Abu Ruffa

Abu Ruffa

Share

27/01/2024

Meqe xaagu taham

17/12/2023

ወጣቱን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ታኅሣሥ 7/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ወጣቱን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሁለት ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።

የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ፀጋዬ በማህበራዊ መገናኛ አውታር አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡

ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታኅሣሥ 2/2016 ዓ.ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን ያግቱታል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዮን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡

የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ ማውጣት ተችሏል፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5 ሺሕ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀል መፈፀማቸውን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዘሪሁን ተፈራ ማሳወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Afar State Dahuli
Addis Ababa