Dungo Communications
Leenjii
- Kameeraa (kan Footoo, Vidiyoo)
- Editiingii (Kan Footoo, Vidiyoo)
- Filmiingii
Bakka Galmee: M.B. Taaddessa Birruu Sadarkaa 2ffaa
Bilbila - 0912161978
Turtii - Ji'a 3 hanga 6tti
25/05/2020
ይህ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት በየሳምንቱ እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ መልእክት ነው፡፡
የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ዕቅድ መረዳትና በዕቅዱ መመላለስ
/በእግዚአብሔር መንግስት ተለዋጭ መለኮታዊ ዕቅድ የለም፡፡/
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
ኤፌ 2፡10
ክፍል፡ 1
ባለፉት ጊዜያት የሆኑብን ነገሮች ሁሉ አሁን ላለንበት ነገር ትክክል ያልሆነ ውሳኔዎቻችን እንድንወስን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ እንመለከታለን፡፡ በያዕ 3፡2 ያለው የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል እንደሚነግረን… ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና… ይህ ብዙዎቻችን ባፉት ጊዜያቶች በተለያየ መንገድ ስንሰናከል አንደነበረ ይግረናል፡፡ በመክ 7፡20 … ማንም ስህተት ሳይፈጽም ሁል ጊዜ መልካም ነገርን የሚሰራ ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም …. / አመት 1997/ በሮሜ 3፡23 …ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤… ይለናል፡፡
ሉቃ19፡10 … የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።… ባለፉት ጊዜያት በብዙ መንገድ ከጌታ ክብር የጎደልንበት ነገሮች ቢኖሩም ነገር ግን የጌታን ሃሳብ መረዳትና በዚህ ሀሳብ መመላለስ መቻል አለብን፡፡ አንግዲህ የእግዚአብሔር ሀሳብ በእኛ ማንነት የሚቀየር ስላልሆነ የእግዚብሔር ሀሳብ እንዲፈጸም እኛ የሚጠበቅብንን ማድረግ መቻል አለብን፡፡ ባለፉት የህይወት ጉዞዎቻችንና ጊዜያቶች የደረግናቸው ነገሮች ነገሮቻችንን እንዳይያበላሹብን ማድረግ ያለብን ነገር ምንድን ነው?
1. ስላለፈው ውድቀታችን ወይም ስህተቶቻችን ሀላፊነት መውሰድ፡-
በላፉት ጊዜያቶቻችን ለደረሱብን ነገሮች ብዙውን ጊዜ በሌላ ሰው ወይም በሰይጣን ስናሳብብ መኖራችን ይታወቃል፡፡ እውነት ነው ሰዎች ወይም ሰይጣን ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ወሳኙ እኛ ነን ምክንያቱም ያንን ከፊታችን የተጋረጠውን ነገር ማድረግ ወይም አለማድረግ ሃላፊነቱ ያለው በእኛ ስለሆነ፡፡ ሰይጣን ቢሆን መንገድ ስንከፍትለት ነው ስፍራን ሊያገኝ
የሚችለው፡፡ ኤፌ4፡27 የሚነግረን ሰይጣን አይፈትንም ሳይሆን ነገር ግን … ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።… ይህ ክፍል ከሰው ጋር ላለን ጉዳይም የተያያዘ እንደሆነ ያለመክተናል፡ ስለዚህ ዋናው ላለፈው ውድቀት ወይም መሰናክል ሃሳፊነትን መውሰድ ግድ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በተለይ የምንሰናከልባቸው አጋጣሚዎች በማር 14 ላይ ጌታ ኢየሱስ ሁላችሁም በእኔ ትሰናከላላችሁ ብሏል ለምሳሌ ጴጥሮስ የተሰናከለባቸውን አራት ምክንያቶች እንመለከት፡-
1.1. ትዕቢት፡- ትዕቢት ለብዙዎቻችን ድብቅ የሆነ ማንነት ነገር ግን ሰውን ወደከፋ ነገር የሚመራ ሂደት ነው፡፡ ቁ.29 …ጴጥሮስም፦ ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው… ጵጥሮስ ራሱን ከሁሉም እንደበለጠ አድርጎ በማየቱ ነው ይህንን ሊናገር የቻለው፡፡ ነገር ግን ጌታ ትሰናከላለህ ለዚያውም ዶሮ ሳይጮህ 3 ጊዜ ትክደኛለህ አለው፡፡ ነገር ግን የጴጥሮስ ትምክህት ወይም ትዕቢት ወደውድቀት መራው፡፡ … ትዕቢት ከመጣ ውርደት ይመጣል… ምሳ 11፡2 ይህንኑ ይነግረናል፡፡
1.2. ድካም ወይም መጨናነቅ፡- ማር 14 የተፈጸመበት ሁኔታ በጌቴሰማኒ ት እንደሆነ ስንመለከት በዚህ ስፍራ በተለይ ጌታ ኢየሱስ አልፎ ሊስጥበት ባለው ምሽት ነው፡፡ ወደዚህ ስፍራ ከመምጣታቸው በፊት አብረው እራት በልተዋል እግራቸው ታጥበዋል ይህንን ሁሉ ከሆነ በኃላ ነው ወደዚህ ስፍራ የመጡት ስለዚህ ድካም ድካም ብሎአቸው ነበር፡፡ … ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፥ የሚመልሱለትንም አላወቁም።.. ቁ.40 መጸለይ የማይቻል ሰዓት ነው፡፡ ወደፈተና እንዳይገቡ መጸለይ ነበረባቸው ነገር ግን አልቻሉም፡፡ ሁልጊዜ ድካም ሲይዘን መጸለይ ሲያቅተን ፈተናን መወጣት አንችልም፡፡ ብዙዎቻችን እንዲህ ባለ ሰዓት ነው የምንሰናከለው፡፡
1.3. ከርቀት መከተል፡- ከጌታ በራቅን ቁጥር ነገሮች አጥብቀው ይፈትኑናል፡፤ ጌታ ኢየሱስ እንደተናገረው ደቀመዛሙርቱ ወድያው ተበታተኑ ጵጥሮስ ጌታን እከተልሀለሁ እንዳለው ሳይሆን ነገር ግን ከሩቅ መከተል ጀመረ፡፡ አብዛኞቻችን በቤተክርስቲያንም ሆነ በአገልግሎታችን በደረሰብን ነገር የተነሳ ከሩቅ የምንከተል ከሆን ይህም ለመሰናከል ወይም እግዚአብሔር ላየልን ራዕይ እንዳንኖር ያደረገን ውሳኔ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ቁ.54 … ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፥… ፡፡
1.4. ጊዜያዊ ደስታ ላይ ማተኮር፡- ጌታ ኢየሱስ እንደዛ እያነገላቱት እየገረፉት ጵጥሮስ ግን ራሱን ከህዝቡ ጋር አመሳስሎ ነበር ቁ.54… ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር።… ከጠላት ጋር አብሮ ተቀምጦ ነበር ስለዚህም ጌታ እንደተናገረው ጴጥሮስ ጌታን ሲክደው እንመለከታለን፡፡
ጌታ የሚሆነውን ያውቅ ስለነበር ነው ጴጥሮስን አስቀድሞ የነገረው፡፡ የሚገርመው ነገር ግን በሉቃ 22፡31-32 ጌታ አስቀድሞ ጸልዮለት ነበር፡፡ …ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።… ሊቀካህን የሆነው ኢየሱስ ስለእኔና ስለአንተ ይማልዳል፡፡ ጌታ ከዚህ ውድቀት በኃላ ዳግመኛ ተሀድሶ እንዲሆን ነው የነገረው፡፡ ነገር ግን ስለውድቀቱ ብቻ ሳይሆን ከውድቀቱ መልስ ሊሆነው ስለሚገባ ነገር ሲነግረው እንመለከታለን፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሚያጋጥሙን ውድቀቶች የህይወታችን ፍጻሜ አይደሉም ጌታ ባለፍንበት መንገድ ለሌሎች የመነሳት ምክንያት እንድንሆን ዳግመኛ እድል ይሰጠናል፡፡ 2ቆሮ 1፡4 -6
ስለዚህ ባለፉት ጊዜያት የሆነውን ሁሉ በተለይ ለሰራናቸው አስከፊ ነገሮች ወይም መሰናክሎች/ውድቀቶች/ ሃላፊነት መውሰድ ያለብን እኛ ነን፡፡
ይቀጥላል…………….
ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ በአድራሻችን ላኩልን፡፡
ጌታ ይባርካችሁ፡፡
We at urji Communications are great that our works is being liked by many of our people. Thank for liking our pages
Click here to claim your Sponsored Listing.