Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat

Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat

Share

Photos from Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat's post 15/08/2025

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤትና የአደጋ ፈንድ ተቋቋመ።
****************
ነሐሴ 09/2017
የምክር ቤቱ መቋቋም ዋና ዓላማ በአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር በቅድመ አደጋ፣ በአደጋ ጊዜ እና በድህረ አደጋ ወቅቶች በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ አሰራሩን ለማዘመን እና አገልግሎቶቹ ለከተማው አጠቃላይ ዘላቂ ልማት ቀጣይነት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ መሆኑን የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ዘመን ተስፋዬ ገልፀዋል።

ደንቡ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት እና የአደጋ ጊዜ ፈንድ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር191/2017" ተብሎ እንደተሰየመም አቶ ዘመን አክለው ገልፀዋል።

የተቋቋመው ኮሚቴም በአደጋ ስጋት አመራር እና በሚከሰት አደጋ የተጎዱ ሰዎች የአሰቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የመልሶ ግንባታና በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም እንቅስቃሴዎች ላይ አተኩሮ እንዲሰራም ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን የመጠባበቂያ ፈንዱን የመሰብሰብ፣ የማስተዳደር ፣ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ አፈጻጸሙንም የመከታተልና የመቆጣጠር ስራ እንዲሰራም አቶ ዘመን በአቅጣጫ መልኩ አስቀምጠዋል።

23/07/2025

በክረምቱ አልፎ አልፎ የሚኖር ከባድ ዝናብ ሊያስከትል ከሚችለው ቅጽበታዊ ጎርፍ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ ።

በመጪዎቹ አስር ቀናት አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ።

የኢንስቲትዩቱ መግለጫ እንዳስታውቀው በመጪዎቹ አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በበርካታ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ይኖራቸዋል።

በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት እንደሚኖራቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።

የሚጠበቀው እርጥበት ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ትንበያው ያሳያል።

ስጋቶችን ለመቀነስና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች በተገቢው ሁኔታ መተግበር እንደሚያስፈልግ አመላክቷል።

በሚኖረው እርጥበት ዘር መዝራት፣ ትርፍ ውሃን ከማሳ በማጠንፈፍ ማስወገድ፣ የአፈር መሸርሸር ስጋትን ለመቀነስ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጠቁሟል።

ረባዳማ በሆኑ ማሳዎች የውሃ ማንጣፈፍ ስራዎች መስራትና የደረሱ የበልግ ሰብሎችን በሚኖሩ ደረቅ ቀናቶች መሰብሰብ እንዲሁም የሚገኘውን እርጥበት በመጠቀም የመኸር ዘር መዝራት እንደሚገባም አብራርቷል።

በቀጣዮቹ አስር ቀናት በሚኖረው ዝናብ በአብዛኛው ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖርም መግለጫው ያመላክታል።

አልፎ አልፎ ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል አስረድቷል።

ስለሆነም በወንዝ ዳርቻ እንዲሁም ረግረጋማ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውና የሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት አደጋን በመቀነስ መልካም እድሎችን እንዲጠቀሙም አስገንዝቧል።

የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት፣ወራጅ ውሃን በእግርም ሆነ በቀላል ተሽከርካሪ ለማቋረጥ አለመሞከር፣ የጎርፍ የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን ማፅዳት፣ የዝናብ ውሃ ማሰባሰብና ማጠራቀም እንደሚገባ ተመላክቷል ።

Photos from Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat's post 23/06/2025

በወረዳዉ አስተዳደር በእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ዙሪያ እንዲሁም ከኤሌክትሪክ ጋር ተያይዞ የ4ኛ ሩብ አመት እና የ12ወራት ቅንጅታዊ አሰራር ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተገመገመ
=============================
ሰኔ 12/2017 ዓ.ም
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር
በዋና ስራ አስፈፃሚ ዋና ሰብሳቢነት በስራ አስኪያጅ ምክትል ሰብሳቢነት የሚመራው በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር እና አወጋገድ ፣በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣በእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ዙሪያ እንዲሁም ከኤሌክትሪክ ጋር ተያይዞ የ4ኛ ሩብ አመት እና የ12ወራት ቅንጅታዊ አሰራር በመገምገም ፤ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እንጠያየቅ መድረክ አካሄደ።

በመጨረሻም በቅንጅታዊ አሰራር የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት የእዉቅናና ሽልማት በማበርከት መድረኩ ተጠናቋል

Photos from Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat's post 27/05/2025

ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች አደጋውን ለመከላከል የሚያስችሉ የማቅለያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።

በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች እየተከናወኑ ያሉ የማቅለያና የመፍትሄ እርምጃዎች የደረሱበትን ደረጃ ለመገምገም በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የተመራ በቅንጅት የጎርፍ መከላከልን ስራ እያከናወኑ ያሉ የከተማ አስተዳደር የሴክተር ተቋማትና የተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የክፍለከተሞች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

በመስክ ምልከታው ማጠቃለያ ላይ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት ለአደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች እየተወሰዱ ያሉ የማቅለያና መፍትሄ የመስጠት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ጠቅሰዉ ያልተጠናቀቁ ቀሪ ስራዎች የክረምቱ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ከመግባቱ በፊት ባሉት ጥቂት ጊዚያት አስቀድሞ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

አያይዘዉም በተለይም ኑሯቸዉን በወንዝ ዳርቻ ያደረጉና ለአደጋ ተጋላጭ የነበሩ ነዋሪዎችን ከአደጋ ወደተጠበቀና ምቹ ወደሆነ አካባቢ መዘዋራቸዉንና ቦታዉም በወንዝ ዳርቻ ልማት ታቅፎ እየለማ መሆኑን ጠቅሰዉ ለጎርፍ አደጋ ምክንያት የሚሆኑ የፍሳሽ መስመሮችን በተለያዩ ባዕድ ነገሮች ባለመዝጋትና ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገዉ ጥረት ህብረተሰቡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተባባሪ በመሆን የመፍትሄዉ አካል እንዲሆንም አሳስበዋል።

በመስክ ምልከታዉ በአቃቂ ፣ በነፋስ ስልክ፣ በአዲስ ከተማ፣ ቂርቆስ እና በአራዳ ክፍለ-ከተሞች ባሉ እየተከናወኑ ያሉ የጎርፍ መከላከልና የማቅለያ ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱም የሴክተር ተቋማት፣ የክፍለ-ከተሞች ዋና ስራ አሰፈጻሚዎችና ስራ አስኪያጆች ፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና የአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa