Mere Media

Mere Media

Share

09/04/2023

በክልል ልዩ ኃይሎች ላይ የተላለፈው ውሳኔ፤ “ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ ይደረጋል” ጠሚዶክ አብይ አህመድ. what does it mean?

የሕዝባቸውን ቁጥር ለመጨመር ልጆች ለሚወልዱ ዜጎች ማበረታቻ የሚሰጡ አገራት - BBC News አማርኛ 06/04/2023

የሕዝባቸውን ቁጥር ለመጨመር ልጆች ለሚወልዱ ዜጎች ማበረታቻ የሚሰጡ አገራት
የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል እና የወሊድ ምጣኔ መቀነስ ለበርካታ አገራት አሳሳቢ ሆኗል።
አዲስ የሚተካ ትውልድ ቁጥር እየተመናመነ ነው። በአንዳንድ አገራት አረጋውያን ጧሪ አጥተው ፊታቸውን ወደ ሮቦቶች እስከ መዘርጋት ደርሰዋል።
ትኩስ የሠራተኛ ኃይል እጥረትም አጋጥሟቸዋል።
ይህም በምጣኔ ሃብታቸው ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ እንደሆነ ጥናቶች እያመለከቱ ነው።
ይህንን ስጋት ለመቀልበስ ታዲያ “እባካችሁ ውለዱ!” የሚል ተማፅኖን ጨምሮ ሌሎች የማበረታቻ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው።
ቻይና በስድስት አስርት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሕዝብ ብዛቷ መቀነሱን አስታውቃለች።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳም የወሊድ መጠን መቀነስ አገራቸውን አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደጣላት በመግለጽ፣ የአረጋውያን መብዛት “አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ አደጋ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም “ጃፓን እንደ ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ የምታቆምበት አፋፍ ላይ ትገኛለች” ብለዋል።
በአገሪቷ ያለው የወሊድ መጠን አዲስ ክብረ ወሰን በሆነ መጠን መቀነሱን ተከትሎም የቶክዮ ባለሥልጣናት፣ ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ ለማበረታታት ከሕጻናት ጋር የተያያዙ ፕሮግራሞች ላይ የሚያወጡትን ገንዘብ በእጥፍ እንደሚጨምሩ አስታውቀዋል።
ይሁን እንጂ ይህ ችግር እያሳሰባቸው ያለው ጃፓን እና ቻይናን ብቻ አይደለም።
ሌሎች አገራትም የወሊድ መጠንን ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። የተወሰኑትን እንመልከት፦

የሕዝባቸውን ቁጥር ለመጨመር ልጆች ለሚወልዱ ዜጎች ማበረታቻ የሚሰጡ አገራት - BBC News አማርኛ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳም የአገራቸው የወሊድ መጠን መቀነስ አገራቸውን አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደጣለው በመግለጽ፣ አረጋውያን መብዛት “አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ አደጋ ነው...

05/04/2023

አሜሪካ ወደ ገሃነም ትገባለች:: “ትራምፕ”

መረጃዎችን ለመደበቅ የንግድ መዝገቦችን አጭበርብረዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ወደ ገሃነም ትገባለች ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው በድፍረት ተናግረዋል።
ትራምፕ ማክሰኞ፣ መጋቢት 26/2015 በዋለው ችሎትም በሰጡት የምስክርነት ቃል ጥፋተኛ አይደለሁም ብለዋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መዘገቦችን አጭበረበሩ የተባለው ለአውሮፓውያኑ 2016 ምርጫ እየተሰናዱ በነበረበት ወቅት ነው።
ትራምፕ በኒውዮርክ በሚገኘው የማንሃተን ፍርድ ቤት 34 ክሶች ቀርቦባቸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነት በተወዳደሩበት ዋዜማ ከወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ጋር ምሥጢር አታውጪብኝ በሚል ከፈሉት በተባለው ገንዘብ እና ገንዘቡን ለማወራረድ ያቀረቡት ምክንያት ለዚህ የወንጀል ክስ ዳርጓቸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል የተከሰሱ የመጀመርያው ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
“የፈጸምኩት ብቸኛው ወንጀል አገራችንን ለማፍረስ እየጣሩ ካሉ ኃይሎች መከላከሌ ነው” ሲሉ የ76 ዓመቱ ትራምፕ ከፍርድ ቤት መልስ ፍሎሪዳ በሚገኘው ማር አ ላጎ መኖሪያ ቤታቸው ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።
• 34 ክሶች የቀረቡባቸው ትራምፕ ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ5 ሚያዚያ 2023
• ካረን ማክዱገል፡ ከትራምፕ ጉዳይ ጋር የተያያዘችው ሁለተኛዋ ሴት ማን ናት?5 ሚያዚያ 2023
• ትራምፕ የተጋረጠባቸውን የሕግ ፈተና የሚያስረዱ 7 ቁልፍ ጥያቄዎች3 ሚያዚያ 2023
የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚቀጥለው ዓመት አገሪቷ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ ለመግባት በዲሞክራቲክ ፓርቲ የተቀነባበረ የሴራ አካል ነው ሲሉም ክሱ ሃሰተኛ ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ትራምፕ በሚቀጥለው ዓመትም በሚደረገው ምርጫ ለመወዳደር እንዳሰቡም ተገልጿል።
ለአንድ ሰዓት ያህል በነበረው የችሎት ሂደትም ምንም አይነት ቃል ያልተነፈሱት ትራምፕ ዳኛ ሁዋን መርቻን ጥፋተኛ ስለመሆን አለመሆናቸው ብቻ ሲጠይቁዋቸው ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ የክስ መቃወሚያቸውን አሰምተዋል። ከፍርድ ቤትም ሲወጡ ለጋዜጠኞች ትንፍሽ ያሉት ነገር የለም።
ዶናልድ ትራምፕ በ2016 ምርጫ ወቅት እንቅፋት እንዳትሆንባቸው ለወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳኒኤልስ “ስለነበረን ነገር ትንፍሽ እንዳትይ” በሚል አፍ ማስያዣ 130ሺህ ዶላር ገንዘብ ዝውውር ያደረጉት በቀድሞ ጠበቃቸው ማይክል ኮህን በኩል ነበር።
እንዲህ ዓይነቱ ክፍያ ህገወጥ ባይሆንም ለፕሬዚዳንታዊ ዘመቻ ያግዝ ዘንድ ገንዘብ ማውጣትና ይህንንም ይፋ አለማድረግ የአገሪቱን የፌደራል የምርጫ ዘመቻ ፋይናንስ ህግን ይጥሳል።
ከትራምፕ በተቃራኒ የቆመው የቀድሞ ጠበቃቸው ኮህን ክፍያው የተፈጸመው በትራምፕ መመሪያ መሆኑን ተናግሯል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa
0000