Aloe cosmo distributor
01/04/2016
ለወዛማ ቆዳ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
ወዛማ ፊት ወዝ አመንጪ እጢዎች በርከት ያለ ዘይት ያመነጫሉ፡፡ይህ በተፈጥሮ የሚወሰን ስለሆነ ሁኔታዉን መለወጥ አይቻልም፡፡
መፍትሄዉ ከተቻለ ለወዛማ ፊት በተዘጋጀ ዘይትአልባ ሳሙና ወይም የፊትን ወዛማነት የሚቀንስ ፈሳሽ የፊት ማጽጃ በመጠቀም ፊትን ማጠብ ይህም ካልሆነ ለብ ባለ ዉሀና በሳሙና መታጠቡ ጠቃሚ ነዉ፡፡ብዙ ጊዜ በ እኟ ሀገር ብዙ ሰዎች ባለማወቅ ቫዝሊን ሆነ ሌላ ቅባት መቀባት ለቆዳ ጠቃሚ ስለሚመስላቸዉ አዘዉትረዉ ይቀባሉ፡፡ይህም ወዛም ፊት ያላቸዉ ሰዎች ለከፋ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ሊወገድ የሚገባ ልማድ ነዉ፡፡እንዲሁም ወዛም ቆዳ ያላቸዉ ቅባታማ የፊት ክሬም ሆነ ስክራብ ፈጽሞ መጠቀም የለባቸዉም፡፡
ብዙውቻችን ጸጉራችንን ማሳገድ እጅግ ፈታኝ እና በዙ ጊዜ ሲወስድብን እናሰተውላለን።
እኛም ለዛሬው በቀላሉ እንቁላልን በመጠቀም እንዴት ጸጉርን ማሳደግ እና መንከባከብ ይቻላል የሚለውን ልናካፍላችሁ ወደድን።
እንቁላል ለጸጉር እድገት አስፈላጊ የሆነውን ፕሮቲን በውስጡ በመያዙ ጸጉራችንን በቀላሉ ሊያሳድግልን ይችላል ተብሏል።
b05470764b8a232808e357228e6a8827_L
አዘገጃጀት
• በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ሁልት እንቁላል ሰብረን በመጨመር አዛ ውስሁጥ ሁለት የሾርባ ምንኪያ የወይራ ዘይት ቀላቅለን በደንብ አንድ ላይ ማዋሃድ።
አጠቃቀም
• ጸጉራችንን በሻምፖ ወይም በሳሙና በማደረግ በደንብ መታጠብ።
• የታጠብነውን ጸጉር በፎጣ ተጠቅመን ማድረቅ።
• በመቀጠልም የደረቀው ጸጉራችን ላይ ያዘጋጀነውን የእንቁላል ውህድ ሙሉ በሙሉ መቀባት፥ አዚህ ጋር ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር የጸጉራችን ጫፎች ሳይቀር ሙሉ በሙሉ የእንቁላሉ ውህድ ተዳርሶ መቀባት አለበት።
• የተቀባነውን የእንቁላል ውህድ በሻወር ኮፍያ ወይም በፔስታል ጠቅልለን በማሰር ከ10 እስከ 20 ደቂቃ ማቆየት።
• የመታጠቢያ ሰዓታችን እንደደረሰም ጸጉራችን ሙሉ በሙሉ በኮንዲሺኘር በማደርግ መታጠብ ይኖርብናል።
ማሳሰቢያ፦
• የተቀባነውን እንቁላል ከ20 ደቂቃ በላይ በጸጉራችን ላይ ማቆየት የለብንም ምክንያቱም እንቁላሉ በቆየ መጠን ጸጉራችንን ከመጥቀም ይልቅ ጉዳት ስለሚያስከትል።
• ይህንን የእንቁላል ውህድ በወር አንድ ጊዜ ብቻ መጠቅም በቂ ነው።
በእንቁላልን በዚህ መልኩ በመጠቀምም ጸጉራችን በቃሉ እንዳይበጣጠስ፣ ወዙን የጠበቀ እና ቶሎ እንዲያድግ ማድረግ እንችላለን።
በተጨማሪም ጸጉራችንን በምንታጠብበት ጊዜ ኦርጋኒክ የሆኑ እንቁላል ትሪትመንቶችን መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.