Tadele Kasse
02/02/2023
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናንንም አንድነታቸውን እንዲያስጠብቁና ይህ ባይሆን በቀጣይ ትውልድ ሁሉ የሚያስጠይቅ ይሆናል "በዚሁ ሂደትም ከጎናችሁ እንደምንቆም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ድርጊት እንዳስጨነቃቸውና በቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ ሕግ ብቻ መፈታት እንዳለበት እንደሚያምኑ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ገለጹ::
ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደሩ ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት ግንኙነት እንዳላቸውና ለዚህም ጥንካሬ መንፈሳዊ ትስስሩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን አክለውም በአሁኑ ሰዓት ያለችበት ሁኔታ እንዳሳዘናቸውና እንደኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይነታቸውም እንዳስጨንቃቸው ገልጸዋል።
በቀጣይም በራሷ በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መሰረት በውይይት እንዲፈታ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይቺን ቤተ ክርስቲያን ማፍረስ ማለት ሀገር ማፍረስ በመሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲሉ አጽንዖት የሰጡት አምባሳደሩ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትም እንደቀደመው ጊዜ በመተባበር እንደሚቀጥሉም አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናንንም አንድነታቸውን እንዲያስጠብቁና ይህ ባይሆን በቀጣይ ትውልድ ሁሉ የሚያስጠይቅ ይሆናል "በዚሁ ሂደትም ከጎናችሁ እንደምንቆም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
ማኀበረ ቅዱስ ቴሌቪዥን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Address
1221