Grand Ethiopian Renaissance Dam,Addis Ababa

Grand Ethiopian Renaissance Dam,Addis Ababa

Share

27/04/2026
Photos from Grand Ethiopian Renaissance Dam,Addis Ababa's post 26/02/2026

ዜና ሹመት
የካቲት 19/2018ዓ.ም
ወ/ሮ መቅደስ አዱኛ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ።
በእለቱም ከቀድሞዋ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት አንቺነሽ ተስፋዬ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል ። ወ/ሮ መቅደስን በጸ/ቤታችን ስም እንኳን ደህና መጡ ለማለት እንወዳለን።

Photos from Grand Ethiopian Renaissance Dam,Addis Ababa's post 26/02/2026

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች ከክ/ከተማ የህዳሴ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን የቀድሞ የጽ/ቤቱን ምክትል ስራ አስኪያጅ የሽኝት መርሃ ግብር አዘጋጁ።
የሽኝት መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ንዒመተላህ ከበደ የቀድሞ የጽ/ቤታችን ም/ስራ አስኪያጅ የነበሩትና አሁን የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራአስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት አንቺነሽ ተስፋዬ በስራ ሂደት ስለነበራቸው የአብሮነት ቆይታ አመስግነው አሁን የተሰጣቸውን ኃላፊነትም በብቃት እንደሚወጡና ብቃት ያላቸው አመራር እንደሆኑ ገልፀዋል። ከክ/ከተማና ከማዕከል የባለሙያ ተወካዮችም በስራ በቆዩበት ወቅት ስለነበራቸው መልካም ግንኙነት አመስግነው መልካም የስራ ዘመን እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን በመግለፅ የሽኝትና የምስጋና መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

06/02/2026

የከተማችንን ጐስቋላ ገፅታ በመቀየር ውብ፣ ፅዱ እና አረንጓዴ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጐብኝዎች ሳቢና አለማቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን በ24/7 የስራ መርሀ ግብር ሰርተን ውጤት ያስመዘገብንበት ነው ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

05/02/2026

“በአፍሪካ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም የውሃ ታሪፍ በማቅረብ ረገድ ኢትዮጵያ በየጊዜው በአንደኝነት ትጠቀሳለች!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Mayor Office
Addis Ababa
1000