Melos Tube
Melos tube:
#ሜሎስትዩብ
ቤርሙዳ(ትንሹ ሲኦል)
ክፍል 1
የነበርኩበት ቤት ለቅቄ አሁን እየፃፍኩለት ለሚገኘው ሰፈር ነዋሪነቴን አንድ ብዬ ሳስመዘግብ እጅግ በጣም ነበር የፈራሁት። የሰዎች ትርምስ የሆቴሎች ብዛት እረ ባጠቃላይ ሁሉም ነገር ያስፈራ ነበር ግን ከታገሱት ማይለመድ ነገር የለም ሁሉንም ለመድኩት እንቅልፍ አላስተኛ ይለኝ የነበረው ሙዙቃ
ለመውጣት ሲያስፈራኝ የነበረው ጨለማ
ቀና ብዬ ለማየት እፈራቸው የነበሩ ሴቶችን ተላመድኳቸው ሕይወት በቤርሙዳ ያስፈራል ለኔ ሳይሆን ሕይወታቸውን ከዚህ ሰፈር ጋር ላያያዙት ሴቶች ያስፈራል ቤርሙዳ ቀንም ማታም ብርሀን ነው። አብዛኞቹ ሴቶች ማታ ንቁ ሆነው ለማማለል ቀኑን በመቃም ነው የሚያሳልፋት።
ምሽት 1:00 ሲል ቤርሙዳ ይደምቃል ይቀውጣል ከተለያዩ ቦታ ወደ አፍንጫ እየተገፋ በአየር ግፊት የሚመጣው ሽቶ ያውዳል omg ጥቅሻው ልብ ️ያደነዝዛል ቀኑን በምርቃና ተለጉመው ሲውሉ የነበሩ ሴቶች ማታ አምረው ተውበው የሚያጠምድትን ወንድ ይጠባበቃሉ። መንገድ መጣበብ ይጀምራል ወንዶች ለሴቶች ይለቁላቸዋል። ስትሬቶች (መንገድ ዳር የሚቆሙ) ሴቶች የመንገድ ባለቤት ይሆናሉ። በቃ አሳልፈን ብትል እናትህ ብን...........ግ.....ም..ሸ..... ወዘተ የሚሉትን ስድቦች ከየአቅጣቻው ይወረወርብሀል እድለኛ ከሆንክ ደሞ አሪፍ ጥቅሻ ከአሪፍ ፈገግታ ጋር ተቀብለህ ትሄዳለክ ወይ ትጠመዳለክ ወይኔ ከተጠመድክ ጃሉድን ስማው
#እንዲያውነገርቢያስቸግር
#እንዳትረሳያቺንነገር
#አዎአስታውስ.....
ይቀጥላል ከተመቻችሁ አስተያየት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa