Tuludimtu
09/05/2025
የቆስጣ ለጤና ያለው 11 ገፀ በረከቶች
ቆስጣ ሳይንሳዊ መጠሪያው ስፒናሲያ ኦለራሴ ይሰኛል:: በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ተመራጭ ምግብ ነው:: ለብዙ ሺህ ዓመታትም ሲመገቡት ቆይተዋል::
መገኛው ኢራን ናት:: በዚህም ተክሉን ለረዥም ዓመታት በመመገብ የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛለች:: ባሁኑ ሰዓት አገራችንን ጨምሮ በአሜሪካና በቻይና በስፋት እየተመረተ ይገኛል፡፡
ቆስጣ ሲቀምሱት ከሚሰጠን ጣፋጭ ጣዕም ውጪ በርካታ ለጤና አስፈላጊ የሆኑ አልሚ ምግቦችን ይዟል:: በጥሬውም ሆነ አብስለን ልንመገበው እንችላለን::
ይሁንና ቆስጣን አብስለን ማስቀመጥ የለብንም:: ከሰራነው በኃላ ወዲው መመገብ ይኖርብናል:: በጥሬው የመንመገበው ከሆነ በጭማቂ መልክ ብንመገበው መልካም ነው:: ምክንያቱም ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታዎችን ያስገኝልናል::
1. ከስጋ የምናገኘውን የፕሮቲን መጠንም ከቆስጣ ማግኘት እንችላለን:: ለጤና ጠቃሚ የሆነው ኦሜጋፋቲ አሲድንም ይዟል::
2. የቆስጣ ጭማቂ ከፍተኛ ብረት አለው:: መጠኑም ከጥቅል ጐመንና ከካሮት ከምናገኘው በእጥፍ ይበልጣል::
3. ቆስጣ ቪታሚን ኬ እና ማግኒዥየም ስላለው አዘውትረን ብንመገበው መልካም ነው:: እንደሚታወቀው ቪታሚን ኬ ለአጥንት ጤንነት ይጠቅማል::
ከአንድ ኩባያ የበሰለ ቆስጣ 98 በመቶ የሚሆነውን በየቀኑ የሚያስፈልገንን ቪታሚን ኬ ስናገኝ 39 በመቶ ደግሞ ማግኒዥየም እናገኛለን::
ቫይታሚን ኬ የሰውነታችን አጥንቶች እንዲጐለብቱ ያደርጋል:: በተለይ ለሴቶች እጅግ ጠቃሚ ነው:: ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ የአጥንት መሳሳት ችግር የሚያጋጥማቸው ሴቶች ናቸው:
: እ.ኤ.አ በ1999 የአሜሪካ ጆርናል ኦፍ ክሊኒካል ኒዩትሬሽን እንዳረጋገጠው የቪታሚን ኬ እጥረት ያለባት በመካከለኛ እድሜ ላይ የምትገኝ ሴት የዳሌ አጥንት መሰንጠቅ (መሰበር) ሊያጋጥማት ይችላል::
ይህ የአጥንት መሰንጠቅ ችግር ወንዶች ላይ ሊከሰት የሚችለው እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ነው:: ይሁንና ወንድም ሆነ ሴት በብዛት ቪታሚን ኬ የሚያገኙ ከሆነ ከአጥንት ስብራትና መሰንጠቅ አደጋዎች ሊጠበቁ ይችላሉ::
4. በተጨማሪም በቆስጣ ውስጥ ያለው ፖታሽየም የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል::
5. ቆስጣን በየቀኑ በመመገብ የብረት እጥረትን ማስወገድ ይቻላል:: 36 በመቶ የሚሆነውን በየቀኑ የሚያስፈልገንን የብረት መጠንም ከአንድ ኩባያ ከተሠራ ቆስጣ ልናገኘው እንችላለን::
6. ቆስጣ በቪታሚን ኤ የበለፀገ ነው:: ቪታሚን ኤ ለሰውነት ህዋሳት ዕድገት አስፈላጊ ነው:: ፀጉራችን እንዲያድግና ወዙን ጠብቆ እንዲቆይም ያደርጋል::
ለዚህም የቆስጣ ጭማቂን መጠቀም ተመራጭ ነው:: ቪታሚን ኤ የሪቲኖይድ ውህድ አለው:: ይህ ውህድ ፀረ ፈንገስ በመሆኑ ቆዳ ለይ የሚወጣ ፈንገስን ያክማል::
7. ቆስጣ የፋይቶኒዩትሬንት ስብስብ ነው:: ይህም ከሌሎች የአትክልት አይነቶች በተለየ ሁኔታ ካንሰርን መዋጋት እንዲችል አድርጐታል:: ካንሠርን እንዲዋጋ ያደረገውም ሜቴሌንዲ ኦሊፍላቮኖል ግሎሮናዲስ የሚባል ኤጄንት ነው::
በተጨማሪም በጣም ጥሩ የሆኑ በሽታን መቋቋም የሚችሉ ሉቲይን፣ ዚአዝንቲን፣ ኑኦዛንቲን እና ቫዩዚንቲን የሚባሉ ካንሰርን የሚከላከሉ አንቲ ኦክሲዳንቶችን ይዟል::
8. አንዳንድ ጥናቶቸ እንደሚያመለክቱት ደግሞ ቆስጣ የፕሮስቴት እና የጡት ካንሰር እንዳይፈጠር ይረዳል:: እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የተደረገ ጥናት በበኩሉ እንዳረጋገጠው በሳምንት ከሁለት ጊዜ በላይ ያልበሰለ ቆስጣ የምትመገብ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ አነስተኛ ነወ::
በቅርቡ ማለትም እ.ኤ.አ በ2009 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ደግሞ ቆስጣን አዘውትረው የሚመገቡ ሴቶች ከማይመገቡ ሴቶች ለማህፀን ካንሰር የመጋለጥ ሁኔታቸው ዝቅ ያለ ነው::
9. የቆስጣ ጥቅም ይህ ብቻ አይደለም በውስጡ ያለው ቤተ ካሮቲን የአስም በሽታን እንዲከላከል አድርጐታል:: ማግኒዥየምም ተመሳሳይ ስራ ያከናውናል፤ አስምን በመከላከገል ረገድ:: ሌላው በውስጡ የሚገኘው የአልፋሊፖኢክ አሲድ ከፍተኛ በሽታ ተከላካይ ኦንቲኦክሲዳንት አለው::
ይህ አሲድ በደም ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠንን ይቀንሳል:: እንዲሁም የኢንሱሊን ምላሽን ያፋጥናል:: በስኳር ህመምተኞች ላይ የሚከሰተውን የእጅ መልፈስፈስና መደንዘዝ ይቀንሳል::
10. በሽታን በመከላከል ረገድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ቆስጣ ለልብ ጤንነትም ወሳኝ ነው:: በውስጡ የሚገኘው ፓታሽየም ዝቅተኛ ደም ግፊትንና ስትሮክን ይከላከላል:: በልብ ህመም ምክንያት የሚከሰት ሞትን ይቀንሳል::
11. ፎሊክ አሲድ ለነፍሰ ጡር እናቶች አስፈላጊ ነው:: ቆስጣም በፎሊክ አሲድ የበለፀገ በመሆኑ ለነፍሰ ጡር እናቶች በየቀኑ እንዲመገቡ ማድረግ ጠቃሚ ነው:: 66 በመቶ የሚሆነውን በየቀኑ የሚያስፈልጋቸውን ፎሊክ አሲድ ከአንድ ኩባያ የቆስጣ ጭማቂ ማግኘት ይችላሉ::
04/05/2025
E even Liverpool on top of the league today I can not expect to leave one / three goals shame to me!!!
Fulltime Report: Chelsea 3-1 Liverpool| All Football Fulltime Report: Chelsea 3-1 Liverpool| All Football
Kenyal Labour Day Celebration
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
01/05/2025