EthioScie Tech Zone
07/01/2021
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!!
……………✝️✝️✝️……………
24/11/2020
MQ-9 Reaper - ሰው አልባዋ የመከላከያ ሰራዊት ተዋጊ ድሮን (drone)
ሰሞኑን በትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት MQ-9 Reaper የተባለች የስለላ እና ተዋጊ ድሮን (ሰው አልባ ጀት ) እየተጠቀመ እንደሆነ በተለያዩ መንገዶች እየተጠቆመ ነው። የ አየር ሃይል አዛዡ ይህን በቀጥታ የሚያረጋግጥ ነገር ባይናገሩም፣ "ጠላቶቻችን በአሁኑ ሰአት የት እንዳሉ እናውቃለን" ማለታቸው ይህን ጭምጭምታ የሚያረጋግጥ ነው።
ለመሆኑ MQ-9 Reaper ማን ናት? ምን ምን ብቃቶች አሏት? ለጠቅላላ እውቀት ይረዳ ዘንድ በዚህ አጭር ፅሁፍ እንደሚከተለው ዳስሻታለሁ።
MQ-9 Reaper - አሜሪካ ሰራሿ ተዋጊ ድሮን
MQ-9 Reaper አሜሪካ ሰራሿ ሰው አልባ ድሮን 11 ሜትር ቁመት፣ 20 ሜትር የክንፍ ስፋት ያላት ለተለያዩ ሚሽኖች የምትውል ሰው አልባ ድሮን ናት። General Atomics Aeronautical Systems, Inc በተባለው የ አሜሪካ ዲፌንስ ኮንትራክተር ዲዛይን ተደርጋ የተሰራችዋ ይችው ድሮን ለመጀመሪያ ጊዜ ኦፕሬሽን ላይ የዋለቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 2007 ሲሆን አሜሪካ በዋናነት በውጭ ሀገራት ለምታደርጋቸው የስለላ እንዲሁም ለደህንነት ስጋት የሆኑ ተንቀሳቃሽም ሆነ የቆመ ታርገጌቶችን ነጥሎ የመምታት ኦፕሬሽኖቿን በብቃት ለማክናወን የሰራችው ድሮን ነው።
MQ-9 Reaper ድሮን እስከ 1,800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ውስጥ ሆኖ እንቅስቃሴዋን ሙሉ በሙሉ መከታተል እና ማዘዝ ይቻላል።
የድሮኗ አየር ላይ ለብዙ ጊዜ ቆሞ የመቆየት ብቃቷ (Loiter time)፣ ሰፊ ቦታ መሸፈን የሚችለው ሴንሰሯ (wide-range sensors)፣ መሬት ላይ ካሉ ስቴሽኖች ጋር ለመገናኘት ያላት ብቃት እና በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢላማ ብቃቷ (precision weapons) እጅግ ተፈላጊ (high-value)፣ ለአጭር ጊዜ ብቻ እይታ ላይ የሚቆዩ ኢላማዎችን (fleeting and time-sensitive targets) በብቃት ለመሰለል እና አልሞ ለመምታት ለየት ያለ ብቃት አላት።
ድሮኗ የምትልካቸውን ላይቭ ቪዲዮች ጠላት የት እንዳለ ለመከታተል ታስችላለች። የድሮኗ ዋና ብቃት ደግሞ፣ በብርሃን ጨረር እገዛ ተንቀሳቃሽ የሆነን የጠላትን ታርጌት በብቃት መከተታተል መቻሏ እና በዚሁ በብርሃን ጨረር የሚመራ ፈንጂ መሳሪያ (laser-guided munitions) መተኮስ መቻሏ ነው። ይህ ብቃቷ በጣም ኢላማን የጠበቀ (highly accurate)፣ በጣም ትንሽ የሆነ ከኢላማ ታርጌት ውጭ የሚደርስ ጉዳት (low-collateral damage) ያለው ድብደባን ለማድረግ ተመራጭ ያደርጋታል።
ከውጊያ ባሻገር፣ በድንበር አካባቢ ሊኖር የሚችል የህገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን እና መሰል የሰርቪላንስ ተግባሮችን ለማከናወን የምትውል ድሮን ናት። ድሮና ተነቃቅላ በኮንቴነር ውስጥ በመግባት ከቦታ ቦታ በቀላሉ መዘዋወር ትችላለች።
ሙሉ ገፅታዋ (specifications)
🔸ይህቺ ድሮን ከታች የተጠቀሱት ጠቅለል ያለ ገፅታ (specifications) አሏት:
📌ዋና ጥቅም - የጠላት ታርጌትን ፈልጎ መጨረስ
📌ቁመት - 11 ሜትር
📌የክንፍ ስፋት - 20 ሜትር
📌ከፍታ - 3.8 ሜትር
📌ያለ ጦር መሳሪያ ክብደት - 2,223 ኪሎ ግራም
📌መጫን የምትችለው የጦር መሳሪያ ክብደት - 1,701 ኪሎ ግራም
📌የበረራ ፍጥነት - በሰዓት 370 ኪሎ ሜትር
📌የበረራ ከፍታ - 50,000 ጫማ (15,240 ሜትር )
📌የአንዷ ድሮን ዋጋ - $64.2 ሚሊዮን (የአሜሪካን ዶላር )
▪️ምንጭ - U.S. Air Force
❤️SHARE AND SUPPORT❤️
➖Ⓒ ➖
15/11/2020
https://www.youtube.com/watch?v=HO4PnPvxoLU
የ Instagram ፎቶ እና ቪድዮ በቀላሉ በ Telegram Download ማድረግ||Download Instagram Image & Video Using Telegram 💥የ Instagram ፎቶ እና ቪድዮ በቀላሉ በ Telegram Download ማድረግ||Download Instagram Image & Video Using Telegram 💥Sponsored by ❤️ Download the soft...
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Telephone
Address
Addis Ababa