Bitaniya Tube

Bitaniya Tube

Share

12/08/2025

የሱባዔ ዓይነቶች

የግል ሱባዔ /ዝግ ሱባዔ/

የግል ሱባዔ አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ ገዳም ውስጥ ባለ ዋሻ በቤቱና በአመቺ ቦታ የሚይዘው፤ ማንም ሰው ሳያየው በግሉ የጸሎት በኣቱን ዘግቶ በሰቂለ ኅሊና ሆኖ ፈጣሪው እግዚአብሔርን እያሰበ ጸሎቱን እንዲሰማው በኅቡዕ የሚፈጽመው ሱባዔ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ‹‹ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና… አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ያስረክብሃል›› በማለት የግል ሱባኤ ስንገባ ማድረግ ስለሚገባንን ጥንቃቄ ነግሮናል /ማቴ.6፥5-13/፡፡

በእንዲህ ዓይነት መልክ አምላኩን በጸሎት ለመማጸን ሱባዔ የገባን ሰው ዘጋ እያልን እንናገራለን፡፡ ዝግ ሱባዔ የያዘ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር ይዞ ወደ በኣቱ ወይም ወደ መጸለያው ስፍራ ከገባ በኋላ ሱባዔውን እስኪፈጽም ድረስ ከማንኛውም ሰው ጋር መገናኘት አይችልም፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ፡፡ እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ በፈረስ ቤት እንዳለ እነደ ጉጉት ሆንሁ ተጋሁ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ›› እንዲል /መዝ.101፥6-7/፡፡

የማኅበር ሱባዔ

የማኅበር ሱባዔ የሚባለው ካህናት፣ ምእመናን ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሌዎችና ወጣቶች በአንድ ሆነው በቤተ ክርስቲያንና ለጸሎት አመቺ በሆኑ ቦታዎች ተሰብስበው የሚገቡት ሱባዔ ነው፡፡ የቅዱሳን ሐዋርያት ተከታዮች የኾኑ መነኮሳት፣ ካህናትና ምእመናን በገዳማት፣ በአድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ እንደ ማኅበረ እስጢፋኖስ ጉባኤያቸው እንዲሰፋ፤ ከሐሰተኞችና ከመናፍቃን እንዲጠብቃቸው፤ በመካከላቸው እየገባ ዲያብሎስ እንዳይፈትናቸው የማኅበር ሱባዔ ይይዛሉ::

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa