Aman design
1. አንድን ሰው (እንደሰማህ እያወቅክ) በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አትጥራው፡፡ መልስ ካልሰጠህ ምናልባት የሆነ እየሰራው ያለው ነገር ሊኖር እንደሚችል ወይም በራሱ ምክንያት መልስ ሊሰጥህ እንዳልፈለገ ይግባህ፡፡
2. የተበደርከውን ገንዘብ አበዳሪህ ከመጠየቁ በፊት መልስ፡፡ ምን ያህል ለቃልህ ታማኝና ሃላፊነት የሚሰማህ ሰው እንደሆንክ ማረጋገጫው እሱ ነው፡፡በአንጻሩ የተበደርከውን ጃንጥላም ቢሆን እስክሪፕቶ ሳትጠየቅ መመለስ ቁምነገረኝነትህን ያሳያል፡፡
3. ማንም ሰው ሊጋብዝህ ወደሆቴል ቢወስድህ ከሜኑው ውስጥ ውድ ዋጋ የሚያወጣውን ምግብ አትዘዝ፡፡ሰዎች ምን ደግ ቢሆኑ ይሉኝታ የሌለው ሰውን መታዘባቸው እንደማይቀር አትርሳ፡፡
4. ማንንም ሰው “ለምን እስካሁን አላገባህም/ሽም?" አይነት የግል ጥያቄዎችን አትጠይቅ። ወይም "ለምን ልጅ አልወለድክም/ሽም " አትበል፡፡ ይህ የነርሱ እንጂ ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ አይነት ጥያቄ ሰዎችን ያሳቅቃል፡፡
5. በር ከፍተህ ስትገባ ከኋላህ ወንድም ሆነ ሴት፣ ትልቅም ሆነ ትንሽ ሰው ቢኖር በሩ በላያቸው እንዳይዘጋ ያዝላቸው፡፡ ለሰዎች ትህትና ማሳየት አንተን ያስከብርህ ይሆናል እንጂ ትንሽ አያደርግህም፡፡
6. ከጓደኛህ ጋር ታክሲ ተሳፍረህ ስትሄድ እሱ ከከፈለ ሌላ ቀን ደግሞ ራስህ ክፈል፡፡ ፈቅዶ ካልሆነ በቀር በይሉኝታ ማንም ሰው ያንተን ወጪ የመካፈል ግዴታ የለበትም፡፡
7. ሁሌም እኔ ብቻ ልክ ነኝ አትበል፡፡ ላንተ 6 ቁጥር የሚመስለው ለሌላው ሰው 9 ቁጥር ሊሆን ይችላል፡፡ ትክክልነት ካለህበት አንጻር የሚታይ አንጻራዊነት ነው፡፡ ካንተ የተለየ አስተያየት ማግኘት ይጠቅምሃል እንጂ አይጎዳህም፡፡
8. ሰው ሲናገር እስኪጨርስ ጠብቅ እንጂ አታቋርጥ፡፡ አንድ ሰው ለማለት የሚፈልገውን ሳይጨርስ አስተያየት መስጠት ወደስህተት ሊመራህ ይችላል፡፡
9. በሰዎች ላይ በቀልድ አታሹፍ፡፡ በተለይ ሹፈቱን ካልወደዱት ወዲያውኑ አቁም፡፡ እንዲህ ያለውን ነገር አለመድገም ለሰዎች ስሜት ምን ያህል እንደምትጠነቀቅ ማሳያ ነው፡፡
10. ሁሌም ሰዎች በጥያቄህ መሰረት ከረዱህ በኋላ “አመሰግናለሁ” ማለት ይልመድብህ፡፡
11. ሰዎችን በአደባባይ አመስግን፡፡ የሚታረም ነገር ካላቸውም ቀስ ብለህ በግላቸው ንገራቸው እንጂ በሰው ፊት አታሳጣቸው፡፡ ለመሻሻል የሚጠቅማቸው ይህንን ማድረግህ ነው፡፡
12. ማንንም ሰው ክብደቱን በተመለከተ አስተያየት አትስጥ፡፡ ምናልባት ጥሩ ለብሶ/ሳ ካየህ “ዛሬ ዘንጠሃል ወይም በጣም ታምሪያለሽ” ብቻ በል፡፡ሰዎች ስለውፍረታቸውና ስለቅጥነታቸው ከፈለጉ ራሳቸው ይናገሩ እንጂ ያንተ አስተያየት ሊያበሳጫቸው ይችላል፡፡
13. ሰዎች በስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ሲሰጡህ ያሳዩህን ብቻ አይተህ መልስ፡፡ ሳይፈቀድልህ ወደቀጣዩ ፎቶ አትሂድ፡፡ በድንገት የግል እና ማንም እንዲያየው የማይፈልጉትን ፎቶ አይተህ ቅር ልታሰኛቸው ትችላለህ፡፡
14. አንድ የሥራ ባልደረባህ ሃኪም ጋር ቀጠሮ አለኝ ካለህ “ምንህን አሞህ ነው?” ብለህ አትጠይቅ፡፡ "ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ" ብቻ በል፡፡ የሰዎችን ግላዊነት አክብር፡፡
15. በመስሪያ ቤትህ ስራ አስፈጻሚም ይሁን ጽዳት ሰራተኛ ሁሉንም ሰው በአክብሮት ጥራ፡፡ ብዙዎች “ለሁሉ ትሁት ነው” የሚሉትን ሰው አብልጠው እንደሚወዱና እንደሚያቀርቡ እወቅ፡፡
16. ከሰው ጋር እያወራህ ሳለ በፍጹም ስልክህን አትመልከት፡፡ ይህ ለሰውየው ያለህን ንቀት ማሳያ ነውና ይቀየምሃል፡፡
17. ለሰው ምክር መስጠት ያለብህ ከጠየቀህ ወይም ከፈለገ ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አብዝቶ የሚመክራቸ
Click here to claim your Sponsored Listing.