዊነት እና ክብሬን የተዳፈረ ነው ያለችው ቴህራን አጻፋውን እመልሳለሁ ካለች ሁለት ሳምንታ ተቆጥረዋል።
ከወራት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችና ሮኬቶች ወደ እስራኤል በመተኮስ ያገኘችው ውጤት አመርቂ አለመሆኑም በአሁኑ ወቅት ጊዜ ወስዳ እንድታጤን ሳያደርጋት አልቀረም ይላሉ ተንታኞች።
የኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ከድሮኖች ባሻገር ዘመናዊ የራዳር እና የአየር መቃወሚያ ስርአቶችንም በሞስኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ማቅረቧ የዝግጅቷ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
ከትናንት ጀምሮ ለሶስት ቀናት ክፍት በሆነው አውደርዕይ ላይ የኤሌክትሮኒክ ውጊያ ስርአቶች፣ የአየር እና ባህር ሃይሎች ጸረ ሚሳኤሎች እንዲሁም ባለስቲክ ሚሳኤሎች ለተመልካቾች ክፍት ሆነዋል ነው የተባለው።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ባለፈው ሳምንትም የሀገሪቱ ባህር ሃይል በእስራኤል ላይ ለሚወሰደው እርምጃ ዝግጁ መሆኑንና ከእይታ ተሰውሮ ጥቃት መፈጸም የሚችል ክሩዝ ሚሳኤል መታጠቁን መግለጹ ይታወሳል።
የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ቴህራን የታጠቀቻቸውን አዳዲስ ሚሳኤሎችና ድሮኖች የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል።
13/08/2024
🛢ሊቢያ እና ናይጄሪያ በአፍሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያለቸው ሀገራት ናቸው።
ግሎባል ፋየር ፓወር ያወጣው አዲስ ደረጃ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የተረጋገጠ ወይም በንግድ ሊወጣ የሚችል የነዳጅ ክምችት እንዳላቸው አሳይቷል።
ከፍተኛ ክምችት ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት ከታች የተዘረዘሩት ናቸው፦
🇱🇾 ሊቢያ በ50 ቢልየን በርሜል ክምችት አላት።
🇳🇬 ናይጄሪያ በ37 ቢልየን በርሜል ክምችት አላት።
🇩🇿 አልጄሪያ 12.2 ቢልየን በርሜል ክምችት አላት።
🇦🇴 አንጎላ 7.78 ቢልየን በርሜል ክምችት አላት።
🇸🇩 ሱዳን በ5 ቢልየን በርሜል ከአፍሪካ 5 ደረጃን ይዛለች።
Click here to claim your Sponsored Listing.