ACHE TUBE

ACHE TUBE

Share

25/08/2024

#ነፍስ ይማር

ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራበት ፊልምን ሊያስመርቅ ነው። እናም አባቱን 'ፊልሜን ካላየህ' ይልና ይጨቀጭቃቸዋል። አባት ስራቸው የማያወላዳ ቢሆንም ልጃቸው የፎከረበትን ስራ ሊመለከቱ ሰው ተክተው ፊልሙ ወደሚመረቅበት ስፍራ አመሩ።

ፊልሙ ጀመረ። ጀምሮም አለቀ። አባት ግራ ተጋቡ። ባቡጂ የለበትም።
ወደልጃቸው ዞረው "እሰራበታለሁ አላልክም! የታለህ!?" አሉት።
ባቡጂም "እንዴ አባዬ የሆነ ቦታ ላይ ሁለቴ ያሳልኩት እኔ ነኝ!" ሲል ይመልስላቸዋል። አባት ትክን ይላሉ። እሱን ለማየት ነውና ሰው ተክተው ምርቃት ቦታ የተገኙት። ከመበሳጨታቸው የተነሳ ከምርቃቱ ስፍራ እስከሰፈራቸው ሳያናግሩት ቤት ደረሱ።

ባቡጂ ከ60 በላይ ፊልም ሰርቷል። በብዕር ስም ቢሆንም የጻፋቸው መጽሐፍ አሉት። ድንቅ የኮሜዲ ትወና ብቃት እንዳለውም ይመሰክሩለታል።

ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ውድነህ ክፍሌ ስለጌታቸው እጅጉ(ባቡጂ)

Tube ለባቡጂ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና አድናቂዎች፣ መጽናናትን ይመኛል።

Photos from ACHE TUBE's post 06/09/2022

Ache Tube አዲስ ነገር !

በአጣጥ የኬላ ፍተሻ ላይ 308 ሽጉጥ ተያዘ።

በጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ከተማ 308 የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በኬላ ፍተሻ መያዙን የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አሳውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ሽጉጡ የተያዘው በክፍለ ከተማው በድማዛ ቀበሌ አጣጥ በተባለው የኬላ ፍተሻ መሆኑን ገልጾ 2 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ማለቱን ከጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Photos from ACHE TUBE's post 06/09/2022

በመዲናዋ በጎርፍ አደጋ ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ባለ 2 መኝታ ቤትና 150 ሺህ ብር ተበረከተላቸው

በመዲናዋ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ሁለት ልጆቻቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለ 2 መኝታ ቤትና የ150 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገላቸው፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ÷ "ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው፤ አስተዳደራችን በሚችለው ሁሉ ከጎናችሁ ነው፤ ያጣችኋቸውን ልጆቻችሁን መመለስ ባንችል እንኳን መፅናኛ ይሆናችሁ ዘንድ ይህን ድጋፍ አድርገንላችኋል" ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ÷ ስጦታው ክፍለ ከተማው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ያበረከተው ስጦታ መሆኑን ገልፀው መጭውን አዲስ ዓመት ሀዘናችሁን ቀንሳችሁ ተደስታችሁ መዋል ይገባችኋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሁለት ልጆቻቸውን በጎርፍ አደጋ ያጡት እናት ወይዘሮ ረውዳ ጀማል በበኩላቸው÷ አስተዳደሩ ላደረገላቸው ገንዘብና የቤት ስጦታ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

18
Addis Ababa