Ethio Coding

Ethio Coding

Share

20/10/2025

ቴሌግራም በ SMS Code ኢትዮጵያ ውስጥ መላክ አቁሟል !

❗ቴሌግራም ኢትዮጵያ ውስጥ Verification code በ SMS መልኩ መላክ አቁሟል ።

📌 አዲስ ለሚከፈቱ አካውንት ብቻ Code የሚልክ ሲሆን እንደገና login ለምትሉ ግን code በ sms መላኪያ premium ግዙ ብሏል 🙄

(ይህን ጉዳይ ከ አሁን በፊት አሳውቄ ነበር )

📌 ቡዙ ሰዎች ወደ ድሮው የቴሌግራም አካውንት መላክ መግባት ተቸግረዋል ።

🎯 ምክንያቱ ኢትዮጵያ ለ SMS የምጠይቀው ዋጋ ውድ በመሆኑ ምክንያት ።

🎯 በመሆኑም ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የ ቴሌግራም አካውንት የሚከፍቱ ሰዎች verification code የሚላክላቸው በ email ነው ። email ማስገባት ይጠበቅባችዋል ።

🎯 ከ አሁን በፊት ከፍቶ እንደአጋጣሚ Logout ቢልና እንደገና ለመግባት ቢሞክር በ SMS ኮድ አይደርሳችሁም ስለዚህ የቴሌግራም አካውንታችሁ ላይ Email add አድርጉ ምናልባት በአጋጣሚ log out ብትሉት በኢሜል ኮዱ ይላክላችኋል ።

🎯 email ከለላችሁ ግን ብዙ መረጃ ያስቀመጣችሁበት የቴሌግራም አካውንት መመለስ አትችሉም ።

🎯 ሁለተኛው አካውንት መመለሻ መንገድ የቴሌግራም premium ተጠቃሚ መሆን አለባችሁ ። ቴሌግራም ለ premium ተጠቃሚዎች በ SMS code ይልካል ።
ስለዚህ emai የላችሁ ሆኖ መግባት ቢያቅታችሁ መግቢያው መንገድ ይህ ነው

በጓደኛችሁ በኩል premium ተገዞቶ በ username ኣችሁ እንዲላክ ማድረግ ። username የግድ ሊኖራችሁ ይገባል ።

በ username ችሁ ነው premium ሚላክላችሁ ።

username እንዳላችሁ ቸክ አድርጉ ።

📌 ማስታወሻ ፦ በተለይ ቴሌግራም ላይ ጠቃሚ መረጃና ላላችሁ ሰዎች ና ቴሌግራምን በብዛት ለምትጠቀሙ ሰዎች ።

(ይህን ያስታውሱ )

1) Username ማድረግ አትርሱ
2) አዲስ አካውንት ለምትከፍቱ Email አድ አድርጉ
3) ለጥንቃቄ ከሌላ ስልክ ወይም Pc login በሉ ። በኋላ Scan አድርጋችሁ ለመግባት እንዲቀላችሁ !

4) Code በ SMS ካልደረሳችሁ የመጨረሻ መፍትሔ Telegram premium መግዛት አለባችሁ ።

TikTok · Tewos_Technologies 25/01/2025

TikTok · Tewos_Technologies Check out Tewos_Technologies’s video.

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa