Eyerusalem Negash
የተጠራነው የወንጌል ጡረተኛ ልንሆን ሳይሆን የወንጌሉ ባለ ዐደራ ለመሆን ነው።
ይህ ደግሞ እስከ መራብ፣ መጠላት ሳይሆን እስከ ሞት ዋጋ ይጠይቀናል!
በዚህ ዘመን እግዚአብሔርንና የልቡን ሃሳብ መከተል እንደምን መታደልነው!
ኃጢያተኛነታችን በእግዚአብሔር ከመወደድ አላስቀረንም። ችግሩ በአንዱ ልጁ በኢየሱስ ሙሉ ስራ ባለማመን በራሳችን ልንወደድ ደፋቀና ማለታችን ነው! የሚያስደንቀው በልጁ ያመነ የኃጢያት ባሪያ መሆኑ ቀርቶለታል!
19/06/2026
በዚህ እውቀት እንደ ዶፍ ዝናብ በሚወርድበት ዘመነ ቴክኖሎጂ፥ ክርስቶስን ብቻ ለማወቅ መትጋት፣ በቃሉ ብቻ መዋጥ፣ በመስቀሉ ፍቅር መክነፍ፣ በመንፈሱ መመራትን ያድለን። እንደ ዻውሎስ ከክርስቶስና ክርስቶስ እውቀት ውጪ ሌላ ላለማወቅ ራስን ማቀብ ምንኛ ፀጋና ሃይል ይጠይቃል?
ወገኖቼ በዚህች ከንቱ ዓለም ክርስቶስን ማወቅን የመሰለ “እውቀት” የለም። ይህ ታዲያ ለአሁን ብቻም ሳይሆን ለሚመጣውም ዓለም ትርፋማ ያደርጋል። ከዚህ ውጪ ያለው ግን አላፊ ጠፊም ነው። ለምን ቢባል ከሞት ወዲያ አይሻገርምና! እንደ አካል በስባሽና ረጋፊ፣ ከአፈር ተለውሶ ወድቆ ተበትኖ የሚቀር ነውና!!
እናማ ምን ለማለት ነው? በሞት ፈንታ ህይወት የሰጠንን፣ በጨለማው ዓለም በብርሃኑ የሚያወጣ የሚያገባንን፣ በተሸነፈ ዓለም በድል የሚያኖረንን እርሱን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ ይንጋልን ይምሽልንም። አሜን።
መልካም ቀን!
እየሩ
Click here to claim your Sponsored Listing.