Muler mulex

Muler mulex

Share

የአማራ ጦር ወልቃይትን ሲቆጣጠር የፋሲል ደሞዝ አስገራሚ ንግግር 17/11/2020

https://youtu.be/JDpzXMrZoxI

የአማራ ጦር ወልቃይትን ሲቆጣጠር የፋሲል ደሞዝ አስገራሚ ንግግር ወልቃይት እና ሁመራ አስገራሚው የአማራ ጦር ጀብድ

28/05/2020

እግዚአብሔር ዐረገ

አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። መዝ ፵፮ ፡ ፭።

ዐረገ ማለት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ ማለት ነው።

በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ ማለትም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ዕሪና (መብለጥ ማነስ የሌለበት መተካከል) ያመለክታል። ይህም የሥልጣን እኩልነት የመንበርን አንድነት ይገልጥልናል። የአብ የመንፈስ ቅዱስ መንበር እርሱ የወልድም መንበር ነውና። ከፍና ዝቅ ያለ ዙፋን የለም። ኹለትና ሦስትም አይደለም። አንድ ብቻ ነው እንጅ።

ዐረገ ስንል ጌታችን ስለተዋሐደው ሥጋ ክብር እየተናገርን እንደኾነ እንወቅ። ቅድመ ዓለም በቃልነቱ የወልድ ስፍራው ይኸው ነው። ስፍራው ያልነው ልዕልናውን መኾኑ ይታወቅ። ድኅረ ዓለምም ከልዕልናው ለቅጽበት ዝቅ አላለም። ስፍራውን አልለቀቀም።

በዚያ መንበር ተቀምጦ የማያውቀው ሥጋ ነበረ። በተዋሕዶ ከበረ ስንል ትስብዕት (ሥጋ) ወደዚህ የልዕልና ደረጃ ከፍ አለ ማለታችን ነው። ይህም በማኅፀነ ድንግል ቃል ሥጋ ሲኾን የተደረገ እንጅ ፴፫ ዓመት ከ፫ ወር ጠብቆ የደረሰበት አይደለም። ተዋሐደ ማለት ከኹለት አንድ ኾነ ብቻ ሳይኾን ከበረ ማለትም ነውና። ሰው አምላክ ኾነ ከማለት የሚተካከል ሌላ ምን ክብር አለ?

በጌታ ልደት የዘመሩት ቅዱሳን መላእክት በሰማይም በምድርም ምስጋና ይኹን ያሉት ለምን ይመስላችኋል? ሉቃ ፪ ፡ ፲፬። እዚህ በምድር በእመቤታችን እቅፍ የሚያዩትን ሥግው ቃል ወደ ሰማይ ሲያቀኑ በዘባነ ኪሩብ በማየታቸው ነው። በምድር በትሕትና ስላዩት ያመሰገኑትን በሰማይ በልዕልና ስላዩት ተገረሙ። በምድር አመስግነው እንዳይፈጽሙ በሰማይ ይታያቸዋል። በሰማይ ብለው እንዳይቀሩ በምድር ይታያቸዋል። ስለዚህ በአንድ ጊዜ በምድርም በሰማይም ላለው ምስጋና አቀረቡለት።

ሥግው ቃል - ሰው የኾነው አምላክ (God The Incarnate) በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሥኖ በዚህ ዓለም ሲመላለስ ከየማነ አብ ከዘባነ ኪሩብ ሳይለይ ነው። የደቀ መዛሙርቱን እግር በጉልበቱ ተንበርክኮ ሲያጥብ ሥግው ቃል ከየማነ አብ ከዘባነ ኪሩብ ሳይለይ ነው።

ለዚህም ነው ራሱ ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው" ያለው። ዮሐ ፫ ፡ ፲፫። ይህን ቃል ሲናገር በምድር እንደነበረ ግልጽ ነው። ግን በዚያችው ቅጽበት የሰው ልጅ በሰማይ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እየተሠለሰ እየተቀደሰ ነበረ። ስለዚህ በዚህ በምድር አብሮን እያለ በሰማይ መኖሩን ነገረን።

ስለዚህ ዐረገ ሲባል በተዋሐደው ሥጋ ይዳሰስልን የነበረው ከእንግዲህ የማይዳሰስ ኾነ፤ ከእንግዲህ እናየዋለን እንጅ አንዳስሰውም ማለትን ያጠይቃል። ዐረገ ማለት ቦታ ለቀቀ አይምሰለን። እግዚአብሔር ሔደ፣ መጣ ቢባል ተሰወረ ተገለጠ ማለት እንጅ ምሉዕ በኩለሄ ነውና ወደየት ይሔዳል ወደየትስ ይመጣል? ሲሔድም ሲመጣም ቦታውን አይለቅቅም። ስለዚህ ሲመጣ ተገለጠ ሲሔድ ተሰወረ እንላለን።

ሥግው ቃል ዐረገ ሲባልም ከእንግዲህ፡-

- [ ] የሚከፍለው ካሣ የለም
- [ ] የትሕትና ሥራውን ፈጽሟል
- [ ] በኃይልና በሥልጣኑ ይገለጣል
- [ ] በመለኮታዊ ባሕርይው በቀደመ አኗኗሩ ይገኛል
- [ ] ብናየው እንጅ አንዳስሰውም ማለት ነው።

ሲመጣ የሰማነውን ሲሔድ ዐየነው። ርደት ያለበት ዕርገት የእርሱ ብቻ ነው። ቅዱሳን ቢያርጉ ወደ ማያውቁት አዲስ ቦታ ነው። ጌታ ግን ወደ ነበረበት ብቻ ሳይኾን ወደ አለበት ነው ያረገው። ለጌታ ዕርገት አዲሱ ነገር የእኛ ማየት ብቻ ነው።

ጌታችን ሲያርግ ቅዱሳን ሐዋርያትን ባርኳቸዋል። "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ" እንዲል። ሉቃ ፳፬ ፡ ፶-፶፩። የቡራኬ ቀን ነውና እኛንም ይባርከን። ስንባረክ ቡሩክ ሥራ እንሠራለንና። እነርሱ ሲባረኩ ሰግደውለታል። ሳይንበረከኩ መባረክ የለምና። በክርስትና ከፍ ለማለት ዝቅ ማለት ይቀድማል። ዝቅ ማለት በትሕትና። ቅዱሳን ጌታ ሲያርግ በሰቂለ ሕሊና በተመስጦ ልቡና ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር። ሥራ ፩ ፡ ፲። መባረክ ወደ ሰማይ ያሳያል። ስንባረክ ልባችንም መሻታችንም ከክርስቶስ ጋር ያርጋል። እኛ በእግረ ልቡና እርሱ በአካል።

ከፍ እንበል። የሚወርዱ መኖራቸው እኛን ከፍ አያደርገንም። ካለንበት በጥቂቱም ቢኾን ከፍ እንበል። ልዕልና ወዳለው መንፈሳዊ ሥራ ልቡናችንን እናሳርገው።

እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa