Shop in ethio

Shop in ethio

Share

17/05/2018

ኃያላን ቀስት ተሰባብሮ
አለቅነትን ስልጣናትን ሽሮ
በግርማው ያለ ሁሉን እየረታ
ዛሬም ይገዛል የጌቶች ጌታ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ

ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው
መንግሥቱም ጽኑ ነው ማንም አይረታው
የተነሱበትን ሁሉንም ገልብጦ
ብቻውን ይገዛል እርሱ ብቻ ጸንቶ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ

ጐርደድ እያለ ከጠላት ሰፈር
ሺ ጦር ቢሰለፍ የማይበገር
ድምጹ ነጐድጓድ የሚያስፈራራ
ሁሉን የረታ ተራ በተራ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ

ነጉሰ ነገሥት ግርማዊ ተብለው
በምድር ሲኖሩ ክብርን ተጋፍተው
ዛሬ ተረስተው አፈር ሆነዋል
ሞትን ፈንቅሎ ኢየሱስ ግን ተነስቷል

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ

ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው
መንግሥቱም ጽኑ ነው ማንም አይረታው
የተነሱበትን ሁሉንም ገልብጦ
ብቻውን ይገዛል እርሱ ብቻ በልጦ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ (፪x

16/04/2018

GOD IS LOVE ALL THE TIME

18/01/2018

(ወደ ሮሜ ሰዎች �?ዕራ�?? 12)
----------
1፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።

2፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

3፤ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።

4፤ በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥

5፤ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።

6፤ እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤

7፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤

8፤ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።

9፤ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤

10፤ በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤

11፤ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤

12፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤

13፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።

14፤ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ።

15፤ ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።

16፤ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።

17፤ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።

18፤ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።

19፤ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

20፤ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።

21፤ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

02/01/2018

ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት መቼም ቅርብ ይገኝ
እንዴት ተገኘ ብዬ አያስደንቀኝ
ስለ ቸር ሰው ቢሆን እንደዚሁ ነኝ እኔ
ጊዜዬን በዚህ አልፈጅም ለምኔ ለምኔ
አንድ ነገር አለ እኔን ያስደነቀኝ
ደካማ እያለሁ ሳላውቀዉ ያወቀኝ
ሃጥያት ያራቀኝ ከመንገድ አውጥቶ
ኢየሱስ መለሰኝ ሞቴን ሁሉ ሞቶ አሃ

አዝ፦ እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (፪x)

በአንዷ አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጥያተኛ ሆኑ [1]
ከዲያብሎስ ጋራ ገሃነም ሊጣሉ
በኢየሱስ መታዘዝ ከፍርድ አምልጠናል [2]
የመንግሥተ ሠማይ ወራሽ አድርጐናል

አዝ፦ እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (፪x)

ዝቅ ዝቅ ያለው ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል
ለእኔ ባረገው ነገር ልቤ ተሸንፏል
የፍቅርንም ሚስጥር ያወኩት በእርሱ ነው
አቀብት ዳገቱን የወጣዉ ለእኔ ነው
በደሙ ተድቄ ከቁጣ ድኛለሁ
ጠላትነት ቀርቶ ወገን ተብያለሁ
ሰላሙን ሰብኮኛል የሰላም አለቃ
የጭንቀቱ ዘመን ከእኔ ላይ አበቃ አሃ

አዝ፦ (እንዴት ያለ ፍቅር ነው)
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (

Want your business to be the top-listed Clothing Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa