Wisdom Tutor in ADDIS
15/11/2022
ፍቅር ቊስል ነው
እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው።
እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል።
እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል።
ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው
ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው።
ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር።
"ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው።
አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው።
ፍቅር ቊስል ነው።
በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።
ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ
"እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው።
እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 10 2011 ዓ ም
አዲስ አበባ
ይህ የዲያቆን ሄኖክ የፌስቡክ ገጽ አይደለም:: ትምህርቶቹን ለማካፈል ብቻ የተከፈተ ነው:: መልእክቶችና ጥያቄዎች ወደ እኛ ባለመላክ ተባበሩን:: የዲያቆን ሄኖክ ትክክለኛ ገጽ ይሄ ነው:: https://www.facebook.com/officialHenokhaile
ለመላው የኢትዮጵያ ተማሪዎች እና ለዚህ የብዙሃን መገናኛ መረብ ተከታዮች እና ተጠቃሚዎች በሙሉ፤ እንደምን አላችሁ? ወቅቱ ለፈተና ማለትም ለሀገር አቀፍ ዩኒቨርስቲ መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ት.ቤት መልቀቂያ ፈተናዎችን ለመወስድ ዝግጃታችንን ጨርሰን እረፍት የምናደርግበት ቢሆንም አሁንም ግን የተለያዩ አመት ጥያቄዎችን እና የመርጃ መጸሀፍት ፈታኝ እወቀቶችን እየሰራን እወቀታችንን የምናጸናበት እንዲሁም ሞራላችንን የምንገነባበት በመሆኑ ግዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም። በዚህ በይነ ገጽ እየደወላችሁ ላላችሁ የcollege እና university ተማሪዎች እንዲሁም ለjunior high school and preparatory ተማሪዎች በሙሉ
ከልብ እናመሰግናለን።!!!
መልካም አዝመራ ይሁንልን።
ከKG እስከ ትላልቅ የትምህርት ተቋማት ላሉ ተማሪዎች ሁሉ የማስጠናት አገልግሎት እንዲሁም ለከፍተኛ ት.ት ተቋማት ት.ት ተማሪዎች Assignment and project ስራን አብረን እንሰራለን።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Addis Ababa