Asset Real estate markting
ሰመር ሪል እስቴት 🔥 ለ7 ዕድለኞች ብቻ ልዩ ቅናሽ!
አዲስ ሳይት እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
👉50% የባንክ ብድር አማራጭ ያላቸው
➛እንዳሁም እስከ 5 ዓመት ከወለድ ነፃ
100% ለሚከፍሉ፦ በካሬ 62,000 ብር ብቻ!
10% ቅድመ ክፍያ ለሚከፍሉ፦ በካሬ 88,000 ብር!
➤ እንደ አከፋፈሎ ከ15% - 35% ልዩ ታላቅ ቅናሽ
👉ከባለ ሁለት እስከ ባለ አራት መኝታ
📞+251921388158 summer real estate
゚viralvideo
18/12/2025
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ ስምምነት ተፈራረሙ።
📌 አርቲስት እፀህይወት አበበ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።
| የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ የደንበኞቻቸውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት፣ የአየር መንገዱን የሽልማት መርሃ-ግብር (ShebaMiles) ከሪል እስቴት ግብይት ጋር የሚያስተሳስር ስምምነት ተደርጓል።
በዚህ ስምምነት መሰረት በአኮያ ፕሮፐርቲስ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን የሚገዙ ደንበኞች፣ የስታር አሊያንስ (Star Alliance) አባል ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ የጎልድ አባልነት ሽልማት በክብር ያገኛሉ። ይህም ደንበኞች በኢንቨስትመንታቸው ልክ የአየር መንገዱን ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና የሪል እስቴት ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተመልክቷል።
በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ አኮያ ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ፊልሞችና የጥበብ ስራዎቿ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈችውን አርቲስት እፀህይወት አበበን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በይፋ አስተዋውቋል። አርቲስቷ የድርጅቱን ገፅታ በመገንባትና የምርት ስሞቹን ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ስራዎችን እንደምትሰራ ተገልጿል።
ከ230 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረው አኮያ ግሩፕ፣ በውስጡ የተለያዩ ታላላቅ ድርጅቶችን አቅፎ የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው። ከእነዚህም መካከል፦
📍አኮያ ፕሮፐርቲስ፦ በሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ ቤቶችን የሚያቀርብ፣
📍አኮያ ኮፊ፦ በቡና ምርትና ኤክስፖርት ላይ የተሰማራ፣
📍አኮያ ሞተርስ፦ በተሽከርካሪ ግብይት ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ይገኙበታል።
Click here to claim your Sponsored Listing.