Netsanet Getachew

Netsanet Getachew

Share

21/06/2026

ዛሬ ይፋ በተደረገው ሀገራዊ የምርጫ ውጤት ተቃዋሚ ፓርቲዎች 41 የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸነፉ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች 41፣ የግል ዕጩዎች ደግሞ 8 የፓርላማ መቀመጫዎች ማሸነፋቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ።

ከሶስት ሳምንት በፊት በተካሄደው በዚህ ምርጫ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን 438 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ መቆጣጠሩንም ቦርዱ አስታውቋል።

ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው፤ ዛሬ እሁድ ሰኔ 14፤ 2018 በአዲስ አበባው ስካይላይት ሆቴል ባካሄደው የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሃ ግብር ነው።

ቦርዱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤትን ይፋ ያደረገው፤ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ካስቀመጠው ዕለት 10 ቀናት ዘግይቶ ነው።

የአሸናፊ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የግል ተወዳዳሪዎች ስምና ለየምክር ቤቱ ያሸነፉትን መቀመጫ ብዛት የያዘ ይፋዊ መግለጫ ከምርጫ ቀን ቀጥሎ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ቦርዱ ማውጣት እንዳለበት በህግ ተደነግጓል።

ይህ የሚደረገው ግን “ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር” እንደሆነም በ2011 ዓ.ም. በወጣው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ላይ ሰፍሯል።

በዚህ መሰረት ምርጫ ቦርድ በማዕከል ደረጃ ያረጋገጣቸውን የተወሰኑ የምርጫ ውጤቶችን በየጊዜው ሲያሳውቅ ቆይቷል።

ቦርዱ እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ ይፋ ካደረጋቸው 96 የፓርላማ መቀመጫ ውጤቶች ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያሸነፉት የፓርላማ መቀመጫ ብዛት 19 ነበር።

https://t.me/helloethiopiamedia

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዶች ተዘረፈ 21/06/2026

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዶች ተዘረፈ Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

6killo
Addis Ababa