Odeeffannoo press

Odeeffannoo  press

Share

Photos from Odeeffannoo  press's post 30/09/2025

የኢሬቻን ሀገራዊ እሴቶች ጥንካሬ በትውልዱ ውስጥ በማስረጽ እያጠናከሩ መሄድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2018

የኢሬቻን ሀገራዊ እሴቶች ጥንካሬ በትውልዱ ውስጥ በማስረጽ እያጠናከሩ መሄድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሃይሉ አዱኛ ተናገሩ።

"ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረውን የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ላይ ያተኮረ 'ጉሚ በለል' የውይይት መድረክ በክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት እና በኮሙኒኬሽን ቢሮ ትብብር ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ቢሮው ኃላፊ ሃይሉ አዱኛ፤ የገዳ ስርዓት ትሩፋት የሆነውን የኢሬቻ በዓል የበለጠ ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።

ኢሬቻ ከሰላም፣ እርቅ እና አንድነት ጀምሮ በሀገር ግንባታ እና ህብረ ብሔራዊ እንድነትን ከማጠናከር አንጻር በርካታ ሀገራዊ እሴቶች ያሉት መሆኑን ተናግረዋል።

እነዚህን እሴቶች በጎ አስተዋጽኦ የበለጠ በማጠናከር ለትውልድ ግንባታ ማዋል እንደሚገባ አመልክተው ለዚህም ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የኢሬቻ በዓል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ በዓል መሆኑን አንስተው፤ የዘንድሮው ኢሬቻ በተሻለ መልኩ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

በመድረኩ ላይ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የገዳ ትምህርት መምህር መሐመድ ነሞ(ዶ/ር)፣ ኢሬቻ የበለጠ እንዲያድግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመክተዋል።

በዓሉን ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ በቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ የገቢ ምንጭ ማድረግ እንዲቻል የባለድርሻ አካላት ሚናም ማደግ እንዳለበት አስረድተዋል።

በባህልና ቋንቋ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችም የበዓሉን በጎ ገጽታ ማጉላት የሚያስችሉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነው ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም ህብረትና ትስስር የሚያጠናክርበት ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ የኢሬቻ በዓል አብሮነት፣ ይቅርታ፣ እርቅ፣ አንድነትና መተባባር የሚጎለብትበት መሆኑን ጠቅሰው የተጀመረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ እውን ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ኢሬቻ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

04/09/2025

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሃብት እንዲጨምር አስችሏል-ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሃብትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ስኬት የተመዘገበበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጎርፍን በመከላከል በውሃ የሚወሰድ አፈርና ደለልን በመቀነስ ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው።

መርሃ ግብሩ በውሃ ሀብት ላይ ያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ በቅርቡ በተካሔደ ጥናት የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ መረጋገጡን ጠቅሰዋል።

የዋና ዋና ወንዞችና የጅረቶች የውሃ መጠን መጨመሩንም ተናግረዋል።

ጥናቱ በሐዋሳ ዙሪያ፣በዓባይ እና አዋሽ ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ መካሄዱን ጠቅሰው፥ በእነዚህ አካባቢዎች ችግኞች ከመተከላቸው በፊትና ከተተከሉ በኋላ የታየው ተጨባጭ ለውጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መረጋገጡን አንስተዋል።

በዚህም የአረንጓዴ አሻራ አካባቢውን አረንጓዴ ከማድረጉ ባለፈ በዝናብ ወቅት ሊፈጠር የሚችል ጎርፍ እንዲቀንስና የዝናብ ውሃ ወደ መሬት እንዲሰርግ ማድረጉን በተግባር አረጋግጠናል ነው ያሉት።

በዋናነት የተተከሉት ችግኞት የተጎዱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ እና የጎርፍ መጠን እንዲቀንስ ከማድረግ ባሻገር የከርሰ ምድር ውሃን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ነው ያሉት።

ደርቆ የነበረው የሐሮማያ ሐይቅ መልሶ ያንሰራራው በአረንጓዴ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ሥራ መሆኑን በማንሳት፥ የአረንጓዴ አሻራ ምንጮች እንዲጎለብቱ በማድረግ የውሃ ፍሰትን ለማስተካከል ማስቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች ጎርፍን በመከላከል አፈር እንዳይሸረሸር፣ ግድቦችና ወንዞች በደለል እንዳይሞሉና ንጹህ የውሃ ሀብት እንዲኖር በማድረግ ትልቅ ለውጥ ማመጣታቸውንም ገልጸዋል።

02/09/2025

ታሪካዊ ከፍታ ላይ የሚገኘው የሩሲያ እና ቻይና ግንኙነት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከቻይና ጋር ያላት ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ታሪካዊ ከፍታ ላይ እንደሚገኝ ተናገሩ።

የሩሲያ እና ቻይናን ትብብር ለማጠናከር ያለመ የዓለም አስተዳደር ኢኒሼቲቭ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህ ከሻንጋይ ትብብር ፎረም ማግስት በቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዛሬ ይፋ በሆነው በዚህ መድረክ የተሳተፉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ ሀገራቸው ከቻይና ጋር ወዳጅ መሆኗን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግን “የረጅም ጊዜ ጓደኛየ’ ሲሉ ስላላቸው ወዳጅነት ገልጸዋል።

የቻይና እና ሩሲያ ግንኙነት በዓለም አቀፍ ጫናዎች ሳይበገር በታሪካዊ ከፍታ ላይ ይገኛል ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ የሀገራቱ ግንኙነት በዲፕሎማሲያው ዓለም የጠንካራ ግንኙነት ምሳሌ መሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው÷ ሁለቱ ሀገራት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረውን የባለ ብዙ ዋልታ የዓለም አስተዳደር ስርዓትን ለማስጠበቅ በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ከሩሲያ ጋር ትናንት አብረን ነበርን፣ ዛሬም አብረን ነን፣ ትብብራችን ለወደፊትም ይቀጥላል ነው ያሉት።

የሀገራቱ ግንኙነት ከሩሲያ ዩክሬኑ ጦርነት በኋላ የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በሁለትዮሽ ትብብሮች እንዲሁም በደቡብ ለደቡብ ትብብር እና ብሪክስ ማዕቀፎች በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ የሆነችው ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ 240 ቢሊየን እንደሚደርስ ቢቢሲ እና አናዶሉ ዘግበዋል፡፡

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa