Muler
16/05/2022
በትሮጃን ቫይረስ ተጠቂ የሆነ ኮምፒውተር የሚያሳያቸው ምልክቶች የትኞቹ ናቸዉ?
የትሮጃን (Trojan) ቫይረስ በኢ-ሜይል ወይም በሌሎች ዘዴዎች ማለትም በማህበራዊ የትስስር ገጾች ወይም ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ክምችቶች በተጠቃሚዎች የጥንቃቄ ጉድለትና የእውቀት ክፍተት ምክንያት የሚወርዱና የሚጫኑ አጥፊ ሶፍትዌሮች ናቸው።
እንደየ ቫይረሱ አይነት ስራቸውና አላማቸው የተለያየ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ግን ጥቃት የደረሰባቸው ኮምፒውተሮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ
• የኮምፒውተር ስክሪን ከለር መቀያየርና በትክክል አለመስራት ለምሳሌ ብልጭ ድርግም ማለት፤
• የስክሪን የጀርባ ምስል ወይም የምስል ውቀሮችን መቀያየር፤
• ኮምፒውተሩ ያለትእዛዝ ዶክመንቶችን ፕሪንት ለማድረግ መሞከር፤
• ያለተጠቃሚው ትዕዛዝ የድር ጣቢያዎች(website) መክፈት፤
• የድምጽ መጠን በድንገት መለዋወጥ፤
• የጸረ-ቫይረስ ፕሮግራሞች ወይም መተግበሪያዎች ማቆም እና የዳታ መቀየር፣ መጥፋት ወይም መበላሸት፤
• የኮምፒውተሩ የሰዓት እና ቀን መለወጥ፤
• የማውስ ከርሰር (ወይም ጠቋሚ) በራሱ መንቀሳቀስና የቀኝና የግራ ጠቋሚ አሰራርና ተግባር መለዋወጥ፤
• የዊንዶውስ የስታርት ቁልፍ( በተን) መጥፋት፤
• ፖፕ አፖች (ወይም ብቅ ብቅ የሚሉ የመተግበሪያ ክፍሎች) ግልጽ ካልሆነ መልዕክት ጋር መምጣትና ተጠቃሚውን መረበሽ፤
• የኪቦርድና የማውስ ስራ ማቆም ፤
• ተጠቃሚው ግንኙነት ከሌለው አካል የኢ-ሜይል መልዕክት መምጣት ፤
• እንግዳ የሆኑ የጥያቄና የማስጠንቀቂያ የመልዕክት ሳጥኖች ከአዎንታዊና አሉታዊ አማራጮች (በሁሉም አማራጮች ተጠቃሚውን ለሌላ ጥቃት በር መክፈቻነት ጋር መምጣት፤
• ባልተለመደ መንገድ የኮምፒውተር የእንደገና መነሳት(ሪስታርቲንግ)፤
• የታስክ ማናጀር ስራ ማቆም ይህም ለአጥቂው ወይም ለትሮጃኑ ተጠቃሚው ምን ምን ፕሮሰሶች ስራ እየሰሩ እንደሆነ እንዳያውቅ ለማደረግ እና በትሮጃኑ የተጫኑ ፕሮሰሶች ራሳቸውን እንዲደብቁ ለማድረግ ያስችላል፤
• የሲስተም ፍጥነት ወይም የስራ ሂደት አቅም መገደብ ወይም መቀነስ፤
• የትክክለኛ መተግበሪያዎች ስራ ማቆም ወይም በትክክል አለመስራት እና መረበሽ፤
11/05/2022
ማይክሮሶፍት ወርሃዊ ዝመና መርሃ ግብሩ የዊንዶዉስ ምርቶች 75 የክፍተት መጠገኛዎችን አቀረበ
አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 3/2014: ማይክሮሶፍት በግንቦት /2022-የወርሃዊ ዝመና መርሃ ግብሩ ለዊንዶዉስ ምርቶች 75 የክፍተት መጠገኛዎችን ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ሶስቱ የዜሮ-ደይ ክፍተቶች (zero-day vulnerability) የሚዉሉ መጠገኛዎች መሆናቸዉ ታዉቋል።
በዚህ ወር መጠገኛ ከቀረበላቸዉ 75 ተጋላጭነቶች መካከል ስምንቱ የመረጃ መንታፊዎች በርቀት ሆነዉ የተጠቃሚዎችን እንቅስቃሴ መከታተል የሚያስችሉ በመሆናቸዉ የክፍተት መጠገኛዎቹ “እጅግ ወሳኝ” መጠገኛ ተብለው ተመድበዋል።
የዚህ ወር ለዊንዶዉስ ምርቶች ከቀረቡ መጠገኛዎች መካከል ለሶስት የዜሮ-ቀን ተጋላጭነቶች መጠገኛዎች እንደሚገኙበት ያሳወቀዉ ማይክሮሶፍት ከእነዚህ መካከል አንደኛው በንቃት ጥቅም ላይ የዋለ እና ሌሎቹ በይፋ የታወቁ ክፍተቶች መሆናቸዉን ጠቁሟል።
ማይክሮሶፍት አንድ ተጋላጭነት በይፋ የተገለጸ ወይም ምንም አይነት ይፋዊ የክፍተት መጠገኛ ከሌለውና ክፍተቱ ለመረጃ በርባሪዎች ጥቅም ላይ እንደ ዜሮ-ደይ ክፍተት በማለት ይመድባል።
የቀረቡትን የጥቃት ተጋላጭነት ለመድፈን የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች በመተግበር ብቻ የማይክሮሶፍት ምርቶችን ማዘመን እንችላለን። በመጀመሪያ “stat” የሚለዉን መምረጥ በመቀጠል ከቀረቡ አማራጮች መካከል “setting” የሚለዉን መምረጥ ከዚያ “update and security” በመጫን በመጨረሻ “Check for update” የሚለዉን በመምረጥ ማዘመኛዉን መተግበር ይቻላል።
በመሆኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተጠቃሚዎች እነዚህን ለጥቃት አጋላጭ ክፍተቶችን ለመድፈን ሳያመነቱ በማይክሮሶፍት የቀረቡትን የደህንነት ዝመናዎች በተቻለ ፍጥነት መተግበርን በጥብቅ ይመክራል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
A. A
Addis Ababa