Liyu Mereja

Liyu Mereja

Share

09/07/2026

ለምርቃቱ የተገዛው በሬ ወግቶት ሞተ😭

የሰው ልጅ ህይወትና መጨረሻዋ ምንኛ የማይታወቅና ተለዋዋጭ ነው? ዛሬ በደስታና በፈገግታ የደመቀ ቤት፣ በአንድ ጀንበር የልቅሶና የዋይታ ድምፅ ሲሰማበት ማየት ልብን እጅግ ይሰብራል።

በቅርቡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ (Electrical Engineering) ዘርፍ በታላቅ ስኬት ተመርቆ፣ ለነገው ህይወቱ ትልቅ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ወንድማችን ፍሰሐ አስማማው እጅግ ልብ በሚሰብር አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ስንሰማ የተሰማን ሀዘን ወሰን የለውም።

የነገው የሀገር ተስፋ፣ ለቤተሰቦቹ መከታ እና የብዙዎች ኩራት የነበረው ፍሰሐ፣ የለፋበትን የድካሙን ፍሬ አይቶ ገና ሳይጠግብ እንዲህ በወጣትነቱ መቀጠፉ እጅግ ያማል።

ይህ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ከሳምንት በፊት ነበር የምርቃት ካባውን የደረበው። ወላጆችና ዘመድ አዝማድም የምርቃቱን ደስታ አብረውት ለማሳለፍ ከጎንደር ጋይንት (ጎብጎብ) ከተማ ወደ ተወለደበት አካባቢ ይዘውት አምርተው ነበር።

ነገር ግን በትላንትናው ዕለት ለምርቃቱ ድግስ ተብሎ የተገዛው በሬ በድንገት ወግቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ለአምላክ ምስጋና ይሁን ተብሎ ለደስታ ማክበሪያ የተዘጋጀው በሬ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የቤተሰቡን ተስፋና ደስታ ይዞ ተጓዘ።

የዚህ ወጣት ስኬትና ህልም በአጭር የተቀጨበት አሳዛኝ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በጋይንት ጎብጎብ ቀራኒዮ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የክፍል ጓደኞቹና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተፈፅሟል።

ነፍስህን በአምላክ እቅፍ ይሁንልን🙏

Via _MA

03/07/2026

‎🌎 ዛሬ አርብ የሚደረጉ የ2026ቱ የአለም ዋንጫ ተጠባቂ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች

‎⏱️ 03:00 | 🇦🇺 አዉስትራሊያ ከ ግብፅ 🇪🇬
‎⏱️ 07:00 | 🇦🇷 አርጀንቲና ከ ኬፕ ቨርዴ 🇨🇻
‎⏱️ 10:30 | 🇨🇴 ኮሎምቢያ ከ ጋና 🇬🇭

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Addis Ababa