Ethio Doctors

Ethio Doctors

Share

03/02/2022

Hello guys,
What do you think about our page? We would like to get your reviews on our page and please write the things you want to be improved in the review.

03/12/2021

ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች 8 ምርጥ ምግቦች

1. ገብስ:- ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

2. ባቄላ እና ዘሮቹ:- ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

3. እንቁላል(በመጠኑ):- እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

4. አሳ:- የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

5. የአበሻ አይብ:- የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

6. የወይራ ዘይት:- በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ ዘይት ከፍተኛ anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

7. ስኳር ድንች:- ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው። ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን insulin resistance ይዋጋሉ።

8. ቀይ ስጋ በመጠኑ:- ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

22/11/2021

ኩላሊትዎን ሊጎዱ የሚችሉ 7 ሁኔታዎች

1. በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ - በቂ ውሃን አለመጠጣት የኩላሊት ሥራ የሆነውን አላስፈላጊ ቆሻሻን ከሰውነታችን ማስወገድ በሚገባ እንዳያከናውን ስለሚያደርግ ቆሻሻው በኩላሊታችን ውስጥ ተከማችቶ ጉዳት እንዲያስከትል ያደርጋል፡፡

2. የውሃ ሽንትን መቋጠር - የውሃ ሽንትን ማስወገድ በሚገባን ጊዜ ሳናስወግድ የምንይዘው ከሆነ እና ይህን ተግባር የምናዘወትር ከሆነ የሽንት ፊኛችንም ሆነ ኩላሊታችንን አደጋ ላይ የምንጥል መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

3. ጨው የበዛበትን ምግብ መውሰድ - ጨዋማ ምግቦችን መመገብ የኩላሉትን ጨውን (sodium) ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራ ጫና እንዲበዛበትና ሲቆይም ለችግር እንዲጋለጥ ያደርጋል፡፡

4. ካፊን በብዛት መውሰድ - በሚጠማን ጊዜ ውኃ ከመጠጣት ይልቅ ለስላሳ መጠጦችን እንደ ጥም ቆራጭነት እንጠቀማለን፡፡ ካፌን የደም ግፊት መጠናችንን በመጨመር ኩላሊትን ይጎዳል፡፡

5. ሕመም ማስታገሻ አለአግባብ መውሰድ - ቀላል ለሚባል የሕመም ስሜት ሕመም ማስታገሻዎችን መውሰድ አላስፈላጊ እና አልፎ ተርፎም ከባድ የሆነ የኩላሊት ጉዳትን ሊያደርስ ይችላል፡፡

6. የአልኮል መጠጥን በብዛት መጠጣት - ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥን ማዘውተር የኩላሊት ችግር ያስከትላል፡፡

7. ሲጋራ ማጤስ - ለኩላሊት መድረስ የሚገባውን የደም መጠን ስለሚቀንስ ሲጋራ ማጤስ እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

ሼርርርር

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

St. Nigeria
Addis Ababa
1000