Dr. Solomon werku
የጡት ካንሰር
ከአንዳንድ ለጡት ካንሰር መጋለጥ እድልዎን ይቀንሱ።
የጡት ካንሰር ማለት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የጡት ሴሎች ዕድገት ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ በሽታ የሚጠቁት ሴቶች ቢሆኑም የጡት ካንሰር በወንዶችም ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡
የጡት ካንሰር ዋነኛ ምልክቶች
ዕጢ፣ እብጠት እና የቆዳ ለውጥ ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ ሊከሰት ይችላል፡፡ እነዚህ ምልክቶችም የሚከሰቱባቸው ሰዎች ግዴታ በጡት ካንሰር በሽታ ተይዘዋል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህን ምልክቶች ካዩ ወደ ክሊኒክ በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡
በጡት ላይ የሚደረግ የግል ፍተሻ
በየወሩ ቢደረግ ጠቃሚ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በማንኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች ይህን በማድረግ ራሳቸውን ከጡት ካንሰር መጠበቅ እንደሚችሉም ይመክራሉ፡፡ ይህን ለማድረግ ምቹ ጊዜ የወር አበባ መጥቶ ከሄደ በኃላ በሚከቱሉት ቀናት ቢሆን ይመከራል፡፡ አብዛኞች ሴቶች የራሳቸውን የጡት ካንሰር የሚያገኙት በጡቶቻቸው ላይ ያለውን ለውጥ በመመልከትና በጡታቸው አካባቢ ያለውን ስሜታቸውን በመረዳት ነው።
የጡት ካንሰር ምርመራ
መጀመር ያለበት ምንም ዓይነት የበሽታው ስሜት ባይሰማዎትም ጭምር ነው፡፡ በተለይ ከ40 ዓመታቸው በላይ ያሉ ወይም በቤተሰባቸው ውስጥ የጡት ካንሰር ታሪክ ያለባቸው ሴቶች በየሁለት ዓመቱ አንዴ የማሞግራም ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡ ማሞግራም አነስተኛ ጨረር በመጠቀም ጡቶችን በሁለት ከፕላስቲክ በተሰሩ ጠፍጣፋ ትሪዎች መሃከል አድርጎ በመጫን ከተለያየ አቅጣጫ ምስልን በማንሳት የሚደረግ የጡት ምርመራ ነው፡፡
በጡት ላይ በሚደረግ ፍተሻ ወቅት የጡት እባጭ የሚገኝባቸው ታካሚዎች በተጨማሪ የአልትራ ሳውንድ እና የኤም.አር.አይ (MRI) ምርመራ ሊታዘዝላቸው ይችላል፡፡ ከነዚህ የተገኘውም ውጤት አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ ከእባጩ ላይ በመርፌ ናሙና በመውሰድ (Fine Needle Assessment ወይም Biopsy) ካንሰር መሆኑን ወይም አለመሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እባጩ ካንሰር ያልሆነ እጢ (benign tumor) ሆኖ ይገኛል፡፡ ካንሰር የሆነ እባጭም (malignant tumor) በሚገኝበት ጊዜ በቶሎ እርምጃ በመውሰድ በዘመናዊ ህክምና ታክሞ መዳን ይቻላል፡፡
የጡት ካንሰር ህክምና
አብዛኛውን ጊዜ የሚጀመረው የቀዶ ጥገና በማድረግ ካንሰር የሆነውን እባጭ በማስወገድ ሲሆን ይህን ደግሞ የሚወስነው እባጩ የደረሰበት ደረጃ ነው፡፡
የጡት ካንሰር ሶስት አይነት ህክምና ይኖረዋል
1- ጨረር (Radiotherapy)
2- ኬሞ ቴራፒ (Chemotherapy)
3- ቀዶ ጥግና (Surgery)
አንዱ ወይም ሁሉም አይነት ህክምና ለአንድ ሰው ሊሰጥ ይችላል።
ጤና ይስጥልን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
DOCTOR