EBC Fact Check
21/05/2026
የገንዘብ ሚኒስቴርን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው
*******************
ከሰሞኑ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የገንዘብ ሚኒስቴርን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ማንኛውንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የተመለከቱ መረጃዎችን በራሱ ማህበራዊ ሚድያዎች እና ከትክክለኛ የመረጃ ምንጮች ላይ የሚያወጣ መሆኑን በመግለፅ ሕብረተሰቡ ከመሰል አሳሳች መረጃዎች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
Ethiopian Broadcasting Corporation
18/04/2026
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!
************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሀሰተኛ ድረ-ገፅ ለማጭበርበር ተግባር እየዋለ መሆኑን በመግለጽ ደንበኞቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
አጭበርባሪዎች htttps://reneewu.site/? # # #, htttps://peeryd.site የመሳሰሉ ሀሰተኛ ድረ-ገፆችን በመፍጠር እንደ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ በመሳሰሉ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እያሰራጩ እና ከታች በምስሉ እንደሚታየው የሲቢኢ ብር መተግበሪያን አስመሰለው ሀሰተኛ ድረ-ገፅ በመፈብረክ እንደ ስልክ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል፣ ለማረጋገጫነት የሚላከውን የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (One-time password (OTP)) የመሳሰሉ የደንበኞችን ምስጥራዊ መረጃዎች በመመንተፍ ጥቃት በማድረስ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል ብሏል ባንኩ።
👉 የማጭበርበር ተግባሩ እንዴት ይፈፀማል?
ደንበኞች በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሼር የተደረጉ ሊንኮችን (ማስፈንጠሪያዎችን) ሲከፍቱ ወደ ሀሰተኛ የሲቢኢ ብር ድረ-ገፅ በማሻገር የስልክ ቁጥር እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ።
በመቀጠል ምስጥራዊ የይለፍ ቃል(PIN) እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTP) እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ።
ጥቃቱ የሚጀምረው የስልክ ቁጥርዎንና የይለፍ ቃልዎን ሲያስገቡ፣ ጥቃት አድራሾች በትክክለኛ ሲቢኢ ብር መተግበሪያ ላይ እርስዎ ያስገቡትን ወዲያውኑ በመመንተፍ ትክክለኛ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል በስልክዎ በማስላክ ይጠባበቃሉ።
እርስዎ በፍቃድም ይሁን አውቶማቲክ ሲያረጋግጡ የሲቢኢ ብር ሂሳብዎን ጥቃት አድራሾች (ጠላፊዎች) ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራሉ።
ከዚህ በኋላ ጥቃት አድራሾች የሚፈልጉትን ያልተፈቀደ ግብይት በአጭር ኮድ (*847 #) መፈጸም ያስችላቸዋል።
በመሆኑም መሰል ዘዴዎችን በመጠቀም ጥቃት አድራሾች የማጭበርበር ተግባር እየፈጸሙ እንደሚገኙ እና ባንኩ የሲቢኢ ብር አገልግሎትን በድረ-ገፅ እንደማይሰጥ በመገንዘብ ደንበኞች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባንኩ አሳስቧል።
በተጨማሪም በተመሳሳይ የማጭበርበር ተግባር ተሳስታው ምስጢራዊነት ያላቸውን መረጃዎች የሰጡ ደንበኞች በአስቸኳይ ከስልካቸው ጋር የተገናኙ የባንክ ሂሳቦችን በንቃት መከታተል እና የይለፍ ቃል መቀየር እንዳለባቸው ጠቁማል።
👉 ደንበኞች ከዚህ መሰል ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል ምን ማድረግ አለባቸው?
✅ እንደ አሻራ (Biometrics) ያሉ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication) መጠቀም።
✅ በማህበራዊ ሚዲያ የሚላክ ማስፈንጠሪያም (suspicious links) ሆነ ፋይል (Attachment) ሳያረጋግጡ ከመክፈት መቆጠብ፣
✅ የምንጠቀማቸውን ሶፍትዌሮች እና ሥርዓቶች በመደበኛነት ማዘመን፣
✅ ደህንነታቸው ባልተረጋገጠ ቻናሎች ምስጢራዊነት ያላቸውን መረጃዎች ከማጋራት መቆጠብ፣
✅ የይለፍ ቃልን በጥንቃቄ መያዝ፣ ለማንም አለማጋራት፣
✅ የባንክ መግለጫዎችዎን እና የግብይት ታሪክን በመደበኛነት መከታተል፣
✅ ማንኛውንም አጠራጣሪ ወይም ያልተፈቀዱ ግብይቶች ሲያስተውሉ ወዲያውኑ ወደ 951 በመደወል ማሳወቅ።
#ለጥንቃቄ #ኢቢሲ #ሲቢኢ
04/04/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኅብረተሰቡ ከሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ አሳሰበ
********************
ኅብረተሰቡ ከሐሰተኛ ዜናዎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭት ራሱን እንዲጠብቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አሳስቧል።
ጽ/ቤቱ ቤቱ ባስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት፣ “ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተብሎ የሚደርስዎትን ማንኛውም ይፋዊ መልዕክት ከማጋራትዎ በፊት ሁልጊዜም በጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች እና ድረ-ገጽ በመግባት፣ ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን” ብሏል።
Ethiopian Broadcasting Corporation
01/04/2026
#ለጥንቃቄ
በቲክቶክ አካውንቶች ላይ ያነጣጠረ የሳይበር ጥቃት ዘመቻ መከፈቱ ተነገረ
በቅርቡ የወጡ የሳይበር ደህንነት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የሳይበር ወንጀለኞች የቲክቶክ ለንግድ (TikTok for Business) አካውንቶችን ለመዝረፍ የሚያስችል አዲስና ውስብስብ የማጭበርበሪያ (Phishing) ጥቃት ሰንዝረዋል።
ፑሽ ሴኪዩሪቲ ( ) የተባለው የደህንነት ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ጥቃቱ በተለይ የቲክቶክ እና የጎግል መልዕክቶችን በሚመስሉ የሐሰት ገጾች አማካኝነት የሚፈጸም መሆኑን ገልጿል።
ይህ አደገኛ የሳይበር ጥቃት በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች የሚከናወን ሲሆን፤ እነርሱም፦
፦ መጀመሪያ "የሥራ ዕድል አለ" የሚል ማራኪ መልዕክት በኢሜይል አማካኝነት ለተጠቃሚዎች ይላካል።
፦ ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ፣ የቲክቶክ ወይም የጎግል መግቢያ ገጽን በትክክል የሚመስል ነገር ግን የሐሰት የሆነ ገጽ ይከፈትላቸዋል።
፦ ተጠቃሚው በዚያ ገጽ ላይ የተጠቃሚ ስምና የይለፍ ቃሉን (Password) ሲሞላ፣ መረጃው በቀጥታ በወንጀለኞቹ እጅ ይገባል።
ተጠቃሚዎች ከዚህ ጥቃት ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ ይመከራል፦
👉አጠራጣሪ ሊንኮችን አይጫኑ፦ ከማያውቁት ሰው በኢሜይል የሚላኩ "የሥራ ዕድል" ወይም "ሽልማት" የሚሉ ሊንኮችን በፍጹም አይጫኑ።
👉የድረ-ገጹን ስም ያረጋግጡ፦ ማንኛውንም መረጃ ከመሙላትዎ በፊት የሚገቡበት ድረ-ገጽ ትክክለኛው የተቋሙ አድራሻ (URL) መሆኑን በደንብ ያረጋግጡ።
👉ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ፦ ማንኛውንም የይለፍ ቃል ከመሙላትዎ በፊት ገጹ ትክክለኛ መሆኑን ደግመው ያረጋግጡ።
13/02/2026
#ለጥንቃቄ
የሳይበር ወንጀለኞችን የዝርፊያ ስልት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረው አዲሱ አደገኛ ሶፍትዌር
በቅርቡ የወጡ የሳይበር ደህንነት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ ወርልድ ሊክ (World Leaks) የተሰኘውና በመረጃ ምንተፋ ላይ የተሰማራው አደገኛ የሳይበር ወንጀለኞች ቡድን፣ 'RustyRocket' የተባለ አዲስ አጥፊ ሶፍትዌር (Malware) በስራ ላይ ማዋሉ እየገለጹ ይገኛሉ።
ይህ ማልዌር ቀደም ሲል ከታዩት ተመሳሳይ የጥቃት አይነቶች በተለየ መልኩ እጅግ ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ቋንቋ (Rust) የተገነባ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በኩባንያዎች የውስጥ ኔትዎርክ ውስጥ ሳይታወቅ ተሸሽጎ በመቆየት እጅግ ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን መስረቅ መቻሉ ነው።
አክሴንቸር (Accenture) የተባለው የደህንነት ተቋም እንዳረጋገጠው፣ ይህ እጅግ ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ቋንቋ የሳይበር ወንጀለኛ ቡድኑ መረጃን ተቋማትን ወይም ግለሰቦችን የማስፈራራትና ገንዘብ የመዝረፍ (Extortion) ተግባር ወደ ላቀ ደረጃ እንዳሸጋገረው ጠቁሟል።
ይህ 'RustyRocket' የተባለው ማልዌር እጅግ አደገኛ የሚያደርገው አንዱ ባህሪው፣ መረጃዎችን የሚሰርቅበት መንገድ እጅግ ረቂቅና ብዙ የደህንነት ደረጃዎች ያሉት መሆኑ ተገልጿል።
ማልዌሩ በዊንዶውስ እና በሊኑክስ ኮምፒውተሮች ላይ እኩል የመስራት ብቃት ያለው ሲሆን፣ የሚሰርቃቸውን መረጃዎች ደግሞ እንደ መደበኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም በማስመሰል (Proxying) ወደ መረጃ ጠላፊዎቹ መቆጣጠሪያ እንደሚልካቸው ታውቋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ማልዌሩ ስራ ከመጀመሩ በፊት ልዩ የሆነ ሚስጥራዊ ኮድ እንዲሰጠው ስለሚጠይቅ፣ የደህንነት ባለሙያዎች ሶፍትዌሩን ወስደው ላቦራቶሪ ውስጥ እንዳይመረምሩትና እንዳያመክኑት ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
የዚህ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል ዝነኛው የናይኪ (Nike) ኩባንያ አንዱ መሆኑ ተገልጿል።
ጠላፊዎቹ ከኩባንያው የውስጥ መረጃ ማከማቻ ላይ ከ188,000 በላይ ፋይሎችን የሰረቁ ሲሆን፣ ናይኪ የተጠየቀውን የገንዘብ ክፍያ ባለመክፈሉ ምክንያት መረጃዎቹ በይፋ እንዲለቀቁ ተደርገዋል።
እንደነዚህ ያሉ ጥቃቶች የሚያሳዩት፣ ጠላፊዎች አሁን ላይ መረጃን ከመቆለፍ ይልቅ መረጃን ሰርቆ በማውጣትና "ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን" በሚል ዛቻና ማስፈራሪያ ኩባንያዎችን ማስጨነቅ ላይ እያተኮሩ መሆኑን ያሳያል።
ተቋማት ራሳቸውን ከዚህ አዲስ አደጋ ለመጠበቅ ከተለምዷዊ የመከላከያ ዘዴ መውጣት እንደሚገባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ተቋማት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል የኮምፒውተር መረባቸውን በክፍሎች በመከፋፈል የጠላፊዎችን እንቅስቃሴ መገደብ፣ ያልተለመደ የመረጃ ፍሰትን በንቃት በመከታተል ስርቆት ሲጀመር በቶሎ መለየት፣ እና ሰራተኞቻቸው በአጠራጣሪ መልዕክቶች እንዳይታለሉ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የጥቃቱን በር አስቀድሞ መዝጋት ይኖርባቸዋል።
06/02/2026
‘ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች’ በሚል በርካቶችን ያሳሳቱት ሐሰተኛ የኤአይ ቅንብሮች
*******
በቅርብ ጊዜ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ‘ቫለሪያ’ እና ‘ካሚላ’ በሚል ስም የሚጠሩ መንትዮች ታሪክ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
መንትዮቹ በአካል ተጣብቀው የተወለዱ (Conjoined twins) መሆናቸውንና በአሜሪካ ማያሚ እንደሚኖሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፅ ቢገልጹም፣ የተደረገው ማጣራት ግን ጉዳዩ ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጧል።
ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮችን በመምሰል በተከፈተው በዚህ ገጽ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ተከታዮችን ማፍራት የተቻለ ሲሆን፣ ምስሎቹም እጅግ እውነተኛ ይመስሉ እንደነበር በርካታ መገናኛ ብዙኃንም ዘግበዋል።
ሆኖም የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ምስሎቹን መርምረው እንደገለጹት፤ እነዚህ መንትዮች በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የተፈጠሩ የምስል ቅንብሮች እንጂ እውነተኛ ሰዎች አይደሉም።
በምስሎቹ ላይ የሚታዩ አንዳንድ ጥቃቅን የቴክኒክ ስህተቶች፣ በተለይም የጣቶች ቁጥር መብዛትና የጀርባ ገጽታዎች መዛባት ምስሎቹ በቴክኖሎጂ የተቀነባበሩ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
መንትዮቹ በማኅበራዊ የትስስር ገፅ ላይ "እውነተኛ ሰዎች ነን" የሚል ክርክር ቢያቀርቡም፣ የዲጂታል ምርመራ ውጤቶች ግን ምስሎቹ ‘ዲፕ ፌክ’ (Deepfake) መሆናቸውን አሳይተዋል።
ጉዳዩን የታዘቡ ብዙዎች የሰዎችን አካል ጉዳት ለንግድ ማስታወቂያነትና ለተከታይ ማፍሪያነት መጠቀም ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ድርጊቱን እየተቹት ይገኛሉ።
ይህ ክስተት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እውነትንና ሐሰትን መለየት እስከሚያቅተን ድረስ እየረቀቀ መምጣቱን የሚያሳይና ማኅበረሰቡ በማኅበራዊ ገጾች የሚመለከታቸውን መረጃዎች በጥንቃቄ መመርመር እንዳለበት ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል።
በሜሮን ንብረት
29/01/2026
ለዲጂታል ምዝበራ በር እየከፈተ ያለው የግንዛቤ እጥረት
*****************
በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ አገልግሎቶች መስፋፋታቸውን ተከትሎ፣ ከግንዛቤ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችና ምዝበራዎች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑ ተገለጸ።
ዜጎች ለማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ለባንክ መተግበሪያዎቻቸው የሚሰጡት የደህንነት ጥንቃቄ አናሳ መሆን ለጥቃት ተጋላጭነታቸውን እንዳሰፋው ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር መከላከል ዳይሬክተር መሐመድ ፈረጃ ተናግረዋል።
በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ መድረኮች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
ዜጎች ለዲጂታል ደህንነታቸው የሚሰጡት ትኩረት አናሳ መሆን ለምዝበራው ዋነኛ መንስኤ መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ ለኢቲቪ ዜና የገለጹት።
ጥቃቶቹ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጥቅሞችን ባነገቡ አካላት የሚሰነዘሩ ሲሆን፣ ድንበር ተሻጋሪ መሆናቸው ደግሞ ወንጀለኞቹን በሕግ ቁጥጥር ስር ለማዋልና ለተጠቂዎች ፍትሕ ለማሰጠት ተግዳሮት ሆኗል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ዜጎች መተግበሪያዎችን በየጊዜው ካለማሻሻል ባለፈ፣ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) አለመጠቀማቸው ለጠላፊዎች ትልቅ እድል እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።
ተጠቃሚዎች ከምዝበራ እንዲጠበቁ አስተዳደሩ የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲተገብሩ አሳስቧል፦
• የምስጢር ኮድ ጥንቃቄ፦ በስልክ የሚደርስ ማንኛውንም ምስጢራዊ ኮድ (OTP) ለማንም አካል አለመስጠት።
• አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት፦ በሽልማትና በተለያዩ ስሞች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን ፈጽሞ አለመክፈት።
• የሁለትዮሽ ማረጋገጫ፦ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን (Two-Step Verification) ተግባራዊ ማድረግ።
• ሪፖርት ማድረግ፦ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ ሪፖርት እና ማገድ (Block) ማድረግ።
አፎሚያ ክበበው
ተጨማሪ የኢቢሲ ዶትስትሪም የዲጂታል አማራጭ አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-
26/01/2026
#ለጥንቃቄ
በ2026 የሳይበር ደህንነት ትልቁ ስጋት
*****************
"የአቅርቦት ሰንሰለት ጥቃት" ምንድን ነው?
የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነታችን በጨመረ ቁጥር ሌቦችም ስልታቸውን እየቀየሩ ነው። አሁን ላይ ተቋማት የውስጥ ደህንነታቸውን አጥብቀው ስለያዙ፣ ጥቃት ፈጻሚዎች በአቋራጭ መንገድ መግባት ጀምረዋል። ይሄም የአቅርቦት ሰንሰለት ጥቃት (Supply Chain Attack) ይባላል።
ለመሆኑ ይሄ ጥቃት እንዴት ነው የሚከሰተው?
ጥቃቱ የሚፈጸመው በአንድ ተቋም ላይ በቀጥታ ሳይሆን፣ ተቋሙ በሚጠቀምባቸው አቅራቢዎች (ሶፍትዌር፣ ሃርድዌር ወይም ሌሎች አገልግሎቶች) ላይ ነው። ሌቦቹ "አጥር ሰብሮ ከመግባት ይልቅ፣ ቁልፍ ያለው ሰው ላይ ጥቃት ማድረስ ይቀላል" በሚል መርህ ይሰራሉ።
ዋና ዋና የጥቃቱ አይነቶች፦
በሶፍትዌር በኩል፦ በምንጠቀምባቸው ሶፍትዌሮች ወይም አፕሊኬሽኖች ማዘመኛ (Update) ውስጥ ተንኮል-አዘል ኮድ በመክተት የሚደረግ ስርቆት ነው።
በሃርድዌር በኩል፦ የምንጠቀማቸው ስልኮች፣ ኮምፒውተሮች ወይም ራውተሮች ገና ተመርተው ወደ እኛ ሳይደርሱ፣ በውስጣቸው የድብቅ መግቢያ (Backdoor) በማዘጋጀት የሚደረግ ጥቃት ነው።
በአገልግሎት አቅራቢዎች በኩል፦ ለብዙ ድርጅቶች የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚሰጡ የውጭ ተቋማትን በመጥለፍ፣ በአንዴ የሁሉንም ደንበኞች መረጃ መቆጣጠር ነው።
መፍትሄው ምንድን ነው?
የምንጠቀማቸውን ሶፍትዌሮችና መሣሪያዎች ምንጭ ማረጋገጥ።
የአቅራቢዎቻችንን የደህንነት ጥንካሬ በየጊዜው መፈተሽ።
"ታማኝ ነው" ብለን የምንጠቀመው ማንኛውም መሣሪያ ወይም ሶፍትዌር የደህንነት ክፍተት ሊኖረው እንደሚችል ማሰብ።
የሳይበር ደህንነት የሁላችንም ኃላፊነት ነው!
#ኢቢሲ #
12/01/2026
#ለጥንቃቄ
"አንግለር ፊሺንግ፦ በማህበራዊ ሚዲያ እየተስፋፋ የመጣዉ አዲሱ የዲጂታል ወጥመድ"
አንግለር ፊሺንግ የጥቃት አይነት በዋናነት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ አጥቂዎች ራሳቸውን እንደ ደንበኛ አገልግሎት ሰጪ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ በመምሰል ተጠቃሚዎችን ያጠምዳሉ።
ጥቃቱ የሚጀምረው አጥቂዎች እንደ ባንክ፣ የቴሌኮም ድርጅት ወይም የታወቁ የንግድ ተቋማትን ትክክለኛ ገጾች (Official Pages) በመከታተል ነው።
አንግለር ፊሺንግ ስያሚዉን ያገኘዉ አንግለርፊሽ (Anglerfish) ከተባለዉና በዋናነት በጥልቅ ባሕር ውስጥ የሚኖር፣ እጅግ አስገራሚና አስፈሪ መልክ ያለው የዓሣ ዝርያ ነዉ።
?
👉1. ክትትል፦ አጥቂዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን (ለምሳሌ፦ ባንኮች፣ የቴሌኮም ኩባንያዎች ወይም የንግድ ተቋማት) የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይከታተላሉ።
👉2. ኢላማ መለየት፦ አንድ ደንበኛ በድርጅቱ ገጽ ላይ ቅሬታ ሲጽፍ ወይም እርዳታ ሲጠይቅ (ለምሳሌ፦ "ATM ካርዴ አልሰራም" ወይም "ኢንተርኔት ተቋርጦብኛል") አጥቂዎቹ ወዲያውኑ ያዩታል።
👉3. መመሰል፦ አጥቂዎቹ የድርጅቱን ትክክለኛ ስም እና አርማ (Logo) በመጠቀም የሐሰት አካውንት ይፈጥራሉ።
👉4. ተግባቦት፦ ለደንበኛው በግል መልዕክት ወይም በኮሜንት "ችግርዎን ለመፍታት እንርዳዎ፣ እባክዎ በዚህ ሊንክ መረጃዎን ይሙሉ" በማለት ምላሽ ይሰጣሉ።
👉5. መረጃ መስረቅ፦ ደንበኛው ሊንኩን ሲጫን ወደ ሐሰተኛ ድረ-ገጽ ይወሰዳል፤ እዚያም የባንክ መረጃውን ወይም የሶሻል ሚዲያ የይለፍ ቃሉን እንዲያስገባ ተደርጎ መረጃው ይዘረፋል።