Yami Media

Yami Media

Share

23/03/2022

[


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል።

አቶ ተወልደ ይህን የገለፁት ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብለው ጡረታ መውጣታቸውን ገልፀው ፤ ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጠዋል።

አቶ ተወልድ አየር መንገዱን ለ37 አመት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ያገለገሉ ሲሆን ላለፉት 11 አመታት በዋና ስራ አስፈፃሚነት አገልግለዋል።

አቶ ተወልደ በአገልግሎት ዘመናቸው " የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ስራ አስፈፃሚ " ን ጨምሮ እጅግ በርካታ ሽልማቶችን ለግላቸው እና ለአየር መንገዱ አስገኝተዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማን እንደሚሆን እስካሁን አልታወቀም/ ይፋ አልተደረገም።

መረጃው የኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ (https://t.me/ethiopiacheck/1152) ድረገፅ ነው።

23/03/2022

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ለ ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ዘጋቢው ቶማስ ጋርድነር ማስጠንቀቂያ ሰጠ!

የኢፌዲሪ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ለተሰኘው ጋዜጣ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ቶማስ ጋርድነር የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጠ።

: “መጋቢት 10 ቀን በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሕወሓት መሪ ጋር ተነጋገሩ” በማለት በግል የትዊተር ገፁ ያሰራጨውን መረጃ የተመለከተው ባለስልጣኑ፤ የቶማስ ጋርድነር መረጃ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሀገራዊ ጉዳይ ሲሆን ተገቢውን የመረጃ ምንጭ ያልጠቀሰ እና በሚመለከተው ባለስልጣን ያልተደገፈ ነው ብሏል።

ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው “ይህ ተግባር የጋዜጠኛነትን ሙያ እና ንቃት የማይመጥን” በመሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል። በቀጣይ ዘገባዎቹም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጋዜጣኛውን አስጠንቅቋል።

22/03/2022

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑክ ጋር የልማት ፕሮጀክቶችን ለመስራት ተፈራረሙ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከልዑኩ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በዘላቂ ልማት ዙሪያ ላይ ከተወያዩ በኋላ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑካን ቡድን ከክልሉ መንግስት ጋር በዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፣ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በህብረተሰቡ ህይወት ላይ ካደረሰው ተፅዕኖ መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ የልማት መርሃ ግብሮችን ለመተግበር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በማቀድና በመተግበር ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

4kilo
Addis Ababa